TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoH

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 1 ሺህ 311 የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

በነገው ዕለት የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕሙማን ደህንነት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን ተከታዩን ብለዋል ፦

- ኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሥራ ግንባር ቀደም የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ላይ መጠነ ሰፊ ችግር አስከትሏል።

- 1 ሺህ 311 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 700 የሚሆኑት ደግሞ አገግመው ወጥተዋል፤ ቀሪዎቹ በህክምና ተቋማት ይገኛሉ።

- ሁለት የሕክምና ባለሙያዎችም ለሞት ተዳርገዋል።

- ነገ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቱ የሚከበረው የሕሙማን ቀን ቫይረሱ የተገኘባቸው ወገኖቻቸውን ሌት ተቀን እያገለገሉ ላሉ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ክብርና ምስጋናን በመስጠት ይከበራል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ።

የጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ክትባቱን የወሰዱት በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በመቐለ ጠቅላላ ሆስፒታል ተገኝተው የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት ነው።

ዶ/ር ሊያ ፥ በመላው ሀገሪቱ ለኮሮና ቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው ከፍ ያሉ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን በቀዳሚነት ያገኛሉ ብለዋል፡፡

የክትባቱ አቅርቦት በአለም አቀፍ ደረጃ ውስንነት ስላለው እና ሁሉንም የህብረተስብ ክፍሎች ማዳረስ የማይቻል በመሆኑ ህብረተሰቡ ክትባት መጣ ብሎ መዘናጋት እንደሌለበት እና ቫይረሱን መከላከያ መንግደ በአግባቡ እንዲተገብር አሳስበዋል።

#MoH
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ፦ የብቃት ምዘና ፈተናው ከመጋቢት 20-24/2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የፈተና ፕሮግራሙ ፦ • ነርሲንግ - 20/07/2013 ዓ.ም • ጤና መኮንን - 21/07/2013 ዓ.ም • ህክምና እና ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ - 22/07/2013 ዓ.ም • ፋርማሲ እና አንስቴዥያ - 23/07/2013 ዓ.ም • ሚድዋይፈሪ - 24/07/2013 ዓ.ም * የብቃት…
#Update

ዛሬ የጤና ሚኒስቴር የብቃት ምዘና ፈተና መስጠት ጀምሯል።

በህክምና ፣ ነርሲግ ፣ ጤና መኮንን ፣ አኒስቴዥያ ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጅ ፣ ፋርማሲ እና ሚድዋይፈሪ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ ባለሙያዎች ከመጋቢት 20 እስከ 24/07/2013 ዓ.ም ድረስ የብቃት ምዘና ፈተና መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ፈተናው በመላው ሀገሪቱ በተዘጋጀ 38 የፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ ነው።

የፈተና አሰጣጥ ስርአቱን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ እና የሀገር አቀፋ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ከመፈተኛ ጣቢያዎች አንዱ በሆነው የቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ሜ/ ኮሌጅ በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡

የብቃት ምዘና ፈተናውን የሚወስዱት 18,926 ተመዛኞች ሲሆኑ የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት መስጠት ከመጀመራቸው በፊት ብቃታቸውንና ክሎታቸውን ለመመዘን የሚሰጥ ፈተና ነው። #MoH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SinopharmCovid19Vaccine

የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ያበረከተው "ሲኖፋም" የተባለ 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ ገባ።

ክትባቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢውሃን አስረክበዋል። #MoH

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
አጭር መረጃ ስለኮቪድ-19 ኢትዮጵያ መተግበሪያ፦

የኮቪድ ኢትዮጵያ መተግበሪያ በውስጡ ስለኮቪድ ቁጥጥር ፣ ህክምና እና መከላከል ማወቅ ያለብንን በ7 ኮርሶች የያዘ ሲሆን ስልጠናው ፦

- የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶቦት በቤት ውስጥ እራሳችንን ለይተን ለራሳችን ማድርግ ስለሚገባን እንክብካቤ እና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ ያሳውቃል።

- ስለኮቪድ-19 ክትባት ለማወቅ እና ስልጠና ለመውሰድ ይጠቅማል።

- ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር ሰራተኞች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ለማውቅ ይረዳል።

- ሰልጣኞች ስልጠና እንዳጠናቀቁ በሚመዘገቡበት የስልክ ቁጥር ባላቸው የቴሌግራም አድራሻ ስልጠናውን በአግባቡ ላጠናቀቁ እና የስልጠና መመዝኛውን ከ80 በመቶ በላይ ላስመዘግቡ በጤና ሚኒስቴር የተረጋገጠ የተከታታይ ሙያ ማጎልብቻ ነጥብ ያለው ሰርተፍኬት የሚላክላቸው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በየ3 አመት ለሚደረገው የሙያ ፍቃድ እድሳት ነጥብ ለመጠቀም ያስችላል።

- መተግበሪያውን በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከጫኑና ስልጠናዎች ካወረዱ በኋላ ኢንተርኔት የማይፍልግ ሲሆን ስልጠናውን የሚስብ እና ለመረዳት ቀላል ለማድረግ ቪድዮዎች ተካተውብታል።

- ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የኮቪድ ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንዲሁም የተሻለ እንክብካቤ ለመስጠት ይረዳል።

መተግበሪያውን ከየት ላግኘው ?

መተግበሪያውን በስልክዎ ለመጫንና ስልጠናውን ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ - https://bit.ly/3apv5J2

#MoH #EPHI

@tikvagethiopia @tikvagethiopiaBOT
#MoH

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ላይ ያለውን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል አጋር ድርጅቶች እገዛቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ከአጋር ድርጅቶች ተወካዮች ጋር የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ያለውን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ በተመለከተ ትላንት ውይይት አደርገዋል።

ውይይቱን የመሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ አጋር ድርጅቶች እየሰጡ ላለው ሰብዓዊ እርዳታ አመስግነው የፀጥታ ችግር ባለባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የጤና አገልግሎት በመጓደሉ የእናቶች እንዲሁም ህፃናት ጤና ችግር ላይ መውደቁን ፣ የውሃ እጥረት በመኖሩም ኮቪድና ኮሌራን ጨምሮ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊጋለጡ እንደሚችሉ ጠቁመው ችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን ዳይሬክተር ዶክተር አለኝታ ገ/የሱስ የጤና ተቋማትና አምቡላንሶች ያሉበትን ሁኔታ የገለፁ ሲሆን ፥ በግጭት አካባቢዎች አብዛኞቹ ተቋማትና አምቡላንሶች አገልግሎት እየሰጡ አለመሆናቸውን፤ አገልግሎት የሚሰጡትም ያሉባቸውን ዕጥረቶች በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች በየአካባቢዎች እያደረጉ ያሉትን አስተዋፅኦ አብራርተው በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

Via MoH Ethiopia

@tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

" ...እየሞቱ ያሉ ሰዎች መሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ክትባት ያልወሰዱ ናቸዉ"- ዶ/ር ሊያ ታደሰ

ዛሬ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅታዊነት እና ክትባት እዲሁም በመጪው ቀናት የሚከፈቱ ት/ቤቶች ማድረግ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ዙርያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ሊያ በመግለጫቸው፦
-አደገኛው የዴልታ ዝርያ መኖሩ
-በየቦታው መሰባሰቦች እና ማስክ አለማድረግ በመበራከቱ
-ደንቦች ተግባራዊነታቸው መቀዛቀዝ ምክንያት በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን መከታታያ ክፍል የሚገቡና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

በወረርሽኙ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ቁጥር 6000 እየተጠጋ እንደሆነ ገልፀው፤ ባለፈው ሳምንት ብቻ 308 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው እንዳጡ ይህም ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ትልቅ የሞት አሃዝ ሆኖ እንደተመዘገበ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በየቀኑ በአማካይ ከ1 ሺ ሰዎች በላይ በቫይረሱ ይያዛሉ በዚህ ሳምንትም በየቀኑ በአማካይ 44 ወገኖቻችን እየሞቱ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ ያለተከተቡ ሰዎች ለበሽታው ከፍተኛ ታጋላጭ እንደሆኑ የCDC ጥናትን መነሻ አድረገው የተናገሩ ሲሆን በዚህም በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው ከ4.5 እጥፍ በላይ ነው፣ሆስፒታል የመግባት እድላቸው ከ10 እጥፍ በላይ፣ ታመው የመሞት እድላቸው፣ ከ11 እጥፍ በላይ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ዶ/ር ሊያ ታደሰ፥ በአሁን ሰዓት ሀገራችን እየሞቱ ያሉት ሰዎች መሉ በሙሉ ሊባል በሚቻል ደረጃ ክትባቱን ያልወሰዱ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ከሰኔ ወር አጋማሽ እሰከ ነሀሴ ወር አጋማሽ በኮቪድ19 ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የመጀመርያ ክትባት የወሰደ የሚገኝበት ሲሆን የተቀሩት ግን ያልተከተቡ ናቸው ብለዋል ሚኒስትሯ።

#MoH

@tikvahethiopia
#MoH

የጤና ባለሞያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 27 ድረስ ይሰጣል።

በህክምና ፣ ነርሲንግ ፣ ጤና መኮንን ፣ ፋርማሲ ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ፣ ሚድዋይፈሪ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያዎች ተመርቀው የጤና ሚኒስቴር የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ለተመዘገቡ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው የሚሰጠው ከታህሳስ 21-27/2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፥ ተፈታኞች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቦ የፈተናውን ፕሮግራም በቅርብ ቀን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#MoH

የጤና ተቋማት ወደነበሩበት ለመመለስ ርብርብር እየተደረገ ነው።

በግጭት ምክንያት የወደሙና የተጎዱ ጤና ተቋማትን ወደነበሩበት ለመመለስ እና የጤና አገልግሎት ለማስጀመር የአዲስ አበባ ጤና ቢሮና የፌዴራል ሆስፒታሎችን ከወደሙ ሆስፒታሎች ጋር በማስተሳሰር ድጋፍ እንዲያደርጉ ሰፊ ስራ መጀመሩን ከጤና ሚኒስቴር ተሰምቷል።

በቀጣይ ሌሎች ክልሎች እና ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን በማስተባበር የድጋፍ ስራው በስፋት እንዲቀጥል ይደረጋል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት:-

• ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌንየም ሜዲካል ኮሌጅ 👉 ደሴ ሆስፒታልን፤
• ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 👉 ከልዋን ሆስፒታልና ቦሩ ሜዳ ሆስፒታልን፤
• አቤት ሆስፒታል 👉 ባቲ ሆስፒታልን፤
• የካቲት 12 ሆስፒታል 👉 ወረ ኢሉ ሆስፒታን፤
• ምኒሊክ ሆስፒታል 👉 መሃል ሜዳ ሆስፒታልን፤
• ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል 👉 ከሚሴ ሆስፒታልን፤
• ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል 👉 ሀይቅ ሆስፒታልን፤
• ራስ ደስታ ሆስፒታል 👉 ደብረ ሲና ሆስፒታልን፤
• አለርት ሆስፒታል 👉 ኮምቦልቻ ሆስፒታልን፤
• ዘውዲቱ ሆስፒታል 👉 ደጎሎ ሆስፒታልን፤
• ጋንዲ ሆስፒታል 👉 ሞላሌ ሆስፒታልን፤
• አማኑኤል ሆስፒታል የአእምሮ ጤናና የስነልቦና ማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ 👉 ለሁሉም ሆስፒታሎች ድጋፍ ለመስጠት ትስስር በመፍጠር ወደ ስራ ገብተዋል።

ጤና ሚኒስቴር የአዲስ አበባ እና ፌዴራል ሆስፒታሎች እያደረጉ ስላሉት ርብርብ ምስጋና አቅርቧል።

ሆስፒታሎቹ በአፋጣኝ ስራ ለማስጀመር ከክልሉ እና ከጤና ሚንስቴር ጋር እየሰሩ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ወደነበሩበት ለመመለስ አሁንም ከፍተኛ መዋለ ነዋይና ድጋፍ ስለሚያስፈልግ ሁሉም የሚመለከተው አካል ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#MoH

አዳዲስ ምሩቃን ሃኪሞችን ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የጤና ሚኒስቴር አዳዲስ ምሩቃን ሃኪሞችን በቅጥር ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል የፕሮጀክት ስምምነት ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ጋር ተፈራረመ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፕሮክጀቱ በብዙ ልፋት ተመርቀው ስራ ላይ ያልተሰማሩ ሃኪሞችን ወደ ስራ የሚያሰማራ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ ትልቅ እምርታ ነው ብለዋል፡፡

ከተያዘው አመት ጀምሮ የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት የሶስት ዓመት ቆይታ እንደሚኖረው ገልፀዋል።

በመጀመሪያው ዓመት 2 ሺ 898 ሃኪሞችን ወደ ስራ ለማሰማራት መታቀዱን ተናግረዋል።

ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው በጀትም የመጀመሪያው ዓመት ከፌዴራል መንግሥት እና ከአጋር ድርጅቶች በተገኘ ገንዘብ የሚሸፈን ሲሆን፥ ሁለተኛው እና ሶስተኛው ዓመት ከፌዴራል፣ ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች እና ከአጋር የልማት ድርጅቶች ድጋፍ በተገኘ ገንዘብ የሚተገበር ይሆናል።

ከአራተኛው ዓመት በኋላ ሙሉ በሙሉ በክልሎች አቅም እንደሚተገበርም ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ጤና ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የፈተና ውጤታችሁን ከነገ ጀምሮ መመልከት ትችላላችሁ። በህክምና /Medicine/ ሙያ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች የፈተናው ውጤት ከነገ ጀምሮ መመልከት ይቻላል። ከታህሳስ 21-27/2014 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ የህክምና /Medicine/ ተመዛኞች ከየካቲት 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥር…
#MoH

በህክምና /Medicine/ ሙያ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች የፈተናው ውጤት ትላንት የካቲት 1 ይፋ ሆኗል።

ተመዛኞች ከትላንት ማክሰኞ ጀምሮ በ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እንዲሁም የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን እየተመለከቱ ነው።

በሌሎችም የሙያ ዘርፎች ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ውጤት በቅርብ ቀን ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ መረጃ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ የ2014 የሕክምና ሳይንስ /Medicine/ ተመራቂዎች #በሙሉ ማለፋቸውን ገልጿል።

ውድ ቤተሰቦቻችን የተለያዩ የ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልዕክቶች በ @tikvahuniversity በኩል ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoH በህክምና /Medicine/ ሙያ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች የፈተናው ውጤት ትላንት የካቲት 1 ይፋ ሆኗል። ተመዛኞች ከትላንት ማክሰኞ ጀምሮ በ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እንዲሁም የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን እየተመለከቱ ነው። በሌሎችም የሙያ ዘርፎች ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ውጤት በቅርብ ቀን ይፋ ይደረጋል ተብሎ…
#MoH

ከዛሬ የካቲት 4 ጀምሮ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ውጤታቸው ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ከታህሳስ 21 - 27/2014 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ከዛሬ የካቲት 04/2014 ዓ/ም ዓ.ም ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ውጤት የመመልከቻ አድራሻ hple.moh.gov.et ላይ ሲሆን ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤት መመልከት ይቻላል።

በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማሩበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahethiopia
#MoH

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ፥ በሚኒስቴሩ ስፖንሰርነት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሕክምና ኮሌጆች የስፔሻሊቲ ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች በያሉበት ተቋም የትምህርት ውል የሚገቡ መሆኑን ገለፀ።

የጤና ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ተማሪዎቹን የትምህርት ውል እያስገባ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ የትምህርት ውል ማዋዋሉ በመደበኛ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና ከመፍጠሩ በተጨማሪ በተማሪዎች ላይም ከፍተኛ እንግልት እየፈጠረ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በመሆኑም ተማሪዎቹ በያሉበት ተቋም ውል የሚገቡ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳው ወደፊት ይፋ ይደረጋል ብሏል።

@tikvahuniversity
#MoH

#ጨረታው_ተሰርዟል !

30 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የወባ አጎበር ግዢ ጨረታ ተሰረዘ።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር 30 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት በኬሚካል የተነከረ የወባ መከላከያ አጎበር ግዢ በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት በኩል ግዢ እንዲፈጸም ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

በዚህም መሰረት ፤ ዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ወጥቶ ተጫራቾች ቀርበው አሸናፊውን ቢለይም በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ መቅረቡን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ማጣራት በማድረግ ጨረታውን እንዲሰረዝ ማድረጉን አሳውቋል።

የጤና ሚኒስቴር በሌሎች ተቋማት የማጣራት ስራ መሰራቱን እንዲሁም ደግሞ በራሱ ባደረገው የማጣራት ስራ በጨረታ ሂደቱ ላክ የተፈጸመ ህገ-ወጥ ድርጊት እንዳላገኘ ገልጿል።

ነገር ግን " የብቃት ማረጋገጫ " እና " ምዝገባ " ጋር በተያያዘ በግብርና ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በህግ የተሰጠ ነገር ግን የስልጣን መደራረብ የነበረ መሆኑን እና የጨረታ መገምገሚያ መስፈርት ጋር በተያያዘ ቅሬታ ቀርቦ ባለበት ሁኔታ ሂደቱን ከማስቀጠል የፋይናንስ ድጋፍ በሚያደርገው ድርጅት አማካኝነት ግዢው እንዲፈጸም ማድረግ ለሚኒስቴሩ የተሻለ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመገንዘብ ጨረታው እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡

(ተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ProfessorSenaitFisseha ዛሬ የጤና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በቅጥር ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ፕሮጀክት ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ጋር ተፈራርሟል። ፕሮጀክቱ ዘንድሮ ጀምሮ ለ3 ዓመት ይቆያል። በመጀመሪያ አመት 2,898 ሃኪሞች ወደስራ ለማስገባት ታቅዷል። ለዚሁ ለመጀመሪያው ዓመት ስራ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከፌዴራል እና ከልማት አጋር…
#MoH

➤ በአዲስ አበባ ለ161 ጠቅላላይ ሀኪሞች ቅጥር ወጥቶ ለመቀጠረ ያመለከቱት 2,300 ናቸው።

0⃣ በሶማሌ እና አፋር ክልል ለጠቅላላ ሀኪሞች የስራ ቅጥር ቢወጣም #ምንም አመልካች ጠቅላላ ሀኪም ለማግኘት አልተቻለም።

ጤና ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር 2,898 አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በሃገር አቀፍ ደረጃ በመቅጠር ወደ ስራ ለማሰማራት ከሁሉም ክልል ጤና ቢሮዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በተደረገ ስምምነት ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም አንድ ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩ ይታወሳል።

ይህ እኩል በእኩል መዋጮ ፕሮጀክት የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በመጀመሪያዉ የፕሮጀክት ዓመት ወደ ስራ ለማሰማራት ከታቀደው 2,898 ጠቅላላ ሐኪሞች እና በተጨማሪ ከፕሮጀክቱ በጀት ዉጪ በክልሎች ተጨማሪ በጀት ➙ 961 ሃኪሞች በድምሩ ➙ 3,701 አዳዲስ ምሩቃን ጠቅላላ ሀኪሞች ለመቅጠር ከወራት በፊት በሁሉም የከተማ አስተዳደር እና የክልል ጤና ቢሮዎች የቅጥር ማስታወቂያ ወጥቶ ነበር።

የቅጥር ማስታወቂያ ቢወጣም አመልካች ጠቅላላ ሀኪሞች በሁሉም የቅጥር ማስታወቂያ በወጣባቸው ቦታዎች ላይ #በወጥነት እንዳላመለከቱ በተደረገ ክትትል ታውቋል።

ለአብነት ያህል ፤ አዲስ አበባ ላይ ለ161 የቅጥር መደብ 2,300 ጠቅላላ ሀኪሞች ናቸው ለመቀጠር ያመለከቱት።

ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በአንዳንድ ክልሎች ለቅጥር ማስታወቂያ ከወጣባቸዉ መደቦች በጣም ባነሰ ቁጥር ያመለከቱ ሲሆን በአንዳንድ ክልሎች ደግሞ ምንም አመልካች አልተገኘም።

ምንም አመልካች ጠቅላላ ሀኪም ያልተገኘው ሶማሌ እና አፋር ክልሎች ላይ ነው።

እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 1,309 ጠቅላላ ሃኪሞች ብቻ የተቀጠሩ ሲሆን ይህም ከሚጠበቅው የቅጥር ብዛት አንፃር 35% ላይ ይገኛል።

ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ጠቅላላ ሃኪሞች በተለይም አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞች የቅጥር ማስታወቂያ በወጣባችው ክልሎች ፦
➡️ አማራ ክልል፣
➡️ አፋር ክልል፣
➡️ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
➡️ ጋምቤላ ክልል፣
➡️ ኦሮሚያ ክልል፣
➡️ ሲዳማ ክልል፣
➡️ ደቡብ ክልል፣
➡️ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እና ሶማሌ ክልል ለ2,392 ጠቅላላ ሃኪሞች ክፍት የሆነ የቅጥር ቦታ እንዳለ አውቀው እድሉን እንዲጠቀሙ ጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#MoH

ሚሊኒየም አዳራሽ ለሚድሮክ ተመለሰ።

2 ዓመታት የኮቪድ -19 የህክምና እና የድንገተኛ ምላሽ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል የቆየውን አዲስ ፓርክ /የሚሊኒየም አዳራሽ/ ለባለቤቱ ተመለሰ።

ጤና ሚኒስቴር ሚሊኒየም አዳራሽን ከምስጋና ጋር ለባለቤቱ ለሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አስረክቧል።

የጤና ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዶከተር ሊያ ታደሰ ማዕከሉን ለሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባስረከቡበት ወቅት ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪ ፦ " ዛሬ የኮቪድ-19 የህክምና እና የድንገተኛ ምላሽ ማዕከሉን ዘግተን ወደነበረበት የምንመልሰው ኮቪድ ስለጠፋ ሳይሆን አገልግሎቱን በሌሎች የጤና ተቋማት ለማቅረብ የምንችልበት አቅም ስለፈጠርንና በመላ ሀገሪቱ የክትባት ሽፋንን በማድረስና የበሽታውን ጉዳት መቀነስ በመቻሉ ነው " ብለዋል፡፡

በቀጣይም ክትባቱን ያልወሰዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወስዱና ጥንቃቄያቸውን ሳይዘናጉ እንዲተገብሩ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#MoH

የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና ምዝገባ ተጀመረ።

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በ2016 የትምህርት ዘመን በ21 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች አመልካቾችን ተቀብሎ እንደሚያሰለጥን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና /ERMP/ መግቢያ ፈተና በመስጠት አወዳድሮ እንደሚያሰለጥን የገለፀ ሲሆን የህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ያላቸውና የስፔሻሊቲ ስልጠና መውሰድ የሚፈልጉ ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉ ገልጿል።

ምዝገባው ከዛሬ ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ /ም የሚጀምር ሲሆን ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚያበቃ አሳውቋል።

አመልካቾች የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ www.moh.gov.et/ermp ላይ በመግባትና ለመሰልጠን በሚፈልጉት የስፔሻሊቲ ትምህርት ላይ በመመዝገብ መወዳደር እንደሚችሉ ተገልጿል።

ተመዝጋቢዎች ምዝገባውን ከመጀመራቸው በፊት ዝርዝር መረጃዎችንና መመሪያዎችን በዚህ ይመልከቱ ተብሏል👇
https://www.moh.gov.et/site/initiatives-4-col/ermp

@tikvahethiopia
#ትኩረት🚨

ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በተለይ ትንንሽ ህጻናት በጉንፋን እና በጉንፋን መሰል የመተንፈሻ አካላት ህመም እየተያዙ ይገኛሉ።

ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመክቶ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ያጋራ መግለጫ ልከዋል።

ምን አሉ ?

➡️ የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

➡️ ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ ሙከስ መምብሬን ” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡

➡️ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

➡️ ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

➡️ የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል።

➡️ ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ ፦
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° አይን ማሳከክ እና መቅላት፣
° ማስታወክ፣
° ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣
° ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

➡️ ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

➡️ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

➡️ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል።

➡️ የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን የምንከላከልባቸው መንገዶች ምንድናቸው ?
° የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣
° ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) ማድረግ
° በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት
° የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡


#ማሳሰቢያ ፦ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

#MoH #EPHI

@tikvahethiopia
#SavetheChildren #MoH

የህፃናት አድን ደርጅት (Save the children) በኢትዮጵያ በ3 ክልሎችበ16 ወረዳዎች የክትባት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚረዳ “ቡስት” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ ፕሮጀክቱን ይፋ ያደደረገው ከጂኤስኬ ተገኘ በተባለ የገንዘብ ድጋፍ ፣ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው።

ፕሮጀክቱ በአማራ፣ ኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ 16 ወረዳዎች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ክትባት በሚስጥበት ወቅት ገጠራማ በሆኑ ቦታዎች ለትራንስፓርት አገልግሎት የሚረዱ 50 ታብሌቶች የተገጠሙላቸው 52 ሞተር ሳይክሎችን ድርጅቱ አበርክቷል።

ድርጅቱ ፥ “ በዚህ ፕሮጀክት ከ200 ሺሕ በላይ ልጆች እንዲከተቡ ይደረጋል ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ቲክቫህ ለህጻናቱ የሚሰጡት ክትባት የምን በሽታ መከላከያ ነው ? ሲል ላቀገበው ጥያቄ “ በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡትን 13ቱንም ክትባቶች ሳፓርት እናደርጋለን ” የሚል መልስ ከድርጅቱ ተሰጥቷል።

ክትባቱ ፦
- ሚዝልስ፣
- ፓሊዮ፣
- ዲያሪያ፣
- ኒሞኒያና ከመሳሰሉ ህመሞች የሚከላከል ነው ተብሏል።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴዔታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ “ በኢትዮጵያ ውስጥ ክትባት በአግባቡ ያልወሰዱና ጭራሽም ያልወሰዱ በርከት ያሉ ህፃናት አሉ ” ሲሉ ጠቁመዋል።

እኚህም ከ1 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

እነዚህም ራቅ ያሉ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ናቸው።

ምንም ክትባት ያላገኙና ጀምረው ያቋረጡ ህፃናት በአብዛኛው በአማራ፣ ኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች እንደሚገኙ በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-01

 #TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia