TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦነግ(ABO)፣ አግ 7...⬇️

በሀገሪቱ የሚገኙ 7 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰሞኑን በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱ #ግጭቶችን አወገዙ።

የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ አሁን ላይ በሀገሪቱ በተለይም በአዲስ አበባ እየታየ ያለው ወቅታዊ ግጭት ላይ መስከረም 6 እና 7 ውይይት ካደረጉ በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የጋራ #መግለጫ ሰጥተዋል።

የጋራ መግለጫውን የሰጡት የፖለቲካ ፓርቲወችም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ)፣ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ዴሞራሞክራቲክ ግንባር፣ የኦሮሞ አንድነት ለነጻነት፣ የኦሮሞ አንድነት ግንባር፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንደነትና
ዴሞክራሲ ንቅናቄ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ ባለፉት 2 ቀናት ባደረጉት #ግምገማ መሰረትም ግጭቱ አሳሳቢና አሳዛኝ መሆኑን ነው በጋራ መግለጫቸው ያመለከቱት።

በዚህም በሰዎች ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በጽኑ ማውገዛቸውን ነው በጋራ መግለጫቸው ያስታወቁት።

የግጭቱ #ተዋናያን እና ከጀርባ ሆነው ግጭቱን የሚያስተባበሩ የውጭና የሀገር ውስጥ ሃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲቆጠቡም በጋራ መግለጫቸው አሳስበዋል።

#ወጣቱም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በራሱ መስዋትነት የመጣውን ሃይል #ለመቀልበስ ከሚሰሩ ሀይሎች ጎን #እንዳይሰለፍም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ የመምራት ሃለፊነት የተጣለባቸው የመንግስት አካላትም የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲሉ እንዲህ ዓይነቱ ግጭት #ከመከሰቱ በፊት የመከላከል እርምጃ እንዲወስዱ እና ወንጀለኞችን #በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።

አሁን ላይ በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት ለማራመድ የሚያስችል ሰላም መስፈኑና ለዘመናት የታገሉለትና ሁሉንም ለማስተናገድ የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳር መፈጠሩንም አስረድተዋል።

ስለሆነም ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል የዴሞክራሲ ባህልን በጋራ ማዳበሩ ጠቃሚ መሆኑ ነው በመግለጫው የተመላከተው።

ልዩነቶችን በሃይል ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች ለማንኛውም አካል ጠቃሚ ያለመሆኑን በመግለጫቸው ያመላከቱት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ፥ ሀገሪቱን የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የአንድነት ተምሳሌት ለማድረግ መስራት እንደሚገባም በመግለጫው ጠቁመዋል።

ለሰላም፣ ዴሞክራሲና ለህዝቦች አንድነት መጠናከር የበኩላቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

ለዚህም ለፖለቲካ ፓርቲ አባሎቻቸው፣ ደጋፊዎቻቸውና ለመላው ህዝብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ‼️

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱ አካላትን #ለሕግ እንደሚያቀርብ ገለጸ።

ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ባወጣው መግለጫ ከመረራና እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ የተገኘውን ለውጥ #ለመቀልበስ ስልጣንን ያለአግባብ ተጠቅመው ዘረፋ ሲያካሄዱ የነበሩና አሁን ጥቅሙ የቀረባቸው አካላት በተለያዩ ቦታዎች እሳትን በማቀጣጠልና የሰው ልጆች ላይ መፈፀም የሌለበት ወንጀል እንዲፈጸም፣ ዜጎች እንዲፈናቀሉና የክልላችን ሰላም እንዲናጋ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የእነዚህ አካላት ሴራ እነሱን በመቅበር የሚጠናቀቅ ይሆናል እንጂ ኦሮሚያን የግጭት ሜዳ ማድረግ አይሳካላቸውም ብሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡

እነዚህ አካላት የተጀመረው የህግ የባላይነትን የማስከበር ስራ እንዲስተጓጎል ሌተ ቀን እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፡፡

የኦሮሞን የህዝብ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን እርስ በእርስ በማጋጨት የጥፋት እጃቸውን እንደዘረጉ መግለጫው ያትታል፡፡

እንደ ፓርቲው መግለጫ፣ እነዚህ አካላት በቅርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የሱማሌ ወሰን አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ #የግድያ_እርምጃ ወስደዋል፣ ሰላማዊ ዜጎችንም አፈናቅለዋል፣ የተቀናጀ ጦርነት በመክፈትም በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ይላል መግለጫው፡፡

በዚህ በሰላማዊ ዜጎችና በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ለደረሰው አሰቃቂ ወንጀል ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው ገልጿል፡፡

ድርጊቱ በሌቦች፣ ዘራፊዎችና በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ላይ መውሰድ ከጀመርነው ሕጋዊ እርምጃ ወደ ኋላ እንደማይመልስ ተገልጿል፡፡

በህዝባችን ላይ ይህንን ጉዳት ያደረሱ አካላት የገቡበት ጉድጓድ ገብተን ለሕግ እናቀርባቸዋለን፤ እንዲሁም እነዚህ አካላት ያላቸውን ኃይል በድጋሚ በማይጠገን መልኩ ሰብረን እንቀብረዋለን ብሏል የፓርቲ መዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው፡፡
ማንኛውም የሰበአዊ ጥሰት የፈፀሙ አካላት በሕግ የሚጠየቁ መሆኑን የማዕከላዊ ኮሚቴው መግለጫ ያስረዳል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia