TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አርፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የቅዱስነታቸውን ሽኝት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ተሰብስቦ በሚያስተላልፈው ውሳኔና በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል። አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ…
#Russia

ሩስያ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማትን ሀዘን ገለፀች።

ሩስያ በአዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ አማካኝነት በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማትን ሀዘን ገልፃለች።

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት በዓለም ለሚገኙ የኦርቶዶክስ አማኞች ከባድ ሐዘን ነው ብላለች።

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ታላቅነት ማስቀጠልና መጠበቅ ውስጥ የማይተካ ሚና መጫወታቸውንም ሩስያ ገልፃለች።

ሩስያ በብፁዕነታቸው እረፍት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነን እናዝናለን ብላለች።

@tikvahethiopia
#Russia

ሩስያ በሀገሯ ፣ በኩባንያዎችና በህዝቧ ላይ " ወዳጃዊ ያልሆኑ " ድርጊቶችን የፈፀሙና እርምጃ የወሰዱ / ወዳጅ ያልሆኑ ሀገራትን እና ግዛቶችን ዝርዝር በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጋለች።

እነዚህም ፦

🇺🇦 ዩክሬን
🇺🇸 አሜሪካ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇪🇺 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት
🇦🇺 አውስትራሊያ
🇨🇦 ካናዳ
🇮🇸 አይስላንድ
🇯🇵 ጃፓን
🇲🇨 ሞናኮ
🇲🇪 ሞንቴኔግሮ
🇳🇿 ኒውዚላንድ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇹🇼 ታይዋን (ቻይና እንደ ተገንጣይ ግዛቷ የምትቆጥራት ሲሆን እሷ ግን ነፃ እና ሉዓላዊ ሀገር ነኝ በሚል እራሷን ችላ ነው የምትተዳደረው)
🇸🇲 ሳን ማሪኖ
🇸🇬 ሲንጋፖር
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇨🇭 ስዊዘርላንድ
🇦🇱 አልባንያ
🇦🇩 አንዶራ
🇱🇮 ሌይቼንስቴይን
🇫🇲 ማክሮኔዢያ
🇲🇰 ሰሜን ሜቄዶንያ ናቸው።

ከላይ የተጠቀሱት ሀገራት እንዲሁም ግዛቶች በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ጥለዋል ወይም በሚጣለው ማዕቀብ ላይ ተቀላቅለዋል የተባሉ ናቸው።

@tikvahethiopia
#Russia #Poland #Germany

አዲስ አበባ ያለው የሩስያ ኤምባሲ ያሰራጨው መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል፤ በኤምባሲዎች መካከልም ውዝግብ ፈጥሯል።

የሩስያ ኤምባሲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጿል።

ይህ መልዕክት እየደረሰው ያለው ከገፁ ተከታዮች መሆኑን አመልክቷል።

ኤምባሲው " ሀገሮቻችን በችግር ጊዜ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንደዚህ አይነት ጠንካራ ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፣ ወዳጃዊ ግንኙነት ስላላቸው ኩራት ይሰማናል " ብሏል።

አክሎም " ልክ አያቶቻችን ከ80 ዓመታት በፊት እንዳደረጉት ናዚዝምን እየተዋጋን ባለንበት በአሁን ጊዜ ያሳያችሁን ድጋፍ እና ከሩስያ ጎን ለመቆም ስለመረጣችሁ በእጅጉ እናደንቃለን " ብሏል።

የሩስያ ኤምባሲ ይህንን መልዕክት ካሰራጨ በኃላ የሌሎች ሀገራት ኤምባሲዎች ምላሽ ሰጥተዋል ፤ ምላሽ ከሰጡት መካከል የፖለንድ ኤምባሲ አንዱ ነው።

ፖላንድ ኤምባሲ ፤ ሩስያ የሀሰተኛ መረጃ እያሰራጨች ነው ሲል ወቅሷል።

ኤምባሲው " የናዚ መስፋፋት የጀመረው በ1939 በፖላንድ ላይ በተደረገ ሕገ-ወጥ ወረራ ነው ፤ በወቅቱም ሞስኮ እንደ አጋር ነበረች ብሏል።

" ሩስያ በዩክሬን ላይ ከፈፀመችው ህገ-ወጥ የሆነ ጥቃት ጋር በተያያዘ ፤ ማን ከናዚዎች ጋር መነፃፀር እንዳለበት ሁለት ጊዜ ማሰብ ይገባል " ሲል ኤምባሲው ገልጿል።

ሌላው ለሩስያ ኤምባሲ ምላሽ የሰጠው የጀርመን ኤምባሲ ሲሆን ኤምባሲው በጉዳዩ ዙሪያ ዝም ሊል እንደማችል ገልጿል።

" ናዚዝም " ን እንዋጋለን በሚል ሉዓላዊ ሀገርን መውረር ፣ ሰላማዊ ዜጎችን እና ሆስፒታሎችን ማፈንዳት (ልክ ትላንት በማሪፖል በሚገኘው የእናቶች እና ህፃናት ሆስፒታል እንደተደረገው) የሚያሳዝን እና የሀሰተኛ መረጃ ማሳያ ነው ብሏል።

ይህ ጦርነት " ናዚዝም " ን ለመዋጋት እንዳልሆነ ይታወቃል ያለው የጀርመን ኤምባሲ ጦርነቱ ለአምባገነን ስርአቶች ትልቁ ፈተና እና ስጋት የሆነውን ዲሞክራሲን፣ የፕሬስ ነፃነትን እና የህዝብ ድምጽን መዋጋት ነው ብሏል።

ኤምባሲው ፤ " የሩሲያ ታንኮች ሰላም ፣ ውሃ ወይም ምግብ አያመጡም ፤ መከራ እና ጥፋት ብቻ ነው የሚያመጡት " ብሏል።

@tikvahethiopia
#Russia

የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ።

ፑቲን ፤ " ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ " ካሉ በኋላ፤ " እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን " ብለዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ ጦር ጎን መሰለፍ የሚፈልጉ 16 ሺህ ሰዎች አሉ ሲሉ ለፑቲን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለፀጥታ ምክር ቤታቸው ምዕራባውያን " በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመተላለፍ ተዋጊዎችን ለዩክሬን እየቀጠሩ ነው " ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም ዩክሬን በ "አፍሪካ" በተለያዩ ሀገራት በሚገኙት ኤምባሲዎቿ በኩል በ #ቅጥር ለዩክሬን የሚዋጉ ሰዎችን እንደምትፈልግ ማስታወቋ በኃላ ይህ ጥሪው ቁጣን ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Russia

ሩስያ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ስንዴ፣ በቆሎ፣ አጃ፣ እና ስኳር ወደ ውጭ እንዳይላክ አገደች።

ሩስያ እህል ለቀድሞ የሶቪየት ሀገራት እንዳይላክ እና በአብዛኛው የስኳር ምርት ወደሌሎች ሀገራት እንዳይላክ ለጊዜው ማገዷ ተሰምቷል።

እገዳው እኤአ እስከ ሰኔ 30 ይቆያል ተብሏል።

ነገር ግን በልዩ የኤክስፖርት ፈቃድ አሁን ባለው የኮታ ሥርዓት ለነጋዴዎች መከፋፈሉ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ሩስያ እህል እና ስኳር እንዳይላክ ለጊዜው ማገዷ መሰማቱን ተከትሎ ከወዲሁ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ መሆኑ ተነግሯል።

ሩስያ በዓለማች ላይ ከፍተኛ እህል ላኪ ሀገር ስትሆን ቱርክ እና ግብፅ ደግሞ ከሩስያ በመግዛት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

@tikvahethiopia
#RUSSIA #USA

ሩስያ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት #ጆ_ባይደንን ጨምሮ ሌሎች የአሁን እና የቀድሞ ባለስልጣናት ወደ ሀገሬ ድርሽ እንዳትሉ ስትል ማዕቀብ ጣለች።

የሩሲያ መንግስት ወደ ሩስያ እንዳይገቡ እገዳ ከጣለባቸው መካከል ፦

👉 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

👉 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን

👉 የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን

👉 የCIA ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ

👉 የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጀን ሳኪ፣

👉 የመከላከያ ሚኒስትር ሊዮይድ አውስቲን

👉 የቀድሞዋ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ይገኙበታል።

በተጨማሪ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

ቀደም ሲል አሜሪካ በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ላይ ማዕቀብ ጥላ ነበር።

መረጃው የአርቲ ኒውስ እና የአልዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#Ukraine #Russia

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያ ጋር ውጤት የሚያስገኝ የሰላም ንግግር በአስቸኳይ ማድረግ እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ ለሕዝባቸው ባስተላለፉት የቪድዮ መልዕክት በግዛታቸው ውስጥ ግዙፍ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ካለችው ሩሲያ ጋር " ካለምንም መዘግየት ትርጉም ያለው " የሰላምና የደኅንት ንግግር እንዲጀመር ጠይቀዋል።

ይህ ሩሲያ በአገራቸው ላይ በከፈተችው ወረራ በፈጸመችው "ስህተት" የሚደርስባትን ጉዳት ለመቀነስ ያላት ብቸኛው እድል ነው ሲሉ ዜሌንስኪ ተናግረዋል።

" ለመገናኘት፣ ለመነጋገርና የዩክሬንን የግዛት አንድነት እንዲሁም ፍትህን ወደነበረበት ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው " ሲሉ ዜሌነስኪ ለሩሲያ ጥሪ አቅርበዋል።

" ይህ ካልሆነ ግን ሩሲያ ከሚገጥማት ውድቀት ለመውጣት በርካታ ትውልዶችን መጠበቅ ሊያስፈልጋት ይችላል " ማለታቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሀሙስ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት አገራቸው ጦርነቱን ለማቆም ከዚህ በፊት ይፋ አድርጋው የነበረውን ቅድመ ሁኔታዎች በድጋሚ ገልፀዋል።

ዋነኞቹ ቅድመ ሁኔታዎች ፦

- ዩክሬን NATOን እንደማትቀላቀል ማረጋገጥ።

- ዩክሬን ትጥቅ እንድትፈታ፣

- በዩክሬን የሩሲያ ቋንቋ እንዲከበር እና የናዚ አመለካከት አራማጅ ናቸው የተባሉ ኃይሎችን ዩክሬን እንድትቆጣጠር፣

- ክራይሚያ የሩሲያ ግዛት መሆኗን፣ በቅርቡ ነጻነታቸውን ላወጁት ምሥራቃዊ የዩክሬን ግዛቶች ደግሞ እውቅና እንድትሰጥ ዋነኞቹ የሩሲያ ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ukraine #Russia

ሩሲያ የዩክሬንን የአየር ክልል ለመዝጋት ከሚሞክር ኃይል ጋር ጦርነት እንደምትከፍት ገለፀች።

ሀገሪቱ ይህን የገለፀችው በዩክሬን እያካሄድኩ ነው ያለችውን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” የመጀመሪያውን ምዕራፍ ማጠናቀቋን ባሳወቀችበት ወቅት ነው።

ሀገሪቱ ተጠናቋል ባለችው የመጀመሪያ ምዕራፍ ያስቀመጠችው ግቦች እንደተሳኩ የገለጸች ሲሆን ብዙ የዩክሬን ግዛቶችን መቆጣጠሯን አሳውቃለች።

ሩስያ ጦሯ የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪቭን ጨምሮ ካርኪቭ፣ ቼርኒሂቭመ ሱሚ እና ሚኮላይቭ የተባሉ አካባቢዎችን መክበቡን ገልፃለች። በተጨማሪ ኬርሶን እና ዛፖሮዚ የተባሉ የዩክሬን ግዛቶች አሁን ላይ በእጇ ላይ መውደቁን አሳውቃለች።

በዩክሬን የተገንጣዮች ግዛት የሆነችውን ሉሃንስክን ደግሞ 93 በመቶ መቆጣጠሯን አሳውቃለች።

የዩክሬንን የአየር ክልል ለመዝጋት ከሚሞክር ኃይል ጋር ጦርነት እንደምትከፍትም ዝታለች።

4 ሳምንታት ባስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች ሲያልቁ ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ተሰደዋል።

መረጃው የአልዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#Ukraine #Russia

የሩስያን ድንበር ጥሰው ገቡ የተባሉ ሁለት የዩክሬን ጦር ሂሊኮፕተሮች የነዳጅ ማከማቻ ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ተሰማ።

ሁለት የዩክሬን ሄሊኮፕተሮች የሩሲያን ድንበር ጥሰው በሀገሪቱ ምዕራባዊ ከተማ ቤልጎሮድ የነዳጅ ማከማቻ ቦታ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የአከባቢው አስተዳዳር ዛሬ አስታውቋል።

የአካባቢው አስተዳዳሪ የሆኑት ቫያቼስላቭ ግላድኮቭ በቴሌግራም ቻናላቸው ላይ ሁለት የዩክሬን ጦር ሄሊኮፕተሮች በፈፀሙት የአየር ጥቃት በሚያስተዳድሩት አካባቢ ባለ የነዳጅ ማከማቻ ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ጽፈዋል።

በቃጠሎው ምክንያት በነዳጅ ማከማቻው ውስጥ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች መቁሰላቸው ተገልጿል።

የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አብስቶ ሩስያ ፤ ዩክሬን ድንበሯን አልፋ ጥቃት ፈፀመችብኝ ብላ ሪፖርት ስታደርግ ይህ የመጀመሪያ ነው።

የ2ቱ ሀገራት ጦርነት እስካሁን ድረስ ይህን ነው የሚባል መፍትሄ ሳይገኝለት ከወር በላይ ተቆጥሯል።

አሁንም ጦርነቱ እንዲቆም ለማድረግ ንግግሮች ቢኖሩም ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ግጭት እንዲቀጥል የሚያደርጉ ወታደራዊ ሁኔታዎች እንደሚስተዋሉ እየተነገረ ነው።

በሀገራቱ ጦርነት ምክንያት ከሚጠፋው የሰው ህይወት ፣ ከሚሰደደው ሰው ባለፈ በዓለም ኢኮኖሚ እና በሀገራት የኑሮ ውድነት ላይ በየዕለቱ እያሳደረ ያለው ግልፅ ተፅእኖ እየከፋ ነው።

@tikvahethiopia
#Russia

ሩስያ ወደ ውጭ በሚላክ ስንዴ፣ በቆሎ እና ገብስ ላይ የታክስ ጭማሪ አደረገች።

የሩሲያ መንግስት ወደ ውጭ በሚላከው ስንዴ ፣ በቆሎ እና ገብስ ላይ የታክስ ጭማሪ ማደረጉን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ፤ ከሀገሪቱ ወደ ውጭ በሚላክ ስንዴ ላይ የተደረገው የታክስ ጭማሪ በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት አንድ ቶን ስንዴ ወደ ውጭ ሲላክ 101 ነጥብ 4 ዶላር እንዲከፈል መንግስት ወስኗል።

በተጨማሪም ወደ ውጭ ሀገራት የሚላኩ የበቆሎ እና ገብስ ምርት ላይ በተደረገድ የታክስ ጭማሪ አንድ ቶን በቆሎ ወደ ውጭ ሲላክ የሚከፈለው ታክስ 70 ነጥብ 6 እንዲሂም አንድ ቶን ገብስ ወደ ውጭ ሲላክ 75 ነጥብ 4 ዶላር እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል።

በስንዴ፣ ገብስና በቆሎ ላይ የተደረገው የታክስ ጭማሪ በምርቶቹም ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያመጣ አመላካች ነውም ተብሏል።

በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ በስንዴ ምርት ላይ ከፍተኛ እጥረት አሊያም የዋጋ ጭማሪ ሊከሰት እንደሚችል ፍርሃቶች መኖራቸው እየተገለፀ መሆኑን አል ዓይን ኒውስ (Al AIN) ዘግቧል።

@tikvahethiopia