TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ቴድሮስ ምን አሉ ? የአፋር እና የአማራ ክልል ባለስጣናት ምን መለሱ ? የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ፦ " 7 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበት ክልል ከአንድ አመት በላይ ሙሉ በሙሉ ከበባ ውስጥ ሆናል። በዚህ ምክንያት ህዝቡ ምንም አይነት የምግብ አቅርቦት፣ የህክምና ፣ ኤሌክትሪክ፣ የቴሌፎን ፣ የመገናኛ አገልግሎት አያገኝም። በመድሃኒት አቅርቦት እጥረት ምክንያት ሰዎች…
#Update

የዓለም ጤና ድርጅት በዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ቅሬታ እና ክስ ቢቀርብም በጦርነት ለተጎዳው የትግራይ ክልል ህዝብ እርዳታ መጠየቁን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ባለፈው ዓርብ የኢትዮጵያ መንግስት ዶክተር ቴድሮስ ጎጂ እንዲሁም የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት እና TPLFን በመደገፍ የተሳሳተ ተግባር ላይ መሳተፋቸውን በመግለፅ ከሶ ድርጅቱ ምርመራ እንዲያከናውን መጠየቁ ይታወሳል።

ዛሬ የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በይፋ ክስ ማቅረቡን አረጋግጧል።

ድርጅቱ ግን 7 ሚሊዮን ለሚደርሰው የትግራይ ክልል ህዝብ መሰረታዊ አገልግሎት እንዲደርስ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈቅድ መጠየቁን እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ባለፈው ዓርብ ዕለት የኢትዮጵያ መንግስት ቅሬታውን ያቀረበው ባለፈው ሳምንት ዶ/ር ቴድሮስ መንግስት ወደትግራይ ክልል መድሃኒትና የነፍስ አድን እርዳታዎች እንዳይገባ እየከለከለ ነው በማለት በክልሉ ያለው ሁኔታ ሲኦል ነው ብለው ከገለፁ በኃላ ነው።

መንግስት ፥ ዶ/ር ቴድሮስ የሰጡት አሰተያየት የዓለም የጤና ድርጅትን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚጥል ፤ የተጣለባቸውን ህጋዊ እና ሞያዊ ኃላፊነት ጥሰው በመገኘታቸው ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር።

በተመድ የኢትዮጵያ ልዑክም ዶ/ር ቴድሮስ የፖለቲካ ውግንና እንዳላቸው በመግለፅ ኢትዮጵያን ከሚመለከቱ ጉዳዮች እራሳቸው እዲያርቁ ጠይቆ እንደነበር የፈረሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ዶ/ር ቴድሮስ ከሰጡት አስተያየት ጋር በተያያዘ የአማራ እና አፋር ክልል ባለስልጣናት ጠንካራ ትችት ሰንዝረው ዶ/ር ቴድሮስ የተናገሩት ለህወሓት ፕሮፖጋንዳ መሆኑንና በአፋር እና አማራ ክልል ህወሓት ስላደረሰው ጥፋት ተናግረው እንደማያውቁ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#ነፃ_ዋይፋይ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ፣ እንጦጦ ፣ አንድነት ፓርክ እና የወዳጅነት አደባባዮች በከፍተኛ ወጪ የዋይፋይ (WiFi) አገልግሎት ገንብቶ በነጻ ማቅረቡን ዛሬ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ውበት

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ?

0911607446 ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!              
ሙሉ ከወገብ በላይ (ቦዲ) - 950ብር
የቦርጭ ብቻ (ጉርድ) -650  ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ @wibet1
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ ቤዛ ህንፃ 2nd floor # webet
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ምድቧን የማለፍ እድል አላት ?

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ ሀ ሦስተኛ የጨዋታ መርሐ ግብር ከቡርኪና ፋሶ አቻው ጋር ዛሬ ምሸት 1 ሰዓት ላይ በባፎሳም ስታዲየም ያካሂዳል።

ለመሆኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ ምድቧን የማለፍ እድል አላት ? ትላንት መግለጫ የሰጡት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተከታዩን ተናግረዋል ፦

" ሁለት ቡድኖች በቀጥታ ከምድቡ ያልፋሉ። ጥሩ ሶስተኛ ሆኖ የሚያልፍም ይኖራል።

ጨዋታውን ማሸነፍ በሌሎች ውጤት ላይ የሚወሰን ቢሆንም የመጀመርያው ነገር ጨዋታውን ማሸነፍ ነው።

የማለፍ ጉዳይ በቀጣይ የሌሎች ውጤትን ተመርኩዞ ነው የሚወሰነው።

ከዚህ ባሻገር በቡድናችን ላይ ችግሮች ተመልክተናል ፤ በተለይ በአእምሮው ረገድ። በዛ ላይ ከሰራን ፣ ባለን ነገር ላይ እምነት ካለን እና እህንንም ወደ ተጫዋቾቹ ማስረፅ ከቻልን ማድረግ እንደምንችል አምናለሁ። እድሉ አለን ፤ እንደምናሳካም አምናለሁ። "

@tikvahethiopia
#DireDawa

የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ 3.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የመኪና ስጦታ ተበረከተላቸው።

ለቀድሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ አስተዳደሩ በአመራርነት ዘመናቸው ላበረከቱት መልካም ስራዎች የምስጋና ኘሮግራም ተካሄዶል።

በዚሁ ፕሮግራም ላይ 3.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዘመናዊ የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ " ጥቂት ብንዘገይም፤ እጅግ ለምንወዳቸው የቀድሞ ከንቲባችን እና ወንድማችን አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ዛሬ ያደረግነው ሽኝትና የሰጠነው ስጦታ፤ በአመራርነት ዘመኑ ካደረጉት አሰተወፅኦ አንፃር ለሳቸው ያንስባቸዋል እንጂ አይበዛም " ሲሉ ተናግረዋል።

ስጦታው በባለሀብቶች ተሳትፎ የተበረከተ መሆኑ ተገልጿል።

የቀድሞው ከንቲባ ለሶስት ዓመት ሙሉ ከተማዋ የነበረባትን የፀጥታ ችግር የፀጥታ አካላትን በማሰባሰብ ፣ አመራሮችን በማቀናጀት የከተማዋ ሰላም በአስተማማኝነት እንዲረጋገጥ እና ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አመራር የሰጡ ጠንካራ መሪ እንደነበሩ ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት ከቀድሞ ከንቲባው በተጨማሪ የድሬዳዋ ፀጥታ አካላት ፣ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ከ25 ሺህ ብር እስከ 100 ሺህ ብር በየደረጃው ተሸልመዋል። አጠቃላይ ሽልማቱ ከ700 ሺህ ብር በላይ እንደሆነ ተመላክቷል።

ብሩ የተገኘው ከባለሀብቶች ሲሆን የመንግስት በጀት እንዳልተነካ ተገልጿል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጠይቀው ቀና ምላሽ ለሰጡ የከተማው ባለሀብቶች ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

የኢፌዴሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።

የበዓሉ ታዳሚዎችና እንግዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆንና በዓሉን በሰላም እንዲከበር ግብረ ኃይሉ ከወትሮው በተለየ መልኩ በቂ ዝግጅት በማድረግ ስምሪት ወስዶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጿል፡፡

ግብረኃይሉ ፥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ የፀጥታ አካላት ማሰማራቱን ገልፆ በታቦታት ማደሪያ ስፍራዎችና በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በሚገኙበት አካባቢ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የተከላከሉ ተግባራት ፦

• ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ ነው።

• በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ድሮን ማብረር ወይንም ማንቀሳቀስ አይችሉም።

• ምንም አይነት የጦር መሳሪያ፣ ተቀጣጣይም ሆነ ስለታማ ቁሳቁስ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም።

የበዓሉ ታዳሚዎች ለደህንነት ሲባል ፍተሻ የሚደረግ መሆኑን ከወዲሁ በማወቅ እና በመረዳት ትብብር እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በፍጥነት ለጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥቆማ ለመስጠት በስልክ ቁጥር ፦
• +251115-52-63-03፣
• +251115-52-40-77፣
• +251115-54-36-78 እና
• +251115-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀምና በአካባቢው ላለ የፀጥታ ኃይል መረጃውን በአካል ማድረስ ይቻላል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ሰሜን_ኮሪያ

ሰሜን ኮሪያ ሁለት የተጠረጠሩ የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳኤሎችን (SRBM) በመዲናዋ ፒዮንግያንግ ከሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጦር ማሳወቁን ሮይተርስ ዘግቧል::

ጃፓን በተመሳሳይ መወንጨፉን ሪፖርት አድርጋ ድርጊቱን የሰላም እና የፀጥታ ጠንቅ ነው ስትል አውግዛለች። ቻይና በበኩሏ ሁሉም ወገኖች የቀጠናውን መረጋጋት እንዲያስጠብቁ ስትል አሳስባለች::

ዛሬ ሰሜን ኮሪያ እንዳስወነጨፈች የተነገረው የሚሳኤል ሙከራ በዚህ ወር 4 ኛው ነው ተብሏል:: ኒውኩሌር የታጠቀችው ሰሜን ኮሪያ ከዛሬ በፊት ከ2 ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 3 የሚሳኤል ሙከራዎች አድርጋለች:: ይህም ያልተለመደ ፈጣን ተከታታይ ሙኩራ ነው ተብሏል::

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የጥምቀት በዓልን ለማክበር የሚወጣው ምዕመን ግጭት ቀስቃሽ ጽሑፎችን እና አርማ የሌላቸውን ባንዲራ ይዞ መውጣት እንደማይችል አስታወቀ::

ፖሊስ ኮሚሽኑ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ምዕመኑ ከበዓሉ አላማ ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ከማድረግ ተቆጥበው በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል::

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሰላም እንዲጠናቀቅ ከበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል::

በዓሉ የአደባባይ በመሆኑ በሁሉም አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር በግልጽና በስውር የተጠናከረ ጥበቃ መኖሩን ጠቅሰዋል።

በዓሉ በሚከበርባቸው ሁለት ቀናት ወደ ማክበሪያ ቦታው መግባት የሌለባቸው ግጭት የሚቀሰቅሱ ጽሑፎች ፣ አርማ የሌለው ባንዲራ እንዲሁም ስለታማ ነገሮች ይዞ መግባት እንደማይቻልም አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል::

ምንጭ : አሀዱ ሬድዮ (ፎቶ - ከኢዜአ)

@tikvahethiopia
#GoodayOn Mobile App

የፈለጉትን ባለሙያ ካሉበት ሆነው አማርጠው የሚያገኙበት መተግበሪያ!

አስጠኚ ፣ ሹፌር ፣ ቧንቧ ሰራተኛ ፣ ኤሌክትሪሺያን ፣ ዲሽ ጥገና ፣ መካኒክ ፣ የግንባታ ፊኒሺንግ ፣ ሽያጭ ፣ የሂሳብ ባለሞያ እና ...ሌሎችም

ከGoodayOn መተግበሪያ በተጨማሪ ፤ ወደ 9675 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።

GoodayOn መተግበሪያን ለማውረድ ፤ https://cutt.ly/JWR6vZb
ቴሌግራም ቻናል ፤ @goodayOn #ጉዳይ 9675
800,000💵

ትላንትና ምሽት በታላቁ ቤተ-መንግስት " በገበታችን ሀገር እንገንባ ፤ በትብብር ወገን እናግዝ " በሚል መርህ በተካሄደ የእራት መርሀ ግብር ከትኬት ሽያጭ ብቻ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ መገኘቱ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በትላንት ምሽቱ የእራት መርሀ ግብር ከትኬት ሽያጭ በቀጥታ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቋል።

በመረሐግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዳያስፖራ አደረጃጀት መሪዎች፣ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር ስለተፈቱ ግለሰቦች ምን አሉ ? ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦ " ... ትላንት ክስ የተቋረጠላቸው የተሸነፉ ኃይሎች ክስ እንዲቋረጥ እና ከእስር ቤት እንዲወጡ ሲደረግ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል። ይህ ቁጣ የተቀሰቀሰው በሁለት ቡድኖች ነው። አንደኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ጭር ሲል የማይወድ ፣ ሁል ጊዜ እያጋጨ በሰበር ዜና ብር የሚሰበስብ፣ የት እንዳለ የማይታወቅ ካለበት ሆኖ ስንዋጋ…
“አንድም መንግስት ‘እነዚህ ሰዎች ታስረዋልና ፍታ ብሎ የጠየቀኝ የለም” - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ትላንት በቤተ መንግስት በተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ፤ በቅርቡ ከእስር የተፈቱ እስረኞችን በተመለከተ “ጉዳዩን እኛም መጀመሪያ ስንሰማ ደንግጠን ነበር” በሚል ለተናገሩት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እስረኞችን ለመፍታት ከውሳኔ ላይ የተደረሰው ከወር በፊት እንደነበር የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሆኖም የሚፈቱ የእስረኞች ዝርዝር እርሳቸውን ጨምሮ ለካቢኔ አባላት የቀረበው የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ የህዳሴው ግድብ በሚገኝበት ስፍራ በተደረገ የሚኒስትሮች ስብሰባ ወቅት እንደነበር አስረድተዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ “እውነቱን ለመናገር ፖለቲካሊ እስረኞችን ለመፍታት ‘እነዚህን ጉዳዮች እናሳካ ነው’ ያልነው እንጂ፤ እነማን ይፈቱ የሚለውን በቀደም ህዳሴ [ግድብ] የሚኒስትሮች ስብሰባ እስካደረግንበት ቀን ድረስ እኔም አላውቅም። እንፍታ ብለን ወስነናል። ዐቃቤ ህግ ሲያጠና ቆይቶ፤ ዝርዝር አመጣልን። ‘እነ እንትናማ አይቻልም፤ እነ እንትና ይቻላል’ ተጨቃጭቀን የተወሰኑ ሰዎች ላይ ወስነን መጣን” ሲሉ ስለ ሂደቱ ገለጻ አድርገዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ እስረኞችን ለመፍታት ሲወሰን የንግግሩ ማዕከል “ ግለሰቦች አልነበሩም ” ያሉ ሲሆን የውይይቱ ማጠንጠኛ “የበጎ ፍቃድ ምልክት (gesture) እና ሆደ ሰፊነት (magnanimity) ያስፈልጋል” የሚል እንደነበር ገልጸዋል። “ሀሳቡ፤ ዝም ብሎ ድርቅ ያለ ነገር አድርገን ሀገራችንን እንዳንጎዳ የሚል ነው” ሲሉ አክለዋል።

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከውሳኔው ጀርባ “ የሌላ ሀገር ግፊት አለ ” በሚል ለሚቀርቡ አስተያየቶችም በትላንቱ ንግግራቸው ምላሽ ሰጥተዋል። እስረኞቹ እንዲታሰሩም ሆነ እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀረበ “አንድም መንግስት” እንደሌለ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “አንድም መንግስት ‘እነዚህ ሰዎች ታስረዋልና ፍታ ብሎ የጠየቀኝ የለም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የእስረኞች ፍቺ ጉዳይ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ ውይይት የተደረገበት ከአንድ ወር በፊት መሆኑን የጠቆሙት አብይ፤ ውሳኔው “እስከ ታች ድረስ” ውይይት የተደረገበት እንጂ “እንግዳ ጉዳይ” እንዳልነበር ገልጸዋል።

“ሁሉም ክልል ተወያይቶበታል። አሁን ድንገት ደርሶ ‘ድንገት ሆነብኝ’ የሚለው ተቀባይነት የለውም። ከወር በላይ ተወያይተንበታል። አዲስ ነገር አይደለም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

Credit : ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሊቀ ጳጳስ ዘኢሉባቡር አረፉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኢሉባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነሥርዓት እና ቀብራቸው የሚፈጸምበት ቦታን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ ይገለፃል ተብሏል።

መረጃው የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
በቀን 22 በረራ ወደ ጎንደር !

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ለጥምቀት በዓል አከባበር ለሚጓዙ ደንበኞቹ ክብረ ወሰን ሆኖ የተመዘገበ በቀን 22 በረራዎች ማድረጉን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ምድቧን የማለፍ እድል አላት ? የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ ሀ ሦስተኛ የጨዋታ መርሐ ግብር ከቡርኪና ፋሶ አቻው ጋር ዛሬ ምሸት 1 ሰዓት ላይ በባፎሳም ስታዲየም ያካሂዳል። ለመሆኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ ምድቧን የማለፍ እድል አላት ? ትላንት መግለጫ የሰጡት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተከታዩን ተናግረዋል ፦ " ሁለት ቡድኖች በቀጥታ ከምድቡ ያልፋሉ። ጥሩ ሶስተኛ ሆኖ…
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሰናበተች።

ሀገራችን ከ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆናለች።

ብሄራዊ ቡድናችን ዛሬ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ እኩል ቢለያይም በአንድ ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

በዛሬው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ በፍጹም ቅጣት ምት ለሀገራችን ብቸኛዋን ጎል በ52ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

@tikvahethiopia