TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ማሳሰቢያ

የቲክቫህን የመረጃ አቀራርብን እንዲሁም መረጃዎችን የማከማቸት አሰራር #በማስመሰል የተለያዩ አካላት ሀሰተኛ መረጃዎችን እየሰራጩ ነው፤ በተመሳሳይ አቀራረብም የተከፈቱ እጅግ በርካታ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች አሉ እኛን የሚወክሉ አይደሉም።

በዚህ ገፅ ላይ የሚሰባሰቡት እና የሚከማቹ መረጃዎችን የቲክቫህን ስምን መጥቀስ ሳይጠበቅባችሁ በየትኛውም ሚዲያ፣ በየትኛውም ገፅ የማሰራጨት ሙሉ መብት አላችሁ፤ ነገር ግን ከታች የምንናስቀምጣቸውን ወይም መረጃው ከየት እንደተገኘ የሚገልፁ [የሚዲያዎች ስም፣ የግለሰቦች ስም፣ የተለያዩ ተቋማት ስም] መጥቀስ እንዳትረሱ።

ከዚህ ውጪ የገፁን አጠቃላይ አቀራረብ በማስመሰል፣ የምንከተላቸውን መንገዶች በመጠቀምና ያላስቀመጥናቸውን መረጃዎች እንዳስቀመጥን አድርጋችሁ የምታሰራጩ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ። ይህ ካልሆነ ግን እያንዳንዱ የሚሰሩትን ስራዎች በማንና እንዴት እየተሰሩ እንደሆነ እየተከታተልን ስለሆን በህግ የምናስጠይቅ ይሆናል።

ትክክለኞቹ የTIKVAH-ETH ቻናሎች፡-

- ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ700,000 በላይ ተከታይ ያሉት
(https://t.iss.one/tikvahethiopia)

- ቲክቫህ ማጋዚን 150,000 በላይ ተከታዮች ያሉት
(https://t.iss.one/tikvahethmagazine)

- ቲክቫህ ስፓርት ከ63,000 በላይ ተከታዮች ያሉት
(https://t.iss.one/tikvahethsport)

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከአ/አ ወደ ወላይታ ዞን የገባው የኮቪድ-19 ታማሚ! ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (COVID-19) ላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዳለበት የተረጋገጠበት አንድ ዕድሜው 20 የሆነ ግለሰብ ትክክለኛ ባለሆነ መንገድ ተደብቆ ህብረተሰቡን ለአደጋ ሊያጋልጥ በሚችል መልኩ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ወላይታ ዞን ገብቷል። ግለሰቡ ወደ ወላይታ ዞን ከገባ በኋላ በህብረተሰቡ…
#ATTENTION

በትላትናው ዕለት የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አንድ ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ ዞን ስለገባ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ታማሚ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል።

ዛሬ ከዞኑ ጤና መምሪያ በወጣው መረጃ መሰረት ግለሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ ዞን በህዝብ ትራንስፖርት (አይሩፍ/አባዱላ መኪና) ቅዳሜ ሰኔ 6/2012 ዓ/ም እንደገባ ተገልጿል።

በዕለቱ በእነዚህ መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ የገቡ ግለሰቦች እና አሽከርካሪዎች ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ብሎም ለህብረተሰቡ ሲሉ በአቅራቢያ ወዳሉ ጤና ተቋማት/ዞን ጤና መምሪያ ሪፖርት እንዲያደርጉ #ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በዕለቱ ተጠርጣሪውን ጭኖ የመጣውን መኪናና አብረውት የመጡ ሰዎችን ለማግኘት የዞን እና የከተማ ፀጥታ አካለት እየሠሩ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ የዞኑ ጤና መምሪያ ጥሪ አቀርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

የኳታር መንግስት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና ሽብርተኝነትን በፋይናንስ መደገፍን ለመከላከል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 20/2019 “ማንኛውም ዜጋ ወደ አገሪቱ ሲገባም ሆነ ሲወጣ ከ 50,000 በላይ የቀጠር ሪያል ካሽ እና ተመሳሳይ ዋጋ ያላቸው ውድ ጌጣ ጌጦችን ለጉምሩክ መስሪያ ቤት ማሳወቅ እንደሚገባው” ደንግጓል።

ከላይ የተጠቀሱ ንብረቶች ሳያሳውቁ ከሀገር ለመውጣት ወይም ለመግባት መሞከር ፣ የተሳሳተ መረጃ መስጠት ወይም ደግሞ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ንብረቱን ከመወረስ አልፎ እስከ 3 ዓመት እስር ወይም ከ100,000 እስከ 500,000 የኳታር ሪያል ቅጣት እንደሚያስከትል በህጉ ተቀምጧል።

በመሆኑም በኳታር ነዋሪ የሆናችሁ የኢትዮጵያ ዜጎች ከአገሪቱ ስትወጡም ሆነ ስትገቡ የምትይዙትን ከ50,000 በላይ የሆነ የቀጠር ሪያል የገንዘብ መጠን (በኳታር ሪያል፣ በውጭ አገር ገንዘቦች፣ በቼክ እና የመሳሰሉት) እንዲሁም ከላይ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን በላይ ዋጋ ያላቸውን ውድ ንብረቶች (ወርቅ ፣ ብር ፣ ፕላቲኒዬም፣ ዳያመንድ እና የመሳሰሉትን) በጉምሩክ ጣቢያዎች በማስመዝገብ (declare በማድረግ) ከማንኛውም ህጋዊ ርምጃ ራሳችሁን እንድትጠብቁ በዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

በጢስ አባይ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሚካሄደው ጥገና ምክንያት የጢስ አባይ ፏፏቴ ውሃ ከነገ የካቲት 27/2013 ዓ/ም ጀምሮ መጠኑ ጨምሮ ስለሚለቀቅ ከፏፏቴው ግርጌ በሚገኙ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተብሏል።

#መልዕክቱን_ለሌሎች_ያድረሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

"ነገ ስራ ዝግ ሆኖ ይውላል"

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ነገ እንደማንኛውም የስራ ዝግ ቀን/እንደ በዓል ቀን ስራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል በድጋሚ ተናግረዋል።

ከትራንስፖርት ፣ ከመሰረታዊ እና ከድንገተኛ አገልግሎት (ዋና ዋና አገልግሎት) ከሚሰጡት ተቋማት በስተቀር ሌሎች ስራ ዝግ ሆነው ይውላሉ ብለዋል።

የትራንስፖርት ፣ የመሰረታዊ ፣ ድንገተኛ እና አስቸኳይ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትና ሰራተኞች አሰራራቸውን ይዘው ይቀጥላሉ። ከዛ ውጭ ያሉት ግን ተዘግተው መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

"አንዳንድ ቦታዎች ላይ ነገ ስራ ካልገባችሁ ትቀጣላችሁ/ስራ ግዴታ መግባት አለባችሁ" የሚሉ አካላትን አይትናል ያሉት ወይዘሪት ሶሊያና ይህ ህጋዊ አይደለም፤ የአዋጁን አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታን የሚጥስ ተግባር ነው ብለዋል።

"ስራ ግዴታ መግባት አለባችሁ" የሚሉ አሰሪዎች ህግን ከሚጥስ የወንጀል ተግባር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

"ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው" - ፖሊስ

የቡሔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችቶችን መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የቡሔ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚተኮሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ ሰላምን የመደፍረስ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ የገዙትን የጦር መሣሪያ እንደሚፈትሹና የተለያዩ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ሁኔታዎች እንደሚፈጥሩ ፖሊስ በተለያዩ ጊዚያት ባደረጋቸው ጥናቶችና በደረሰው መረጃ ያረጋገጠ መሆኑን ገልጾ ማንኛውም ግለሰብ ሆነ ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ እንደማይችል ተገንዝቦ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ሁኔታው ለህገ-ወጦች ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ የከተማዋ ፀጥታ ስጋት እንዳይሆን ህብረተሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ ለፖሊስ አባላት መረጃዎችን እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ፍቃድ ሣይሰጥበት ርችቶችን በሚተኩሱ ግለሠቦች ሆኑ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቋል፡፡

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን ዛሬ አሳውቋል። ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሙን ተቋሙ ገልጿል፡፡ ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አዳዲሶቹ የደንብ አልባሳትን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ እና ነባሩ የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ መቀየሩ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ፖሊስ አሮጌውን የደንብ ልብስ ለብሶ የተገኘ አመራር እና አባል…
#ማሳሰቢያ

" የፖሊስ ደንብ አልባሳትን አስመስሎ መጠቀም ፍፁም ክልክል ነው " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነባሩን በመተካት ሥራ ላይ ያዋላቸውን ሦስት ዓይነት የደንብ አልባሳትን አስመስሎ መጠቀም ፍፁም ክልክል መሆኑን አስታውቋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የፖሊስ ተቋማትን ለማዘመን በተያዘው ስትራቴጂካዊ እቅድ የፖሊስ ሠራዊት አርማ እና የደንብ ልብስ እንዲቀየር በተወሰነው መሰረት የአዲስ አበባ ፖሊስ አዲስ አርማና የደንብ ልብስ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነባሩን የደንብ ልብስ በሦስት ልዩ ልዩ ዩኒፎርሞች ተክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኦሞ ሸሚዝ በጥቁር ሰማያዊ ሱሪ ከነ መለዮው፣ ካኪ ሱሪ እና ሸሚዝ በቦኔት መለዮ የደንብ ልብስን ለመደበኛ የፖሊስ ስራ እንዲሁም ቡራቡሬ ወይም ሬንጀር መልክ ያለው ለቋሚና ተወርዋሪ ኃይል የሚጠቀም መሆኑን ገልጿል።

አዲስ ስራ ላይ የዋለውን ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል መሆኑ በህግ የተደነገገ ስለሆነ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ፖሊስ አሳስቧል።

የአ/አ ፖሊስ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረው ነባሩ የደንብ ልብስ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑ ከዚህ በፊት መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

ቤት የሚገዙ፣ የሚሸጡ ሁሉ ስራቸው ህገወጥ ስለሆነ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት አሳስቧል።

የቋሚ ንብረት ሽያጭ የቆመ ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎቱ ሳይጀመር ሽያጭ እና ማስተላልፈ በመንደር ውል እና በውክል እየተሰራ መሆኑ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ፤ በውክልናም ሆነ በመንደር ውል የቤት ሽያጭ ማከናወን ህጉ እንደማይፈቅድ ገልፀዋል።

አገልግሎቱ የሚጀምርበትን ጊዜ እናሳውቃለን ብለዋል።

" ቤት ሽያጭ ውል ሰነድ የማረጋገጥ አገልግሎት ነው " ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ " ይህ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል። ተቋሙ በተለይ ከአ/አ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ህገወጥ ይዞታዎችን የማረጋገጥ ስራ እየሰረ ስለሆነ ከዛ ጋር ተያይዞ ላልተገባ ሰዎች ያልተገባ ውል ውስጥ እንዳይገቡ ያን የማረጋገጥ ስራ እስኪጠናቀቅ በጊዜያዊነት አገልግሎቱን መስጥ ቆሟል " ሲሉ አስረድተዋል።

ይሄ ህገወጥ ይዞታዎችን የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙሉቀን ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ላልተወሰ ጊዜ የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም መኖሪያ ቤት ሽያጭ / በስጦታ የማስተላለፍ ውሉ አሁንም ለጊዜው እንደተቋረጠ ይቀጥላል ሲሉ አሳውቀዋል።

ተቋሙ የተቋረጠውን አገልግሎት በሚጀምርበት ሰዓት በግልፅ በተለያየ ሚዲያ መረጃውን የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።

በተለይ የተጠራቀመ አገልግሎት ካለ ተገልጋዮች በሰልፍ ብዙ ሳንይገላቱ ለመስራት አሰራር ተዘርግቶ ይኬዳል ሲሉ ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ ላልተገባ የመንደር ውል ሆነ ባልተገባ መረጀ ላይ ተመስርቶ ከሚደረጉ ውሎች እንዲቆጠብ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ለሸገር ራድዮ በሰጠው ቃል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ የህልውና ዘመቻ ላይ መሆኗ በማስታወስ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመከላከል፣ ኢትዮጵያ የተደቀነባትን የግዛት አንድነት ስጋትና ሉአላዊነት ጥሰት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መውስድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮሙዩኒኬሽንና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ኤምባሲ ወይም ዲፕሎማት፣ በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች እና ላኪዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

1. ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች ፦
• የጦር ሜዳ መነጽር (binokular)
• ኮምፓስ (Compass)
• የጂፒኤስ መሳሪያ (GPS)

2. ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች ፦
• መገናኛ ሬዲዮ (Walkie Talkies radio)
• ሳተላይት ስልክ (satellite phone)

3. ቪሳት እና ቢጋን (A very small aperture terminal (VSAT) and Broadband Global Area network (BGAN))

4. ድሮኖች (Drones)

እነዚህን የመገናኛ እና ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጅንሲ በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0113851193 ፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ እንደሚጠበቅበት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

ለሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች ፦

በአዲስ አበባ የምንቀሳቀሱ ሞተር ብስክሌቶች ማሟላት ያለባችሁ ነገሮች ማለትም ፦

1. የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ፣
2. የታዳሰ የመንቀሳቀሻ ፈቃድ፣
3. በህጋዊ መንገድ የተሰጠ የመንቀሳቀሻ ፈቃድ፣
4. የተገጠመለት ጂ.ፒ. ኤስ በትክክል የሚሰራ፣
5. ቀይ መብራቱ በአግባቡ የሚሰራ መሆኑን ማረጋገጥ እነዚህን ሳያሟሉ ሲያሽከረክሩ ከተገኙ ለመጀመሪያ ጊዜ 500 ብር፣ ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ እጥፍ ወይም (1000) ብር እንዲከፍሉ በህግ ተቀምጧል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ እነዚህ እና መሰል ጉዮችን እየፈተሸ ተገቢውን ክትትል እና ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ስለሆነም ማሟላት ያለባችሁን ነገር በማሟላት ካለስፈላጊ ጥፋት እና ቅጣት እራሳችሁን እንድትጠብቁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት በትራንስፖርት ዘርፍ የወጡ የመከላከያ መንገዶች በአግባቡ እንዲተገበሩ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ አሳስቧል።

ቢሮው ዛሬ በትራንስፖርት ዘርፍ የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የቫረሱን ስርጭት ለመቀነስ በትራንስፖርት ዘርፍ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል።

የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት፦
- የተሽከርካሪዎችን ንጽህና መጠበቅ፣
- አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ማስክ መጠቀም
- ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ እንደሚገባም ተብራርቷል፡፡

የኮቪድ ስርጭት ለመግታት በወጣው መመሪያ መሰረት ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ከተገኙ ብር 1 ሺህ የሚያስቀጣ ሲሆን፥ ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት በአንድ ሰው 500 ብር የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል። የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል…
#ማሳሰቢያ

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አውንታዊ ድጋፍ ለሚሹ አመልካቾች student.ethernet.edu.et በመግባት ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

በተመሳሳይም በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች result.neaea.gov.et በመግባት እና Compliant የሚለውን በመጫን ቅሬታቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ ሲል አሳውቋል።

ኤጀንሲው ምላሹን በማመልከቻ ቅጹ ላይ በሚያስቀምጡት አድርሻ እንደሚያሳውቅ የገለፀ ሲሆን በአካል ወደ ኤጀንሲው መምጣት አያስፈልግም ብሏል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ መርሀ ግብር ለመማር የሚመዘገቡ ተማሪዎች የሚከተሉትን የቅበላ መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚኖርባቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለሥልጣን አስታውቋል።

እነዚህም፡-

1. የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ከሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያስቀመጠውን የመቁረጫ ነጥብ ሊያሟሉ ይገባል፡፡

2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች ከሆኑ ከሠለጠኑበት የሙያ መስክ ጋር ተዛማጅነት ባለው የሥልጠና መስክ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በደረጃ 4 (ወይም በቀድሞ 10+3 ወይም 12+2) ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን፤ እንዲሁም በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ሥራ ልምድ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች በምዝገባው እለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለዲግሪ መርሃ-ግብር መግቢያ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡

4. በየተቋማቱ የሚዘጋጁትን የመግቢያ ፈተናዎች ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፤ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች በምዝገባው ዕለት ማቅረብ ያልቻለ ተመዝጋቢ ህጋዊ ተቀባይነት አይኖረውም።

ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ህጋዊ መመሪያዎችን ጥሶ የተገኘ ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የስነ ስርዓት መመሪያ መሠረት በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ከህግ ውጪ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎችም ሊደርስባቸው የሚችለውን የጊዜ፣ የገንዘብና የስነ-ልቦና ኪሳራ አውቀው አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለስልጣኑ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና !

በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል HCP በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና /CATARACT SURGERY/ ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 12/2014 ዓ.ም ለማድረግ አስቧል፡፡

ይህን ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ በግንቦት ወር ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናቶች ማለትም (ግንቦት 6፣ 7፣ 13፣ 14፣20፣ 21፣27 ፣28 ) ይካሄዳል።

በኮሌጁ የስልክ አገልግሎት 976 በመደወል ለቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።

#ማሳሰቢያ ፡- በስልክ ቀጠሮ ያልተሰጠዉ ታካሚ ቅድመ ምርመራም፣ ልየታም ይሁን ምዝገባ ማድረግ አይችልም ተብሏል።

(ውድ ቤተሰቦቻችን መልዕክቱን አጋሩ)

@tikvahethiopia
#TikvahFamily

ስለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ፦

• ቲክቫህ/ተስፋ ኢትዮጵያ ሰውነትን ያስቀደሙ ሁሉንም የሰው ፍጡር፣ ህዝብን እና ሀገርን የሚያከብሩ ፣ በማንኛውም ጉዳይ ሚዛናዊ አመለካከት ያዳበሩ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።

• የቤተሰቡ አባላት መረጃ ማካፈል፣ አንዱ ያልሰማውን ሌላው እንዲሰማው መጠቆም ፣ በሚዲያ ላይ የሚከታተሉትን ሌላው የቤተሰቡ አባል እንዲያውቀው ማድረግ ይችላሉ። በአጭሩ የቤተሰብ አባላቱ እርስ በእርስ መረጃ ልውውጥ የሚያደርጉበት ነው። (ምንጭ በመጥቀስ)

• በቤተሰቡ / አባላት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ የሚቻል ሲሆን አንዲት ቃል ስድብ ሆነ የሰዎችን ክብር ፣ ሃይማኖት፣ ብሄር ማንነትን የሚነካ መልዕክት መላክ ከቤተሰቡ ወዲያው በቀጥታ ያስቀንሳል።

• ቲክቫህ ኢትዮ. ከተመሰረተ አንስቶ ከማንም ወገን ፣ ከየትኛውም አካል (የመንግስት ሆነ ተቃዋሚ፣ አልያም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት) ጋር ግንኙነት የሌለው ሲሆን በየትኛውም አካል አይደግፍም፤ አይታግዘም። ለስራ በሚል ከቤተሰቡ ገንዘብ አይጠይቅም አያሰባስብም።

ተቋርጠው የነበሩ የቤተሰቡን ስራዎች ስለማስቀጠል ፦

- ባለፉት ሁለት ክረምቶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በጦርነት ሳቢያ ዓመታዊ ለገጠር ት/ቤቶች የሚደረገው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እና የፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህ አመት ለማስቀጠል ዝግጅት ተደርጓል።

- ሲቆራረጥ የነበረው ለግለሰቦች የሚደረግ የህክምና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻም በዚህ ዓመት የሚጀምር ሲሆን ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ስራው ይሰራ የሚለውን ሃሳብ ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ማሳወቅ ትችላላችሁ።

- ከዚህ ቀደም በቤተሰቡ አባላት የሚተላለፉ አጭር የቅሬታ ፣ የጥቆማ፣ የፀጥታ ችግር ማሳወቂያ ፣ ትችት፣ ጥያቄ በስፋት መላክ ይቻላል። እንደከዚህ ቀደሙ መልዕክት ሲላክ አጭር ከጥላቻ ሃሳብ የፀዳ እና የመፍትሄ ሃሳብንም የሚጠቁም ሊሆን ይገባል።

- ለጀማሪ ወጣቶች ላለፉት ዓመታት ክፍት የተደረገው የነፃ ማስታወቂያ ስራም በዚህ ዓመት ይቀጥላል። በግል ሆነ ተደራጅተው እራስን ሆነ ሀገርን ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ወጣት የቤተሰቡ አባላት ስራቸውን ሆነ አገልግሎታቸው በነፃ ያለምንም ክፍያ ለሌሎች የቤተሰቡ አባላት ማስተዋወቅ ይችላሉ መብታቸውም ጭምር ነው። ነገር ግን በሚሰሩት ስራ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል።

- በጋዜጠኝነት ሞያ ውስጥ ያሉ የቤተሰባችን አባላት እንዲሁም ደራስያን መፅሀፍቶቻቸውን በነፃ ለቤተሰባችን እንዲያስተዋውቁ የተጀመረው ስራ በዚህ ዓመት የሚቀጥል ይሆናል።

#ማሳወቂያ፦ የ "ዕርቅ ሀሳብ አለኝ" በሚል በቲክቫህ አስተባባሪነት የተካሄደው ሀገር አቀፍ በሀገር በቀል ባህላዊ የዕርቅ ስነስርዓት ላይ ባተኮረው ውድድር ላይ የቀረቡ ፅሁፎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደቤተሰቡ ይላካል።

#ማሳሰቢያ ፦ ማስታወቂያን በተመለከተ በቀን እጅግ ውስን ማስታወቂያ ለቤተሰቡ ይላካል ፤ የሚላከው ማስታወቂያ ጠቃሚ እና ህጋዊ ሲሆን ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የሚያስነግሩትም የቤተሰቡ አባላት በመሆናቸው የእርስ በእርስ ተውውቅን ያጎለብታል። በዚህ መሃል ችግር ቢፈጠር በማስታወቂያ ስም ማጭበርበር ቢሰራ ድርጅቱን ከነስሙ የምናጋልጥ ይሆናል። የቤተሰቡ አባላትን ገንዘባቸው እንዲመለስ ይደረጋል። ድርጅቱም ከቤተሰቡ ይቀነሳል።

#ከአጭበርባሪዎች_ተጠንቀቁ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት
- " Tikvah Mart "
- " Tikvah Market "
- " Tikvah Business " በሚሉ አድራሻዎች/ቦታዎች አይሰባሰቡም። በእነዚህ ገፆች የሚተላለፉ ሁሉ ሀሰተኛ መልዕክቶች ናቸው። በማስታወቂያ ስም ገንዘብም እንደሚቀበሉ ደርሰንበታል ፤ ከዚህ በፊትም እንዳልነው ተጠንቅቋቸው። ቻናሎቹንና ግሩፖቹን ለቴሌግራም ሪፖርት አድርጉ ፤ ይህን ስራ ለመስራት የሚጠቀሙበትን የስልክ ቁጥር ካላቸውም ላኩልን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ ምንም አይነት የ #Youtube#TikTok#Facebook አካውንት የለም።

መልዕክት ማስቀመጫ ፦ @tikvahethiopiaBOT

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ📣

" ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው " - የደብረ ማርቆስ ፖሊስ መምሪያ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም ግለሠብ ከፀጥታ ሀይሎች ውጭ ያሉ ግለሠቦች ያለበቂ ምክንያት በከተማ ውስጥ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አሳስቧል።

መሣሪያን በመዝናኛ ቦታዎች ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ያለበቂ ምክንያት ይዞ መንቀሳቀስ የፀጥታ ሀይሉን የሚያዘናጋ እና እኩይ ተግባር ያላቸውን ግለሰቦች ለይቶ ለመቆጣጠር የማያስችል ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የጸጥታ ሀይሉ የህግ ማስከበር ስራውን ለመስራት እንቅፋት እንደሆነበትና የተዝረከረከ የጦር መሣሪያ አያያዝ ለከተማው ህዝብ ደህንነት ስጋት እየሆነ በመምጣቱ በህግ ማስከበር ስራ ላይ ከተሠማራ የጸጥታ ሀይል ውጪ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ በየትኛውም በከተማው ክልል ውስጥ በማንኛውም ሰአት መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይ ፦
- በአልጋ ድርጅቶች እና ሆቴሎች ፣
- በወለል ቤቶች ፣
- በዶርም ፣
- በመኖሪያ ቤት በእንግድነት የሚመጡ ግለሠቦች መሣሪያ ይዘው የመጡበትን ጉዳይ ቅድሚያ ለፖሊስ እውቅና ሳይፈጥሩ እና ፈቃድ ሳያገኙ አገልግሎት ማግኘት የለባቸውም ተብሏል።

የአልጋ ድርጅቶች ፣ ወለል አከራዮች እና የዶርም አከራዮች የተከራዮችን ማንነት እስከ ታጠቁት መሣሪያ ሙሉ አድራሻውን በመመዝገብ በየጊዜው ለፖሊስ ማሳወቅ ይገባቸዋል ተብሏል።

ማህበረሰቡ ከፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ የሚንቀሳቀስ አካላትን በሚመለከትበት ግዜ ፦
0587711232 (3ኛ ፖሊስ ጣቢያ)
0587711669 (1ኛ ፖሊስ ጣቢያ)
0581785658 (2ኛ ፖሊስ ጣቢያ) በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#አዲስአበባ_እና_አካባቢዋ!

በአዲስ አበባና አካባቢዋ በ2014 ዓ.ም በተከሰቱ 511 ድንገተኛ አደጋዎች የ115 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ከ200 በላይ ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

👉 362 የእሳት አደጋ ፤ 149 የጎርፍ፣ የኮንስትራክሽን፣ የወንዝና የኩሬ አደጋዎች ደርሰዋል።

👉 የ115 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በ200 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

👉 ከ115 ሰዎች መካከል 14ቱ በእሳት አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን  ቀሪዎቹ 101 ሰዎች በተለያየ ድንገተኛ አደጋ ነው ሕይወታቸው ያለፈ ነው።

👉 577 ሚሊየን 780 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ፤ በአንጻሩ በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ርብርብ 39 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ድኗል።

👉 የ137 አደጋዎች መንስኤ የታወቀ ሲሆን 63  በኤሌክትሪክ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች ናቸው። አብዛኛዎቹ አደጋዎች ያጋጠሙት በጥንቃቄ ጉድለት ነው።

#ማሳሰቢያ

ሰሞኑን የበዓል ወቅት እንደመሆኑ ከፍተኛ የኃይል አጠቃቀም እንደሚኖር ስለሚኖር ህብረተሰቡ ከምግብ ማብሰል ጋር ተያይዘው ለሚሠሩ ሥራዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ  የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ፤ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት የመለያ ቁጥር (0000039688) የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀምው አሳስቧል።

ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት (NIDO FORTIFIED 400g Full Cream Milk Powder, Batch No. 0000039688) የተባለው ምርት መያዣ ዕቃው (ጣሳው) ላይ የተፃፈው ድብቅ ጽሁፍ (Barcode) ሲነበብ የምርቱ የመጠቀሚያ ጊዜ እ.ኤ.አ 09/2021 የሚል ሲሆን ከምርት መያዣ እቃው (ጣሳው) ላይ የተፃፈው ደግሞ እ.ኤ.አ 01/2024 እንደሆነ ያሳያል፡፡

በመሆኑም በድብቅ ጽሁፉ (Barcode) የሚወጣው የምርቱ ሙሉ መረጃ ላይ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት መሆኑን የሚያሳይ ስለሆነ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የደቄት ወተት የመለያ ቁጥር (0000039688) የሆነውን ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀምው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

(ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ)

የአፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የመንግስትም ሆነ የግል  ቀጣሪ  ድርጅቶች ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመራቂ ሠራተኞቻቸው እና አዲስ ሰራተኞች ከመቅጠራቸው በፊት የተቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃዎች ህጋዊነትና ትክክለኛነት መረጋገጥ ይኖርበታል ብሏል።

ተገልጋዮች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በኩል ይህን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባለሥልጣኑ ከመምጣታቸው በፊት የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት አገልግሎቱን ማግኝት  ይችላሉ ብሏል።

1. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ዲግሪ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

2. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

3. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

4. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በትምህርት ምዘናዎችና ፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት ትክክለኛነቱ  የተረጋገጠ  ከኮፒ  ጋር በማያያዝ ፤

5. ዲግሪውን  ለመማር  በመግቢያነት  የተያዘው  ዲፕሎማ  ከሆነ  ዲፕሎማው  በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የስራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም  የደረጃ  4  ብቃት  ማረጋገጫ(COC) ካገኙበት ማዕከል የተረጋገጠ መሆን አለበት  ከኮፒ  ጋር በማያያዝ እና

6. የስም ለውጥ ካለ የፍርድቤት ውሳኔ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ናቸው፡፡

የማስተርስ ዲግሪ ለማረጋገጥ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለጸው መንገድ መረጋገጥ ሲል ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳስቧል።

#ETA

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

የተከሰተው ጉንፋን መሰል በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት ባህሪ ስላለው በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ሲል የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አሳስቧል።

ቢሮው ምን አለ ?

- በከተማው በተለይ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በብዙ ሰዎች ላይ ጉንፋን መሰል በሽታ ተከስቷል።

- ይህ ወቅታዊና በየዓመቱ ከቅዝቃዜ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሲሆን፤ በወረርሽኝ መልክ የሚገለጽ አይደለም።

- የተከሰተውን የቫይረስ አይነት ለመለየት ከትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት እንዲሁም ከፍተኛ መተላለፊያ በሆኑ ቦታዎች ላይ ከሚገኙ ከ178 ሰዎች ናሙና ተወስዶ ምርመራ ተደርጓል። በዚህም 17 በመቶ በላይ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ እና 3 በመቶ የሚሆነው ከኮቪድ-19 ቫይረስ ጋር የተገናኘ መሆኑ ተረጋግጧል።

- ይህ ህመም በተለይም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ላይ የሚከሰት ሲሆን፤ ከመቶ ሰዎች መካከል ሃያ የሚሆኑት ላይ ይስተዋላል።

ምልክቶቹ ፦

° ከፍተኛ ራስ ምታት፣
° ሳል፣
° ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣
° ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣
° ጡንቻ አካባቢ ህመም፣
° የድካም እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸው።

- ምልክቶቹ ሲታዩ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ እራስን ከከባድ ህመም መከላከል ያስፈልጋል።

- በበሽታው የተያዙ ሰዎች አፋቸውን እና አፍንጫቸውን ሳይሸፍኑ ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ እንዲሁም ቫይረሱ ያረፈባቸውን ነገሮች ከነኩ በኋላ አፍን፣ አፍንጫ ወይም ዓይንን መንካት ቫይረሱ እንዲሰራጭ የሚያደርጉ መንገዶች ናቸው።

የመከለከያ መንገዶች ምንድናቸው ?

ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ፣

በሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን መክፈት፣

የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ

በንክኪ ወቅት እጅን በመታጠብ በሽታውን በቀላሉ መከላከል ይቻላል።

* በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት ባህሪ ስላለው በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል።

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ምንድነው ?

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ህክምናው ከቤት የሚጀምር ሲሆን ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፦
በቂ እረፍት መውሰድ፣
ፈሳሽና ትኩስ ነገሮች መጠቀም
በአካባቢው በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር ማድረግ ከዚህ በተጨማሪ ተገቢውን ህክምና በማግኘት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ማድረግ ይገባል።

#ማሳሰቢያ ፦ በሽታው ከአንድ ሳምንት በላይ የሚቆይ ከሆነ በአቅራቢያው ወደሚገኝ የህክናምና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን አገልግሎትና የጤና ባለሙያዎች ምክረ ሃሳቦች ማግኘት ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia