TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባህር_ዳር

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የተገደሉባት #ዘንዘልማ 'ከገስት ሀውሱ' በ6 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኝ 'ሳተላይት' ከተማ ናት። በከተማዋ የግብርና ኮሌጅ የሚገኝ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ በአብዛኛው ጫት በማምረት የሚተዳደሩ ናቸው። አካባቢውም በጫት ማሳ የተሸፈነ ነው። በከተማው ምዕራባዊ ዳርቻ የኢ.መ.ሠ ምዕራብ ዕዝ ዋና መስሪያቤትና የኢ.አ.ሀ ሰሜን ምድብ ዋና ጣቢያን ጨምሮ የወታደርና የፌ. ፖሊስ ካምፖች የሚገኙ ሲሆን፣ ቃል አቀባይ ንጉሱ ጥላሁን እንዳሉት በክልሉ ም/ፕሬዝደንት ግብዣ ወደ ከተማው እንዲገቡ ሆኗል። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ባለፈው ቅዳሜ ጥቃት ከደረሰባቸው ተቋማት መካከል የአዴፓ ጽህፈት ቤት፣ የክልሉ ምክርቤት እና የአማራ መገናኛ ብዙሐን ኤጀንሲ የሚገኙበት ሲሆን፣ "መፈንቅለ መንግስት" ሞካሪ የተባሉ ሀይሎች የአዴፓን ጽህፈት ቤት መቆጣጠር ችለው ነበር።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ትዕግስታችን አልቋል" ዶ/ር አብይ

"በደቡብ ክልል የቀረበውን የክልል እንሁን ጥያቄ ተቀብለን እየተከታተልን ነው። ምላሹ ለመስጠት ጊዜ ይፈልጋል። ነገር ግን በጩኸት የሚሆን ነገር የለም። ሁሉም ከኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ጉዳይ ጋር ይያያዛል። ይህን የማይቀበል አካል ካለ ግን መንግስት ትእግስቱ ስላለቀ በህጋዊ መንገድ #እናስከብራለን።" ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ

#elu
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እግዚአብሄር በናንተ ላይ ይፍረድ"

ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ በአውሮፓና በአሜሪካ ሀገር እየኖሩ፣ #ኢትዮጵያውያንን ለማባላት የበሬ ወለደ መረጃ ያሰረጫሉ ያሏቸውን ግለሰቦች በፓርላማ ፊት እረግመዋል።

#elu
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የሚቃጡ አካላት ካሉ ብዕራችንን አስቀምጠን ጠብመንጃችንን እናነሳለን"

ጠ/ሚንስትር ዐብይ አህመድ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዛሬም በኢትዮዽያ አንድነት እንደማይደራደሩ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት በተደጋጋሚ ተናግረዋል። #elu

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ላለፉት 2 ቀናት ዝግ ሆኖ የቆየው አዲስ አበባ ከተማን ከባህርዳር ከተማ የሚያገናኘው መንገድ ዛሬ ተከፍቷል።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታግቶ የነበረ የ14 ዓመት ታዳጊ ተገደለ...

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጭልጋ ቁጥር አንድ ወረዳ ከቀናት በፊት ታግቶ የነበረ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ በአጋቾቹ ተገደለ። ታዳጊው ታህሳስ 27 ቀን ከአይከል ከተማ በታጣቂዎች የተወሰደ ሲሆን፣ ለማስለቀቂያ 100 ሺህ ብር ተጠይቆበት ነበር።

በሌላ መረጃ..

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የመከላከያ ሰራዊት ልብስ በመልበስ ኬላ ዘግተው ሲፈትሹ በነበሩ ታጣቂዎች አማካኝነት፣ አንድ አሽከርካሪን ጨምሮ 6 ሰዎች ታግተው መወሰዳቸው ተነግሯል። በተጨማሪ ዕገታው የተፈጸመው ከ4 ቀን በፊት እንደሆነና፣ አጋቾቹ በሰው ከ150ሺህ - 250ሺህ ብር እንደጠየቁም ተሰምቷል።

#ELU
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ለም ተዘጋ?

- ዛሬ ኢትዮዽያን ከሱዳን የሚያገናኘው ዋና መንገድ ዛሬ ከቀት በኅላ በመተማ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተዘግቶ ነበር የዋለው።

- መንገዱ የተዘጋው በትናንትናው ዕለት "የሱዳን ወታደሮች/ታጣቂዎች" በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶችን ዘርፈው ወስደዋል ከተባለ በኅላ ነው።

- መንገዱ ማምሻው የተከፈተ ሲሆን መንገዱ የተከፈተው የሱዳን ወታደሮች እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መሪዎች ከተወያዩ በኅላ ነው። የተዘረፉ ከብቶች ነገ እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

#ELU
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የብሮድካስት ባለስልጣን ማስጠንቀቂያ...

የብሮድካስት ባለሥልጣን በኢኦተ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ማስጠንቂያ ሰጠ። ባለስልጣኑ ጣቢያው በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና፣ በተመጣጣኝ ስፋት እና በተመሣሣይ የሥርጭት ሰዓት የቤተክርስቲያኗን ቅሬታ እንዲያስተላልፍም አዟል።

ባለስልጣኑ ውሳኔውን ያስተለፈው፣ ኃሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በፍቸና በገብረ ጉራቻ ከተሞች ባዘጋጃቸው መድረኮች የተናገሩትን ንግግር ጣቢያው ማስተላለፉን ተከትሎ ነው።

ደብዳቤውን ከላይ ተመልከቱ!

#EotcTV #ELU
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia