TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድና ም/ጠ/ሚር #ደመቀ_መኮንን በአማራ ክልል የሚገኘውን የኩሳኤ ቀበሌ ስንዴ ማሳ ክላስተር ጎበኙ። የሀገራችን የግብርና ኮመርሻላይዜሽን ክላስተር አሰራር አራት አላማዎች አሉት፡፡ እነርሱም የአነስተኛ አርሶ አደሩን ገቢ ማሣደግ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያን ማመቻቸት፣ የአግሮ ኘሮሰሲንግና የእሴት ጭማሪ ስራን ማሣደግ እና የሥራ እድልን መፍጠር ናቸው፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድና ም/ጠ/ሚር #ደመቀ_መኮንን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር የካቲት 6 ቀን 2011 ተወያዩ። ካለፈው የቀጠለው ይህ ውይይት በዋናነት የኮሚቴውን የስራ እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን ገምግሟል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም ኮሚቴው ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እንዲያጠናክር አቅጣጫ በመስጠት የበኩላቸውን ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጁባ🔝

ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድና ፕሬዝዳንት #ኢሳይያስ_አፍወርቂ ደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ሲገቡ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ መሪዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንትና ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በሀገር ውስጥና በቀጠናው #ሰላም ዙሪያ ይወያያሉ፡፡

ፎቶ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሩዳንዳ የዘር ጭፍጨፋ መታሠቢያ🔝

ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው ለሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ በተዘጋጀዉ የእግር ጉዞ ላይ ተሳትፈዋል። የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ ላይ ለመገኘት ወደ ሩዋንዳ የቀኑት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በእግር ጉዞው የተሳተፉት ከፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜና ከሌሎችም የአለም መሪዎች ጋር በመሆን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሩዋንዳ ቆይታቸውን አጠናቀው ትላንት ማምሻዉን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምንጭ:-ጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia