TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ውይይት እና እርቅ የሚጀምርበት ጊዜ ነው " - አንቶኒዮ ጉተሬዝ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይ ልቤ እንደተሰበረ ነው ብለዋል።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፥ " ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለስደተኞች ባደረጉት ቸርነት እና መስተንግዶ አርአያ መሆናቸውን እመሰክራለሁ። ኢትዮጵያውያን ሰላም ይገባቸዋል " ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

አክለውም ፥ " ለሁሉም ወገኖች የማቀርበው ጥሪ ፦ ግጭቱን በሁሉም መልኩ ያቁሙ። ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሁሉ በተቻለ ፍጥነት እርዳታ ሊደርሳቸው ይገባል " ሲሉ ገልፀዋል።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፥ ውይይት እና እርቅ የሚጀምርበት ጊዜ ነውም ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion የአማራ ክልል መንግስት ከፋኖ አደረጃጀት ትጥቅ እንደማያስፈታ አስታወቀ:: " መንግስት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው " የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ ነው ሲል የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ገልጿል:: የክልሉ መንግሥት ይህን የገለፀው ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር በተወያየበት መድረክ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል:: በዚሁ መድረክ : " ፋኖ…
መንግሥት ለአገር ሕልውናና ለሕዝብ ነጻነት የተጋደሉና ጀብድ የሠሩ ፋኖዎችን የበለጠ ያደራጃል እንጂ ትጥቅ አያስፈታም ሲሉ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተናገሩ፡፡

አቶ ግዛቸው ይህን የተናገሩት ለኢፕድ በሰጡት ቃለምልልስ ነው።

አቶ ግዛቸው " በአማራ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ የአማራን ሕዝብ ከጠላት የሚከላከል፣ ከውርደት የሚታደጉና በልማትና በፖለቲካው መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን ዋጋ የሚከፍሉ ሁሉ ፋኖዎች ናቸው፤ በመሆኑም መንግሥት ለአገር ሕልውናና ለሕዝብ ነጻነት የተጋደሉና ጀብድ የሠሩ ፋኖዎችን የበለጠ ያደራጃል እንጂ ትጥቅ አያስፈታም " ብለዋል፡፡

ፋኖ የታጠቀ ኃይል በመሆኑ ክልሉ ላይ አደጋ በተቃጣ ጊዜ እንደማንኛውም ሰው በራሱ አደረጃጀት መሰረት ከሌላው የመንግሥት የፀጥታ ኃይል ጋር ተቀናጅቶ ጠላትን ይመክታል ብልዋል።

አቶ ግዛቸው ፥ ፋኖ ሥርዓት የሚያከብርና ለአማራ ሕዝብ ጥቅም ራሱን መስዋዕት የሚያደርግ ነው፡፡ ሥርዓት አልበኛ የሆነ፣ ለመዝረፍ ለመስረቅና ሌላ ብጥብጥ ለማንሳት የሚንቀሳቀስ ኃይል ካለ ፋኖን የሚወክል ስላልሆነ የክልሉ መንግሥት በሕጉ መሰረት ሥርዓት እንደሚያስከብር ገልጸዋል፡፡

ፋኖ ከመንግሥት አቅም በላይ የሆነ ኃይል ሳይሆን ከመንግሥት ሥር ሆኖ እንደሌላው ማኅበረሰብ የሚዳኝ ነው ያሉት አቶ ግዛቸው ከዚህ ያፈነገጠና ሌላ ፍላጎት ያለው አካል ካለ በፋኖ ስም መጠራት የለበትም ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት ከፖለቲካ አመራሩ ጀምሮ ትጥቅ እንዴት ነው የሚያዘው፣ በትጥቁ የሆነ ነገር ቢፈጽም ምን ይሆናል የሚሉና መሰል ጉዳዮች ሥርዓት ባለው መንገድ እንዲመራ ፍላጎት እንዳለው ጠቅሰው፤ ይህ ግን ትጥቅ ከማውረድ ጋር የሚገናኝ ሳይሆን የትጥቅ አስተዳደሩ በሂደት ታይቶ በሥርዓት መመራት አለበት ከሚል እሳቤ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

@tikvahethiopia
#AU

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች ተስማምተው የኅብረቱ ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዲደረግ በመወሰናቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የኅብረቱን ጉባኤ በአካል በአዲስ አበባ ለማከናወን ያሳለፉትን ውሳኔ ኢትዮጵያ ታደንቃለች ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፥ " ወንድማዊ አጋርነታችሁን በምንሻበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የኮሮናን መስፋፋትንና ወቅታዊውን የጸጥታ ሁኔታ እንደ ምክንያት በማንሣት የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ አካላት ተግባራቸው ኢትዮጵያን አሳዝኖ ነበር " ብለዋል።

አክለው ፥ " በዓመት ሁለት ጊዜ ከሚደረጉት የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤያት መካከል በኮሮና ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የመጀመሪያው ጉባኤ ከ3 ዓመት በኋላ ዳግም በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራትና ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ጋር በመሆን መንግስት ልዩ ልዩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። " ሲሉ አስረድተዋል።

ዶክተር ዐቢይ፥ " ጉባኤው እዚህ መካሄዱ የሚኖረውን ትርጉም የተገነዘቡና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን ጠንካራ አቋም፣ ለአፍሪካ ኅብረት እውን መሆን ያበረከተችውን አስተዋጽኦ እና የአፍሪካ ጉዳዮች በአፍሪካውያን እንዲታዩ ያላትን የጸና መርሕ ከፍ ያለ ዋጋ የሰጡ የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤው በአዲስ አበባ መካሄዱን መርጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ደስ ተሰኝታለች፤ እንኳን ደስ ያለን " ሲሉ ገልፀዋል።

* ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Alibaba #ErmiasAmelga

የኢትዮጵያን የበይነ መረብ ግብይት ከሥሩ ይቀይራል ተብሎ የሚጠበቀው፣ የአሊባባና የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ አዲስ ኩባንያ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ-ኮሜርስ)፣ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

በታዋቂው የቻይና ኩባንያ አሊባባ ባለቤት ጃክማና በኢትዮጵያዊው የቢዝነስ ሐሳብ አመንጪ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ትብብር እየተቋቋመ ያለው አዲሱ የኢ-ኮሜርስ ቴክኖሎጂ ፣ ከሁለቱ የተውጣጣ ጥምር ስም እንደሚሰጠውም ታውቋል፡፡

ድርጅቱ በበይነ መረብ ቴክኖሎጂው ላይ ሁሉንም በኢትዮጵያ የሚገኙ የግብይት ምርቶች መገኛ ዋጋ የሚያሳውቅ መሆኑንና የበይነ መረብ ግዥ ትዕዛዝ፣ የዲጂታል ክፍያና የአቅርቦት አገልግሎትን ያስችላል ተብሏል፡፡

አዲሱ ድርጅት የአቅርቦት (Delivery) አገልግሎቱን ለ " እሺ " ኤክስፕረስ ለመስጠት ስምምነት ላይ መድረሱን ጋዜጣው አረጋግጫለሁ ብሏል።

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ፥ " ወደ ትግበራ ለመግባት ቀጣይ ስድስት ወራት ያስፈልጉናል ፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያትም የዘገዩብን ሥራዎች አሉ " ሲሉ መናገራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Somalia

የሶማሊያ መንግስት ቃል አቀባይ በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገቡ።

ዛሬ ጥዋት በሞቃዲሾ የአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ፍንዳታ መድረሱን ፖሊስ ሪፖርት አድርጓል።

በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቱ የቀድሞው ጋዜጠኛ እና የአሁን የሶማሊያ መንግስት ቃል አቀባይ መሀመድ ኢብራሂም ሙአሊሙ ተሽከርካሪ ኢላማ እንደተደረገ እና እሳቸው ላይም ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።

ቃልአቀባዩ በጥቃቱ ቆስለው ሞቃዲሾ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል እስካሁን የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Timket የጥምቀት በዓል ሊከበር ቀናቶች ቀርተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓል በድምቀት የሚከበርበት የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ሥራ በመፋጠን ላይ መሆኑ ተገልጿል። ወቅታዊ የግንባታ ይዘቱ ከላይ በፎቶ ተያይዟል። Photo Credit : EOTCTV @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Update

የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ተጠናቆ ለበዓል አከባበር ሥርዓቱ ዝግጁ ሆነ።

ከአንድ ወር በፊት የግንባታ ሥራው የተጀመረው የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ መጠናቀቁና ለጥምቀት በዓል ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።

በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል የባህረ ጥምቀቱን ገንዳ በአዲስና ዘመናዊ መንገድ የመገንባት ፣ የኤሌክትሪክና የውኃ መስመር ዝርጋታ ሥራዎች እንዲሁም ቅጽረ ጊቢውን የማስዋብና ቡራኬ ማከናወኛ ስፍራዎችን የማስጌጥ ሥራዎች ተከናውነዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጸበል መርጫ መስመሮች የተገጠሙ ሲሆን ብቃት ያላቸው የውኃ መሳቢያ ሞተሮች ገጠማም ተከናውኖ ዝግጁ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራም ተከናውኗል።

በአጠቃላይ የዘንድሮን የጥምቀት በዓልን በጥሩ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችሉ የግንባታሥራዎች፣ የታቦታት ማረፊይያ ቦታዎች፣ የክብር እኝግዶች የሚስተናገዱባቸው ስቴጆችና የድምጽ ማጉያ መስመር ዝርጋታዎች ተከናውኗል።

ቀሪ የግንባታ ሥራዎችና ይዞታውን የማስከበር ተግባራትም በዓሉ ከተከበረ በኋላ ተጠናክረው መቀጠል ይችሉ ዘንድ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።

ቪድዮ : 25 MB (Wi-Fi ተጠቀሙ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Abala በአፋር ክልል ፣ አብአላ ከተማ በሚሰነዘር የከባድ መሳሪያ ድብደባ የከተማው ነዋሪ ከቄዬው እየተሰደደ መሆኑን የከተማው ከንቲባ ተናገሩ። ከንቲባው ይህን የተገሩት ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ነው። ከመቐለ ከተማ 40 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው የአፋር የንግድ ከተማ አብአላ ከንቲባ አቶ ጣሂር ሀሰን ህወሓት ተቆጣጥሯቸው ከነበሩት የአፋር እና አማራ ክልሎች እንዲወጣ ከተደረገ በኃላ አብአላ ላይ ተደጋጋሚ…
" በአፋር በኩል ጦርነቱ አልቆመም "- አፋር ክልል

የአፋር ክልል መንግስት ፥ ህወሓት በሰላም ወዳዱ የአፋር ህዝብ ላይ በድጋሚ እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ማቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል።

ክልሉ ፥ " አሸባሪው ህወሓት በኪልበቲ ረሱ / ዞን ሁለት / በአብአላ በኩል ከታህሳስ 10/2014 ጀምሮ በከፈተው አዲስ ግንባር በተከታታይ እየተኮሰ ባለው ከባድ መሳሪያ ንፁሀን ዜጎችን መጨፍጨፉን ቀጥሏል" ብሏል።

አክሎ ፥ "የትግራይን ህዝብ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር ለማናከስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪው ህወሀት በትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነው በዚሁ አካባቢ የትግራይን ህዝብ ከጎረቤቱ ጋር በማናከስ፣ ጉርብትና እንዲሻክርና ጎረቤቶችን በማጣላት የራሳቸውን እድሜ ለማራዘም አፋር እና ትግራይ ጎረቤት ህዝቦችን እያናከሰ ይገኛል" ሲል አሳውቋል።

ክልሉ፥ "ጎረቤታሞች በሰላም ውሎ እንዳያድር ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነው" የሚለው የአፋር ክልል" የትግራይ ህዝብም ይሄንን የጀንታውን እብደት ሊቃወም ይገባል፤ በቃቹህ ሊሉ ይገባል" ሲል አስገንዝቧል። ቡድኑ በንፁሀን የአፋር ህዝብ ላይ በተለይም በኪልበቲ ረሲ ዞን አብአላና መጋሌ በኩል የከፈተውን በጥብቅ ሊያወግዝ ይባልም ብሏል።

የአፋር ክልሉ መንግስት " ህወሓት በከባድ መሳሪያ ንፁሀንን የመግደል የመጨፍጨፍ ተግባሩን አሁንም አላቆመም፣በአፋር በኩል ጦርነቱ አልቆመም፣ ንፁሀን ሴት፣ ህፃናት እና አዛውንት አሁንም ሰለባ እየሆኑ ነው" ብሏል።

የዓለም ህብረተሰብ የህወሓትን ድርጊት እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርቧል።

ህወሓት ፥ በሚቆጣጠረው የትግራይ ቲቪ በኩል ባወጣው መግለጫ የአፋር ልዩ ኃይል በህዝባችን ላይ ተከታታይ ግፎችና ጭፍጨፋዎች እየፈፀመ ሰንብቷል ሲል ከሷል።

ያንብቡ : telegra.ph/Afar-Tigray-01-16

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር መሀመድ ሁሴን ሮቤል በሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ መሀመድ ኢብራሂም ሙአሊሙ ላይ ያነጣጠረውን አሰቃቂ ያሉትን የሽብር ጥቃት አወገዙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽብር ጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ቃል አቀባዩ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

ጠ/ሚ መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ፥ ለመሀመድ ኢብራሂም ሙአሊሙ ፈጣን ማገገምን ተመኝተዋል።

እስካሁን ለአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

@tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ድጋፍ ፦

አዲስ አበባ ከተማ ዛሬ እና ትላንት ለሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን በድምሩ የ150 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ አድርጋለች።

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ50 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ ተደርጓል።

በመጀመርያ ዙር 51 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በሁለት ዙር በአጠቃላይ 101 ሚሊዮን ብር የሚሆን ድጋፍ ማድረስ ተችሏል።

ትላንት ደግሞ በሶማሌ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ100 ሚሊዮን ብር የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።

ምንጭ፦ የአ/አ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ItsMyDam🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ ከታላቁ የኅዳሴ ግድብ በዓመት 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የኢትዮጵያ የኢኖቬስን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ደኤታ ሁሪያ አሊ ማህዲ አስታወቁ። ኢትዮጵያ በዚሁ ከመጀመሪያ ዙር እንደምታመነጭ ከሚጠበቀው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጠቃላይ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት…
#GERD🇪🇹

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዚህ ሳምንት በሰጡት መግለጫ ከተናገሩት ፦

(ከሪፖርተር)

" ... የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኤሌክተሪክ ማመንጨት የሚጀምርበትን ቀን ይህ ነው ብሎ መነገር ባይቻልም፣ በጣም በቅርብ ጊዜ ይጀምራል።

የግድቡ ጉዳይ ሊለወጥ የማይችልና ያለቀ ነገር በመሆኑ፣ የታችኛው ተፋሰስ አገሮች ከዚህ ካለቀ ጉዳይ ጋር አብረው መቆም አለባቸው።

ከዚህ በኋላ ግድቡ ሲያመነጭ ለግብፆችም ሆነ ለሱዳኖች ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ ፣ በሚመነጨው ኃይል ሌሎችም አገሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እነዚህ አገሮች ቢሠሩ መልካም ነው። ነገር ግን የሦስትዮሽ ድርድሩ ይቁም ማለት አይደለም።

ሱዳን እና ግብፅ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ከጀመራቸሁ ችግር ይፈጠራል፣ ሰማዩ ይገለባበጣል የሚሉት ነገር አዲስ አይደለም፡፡

ቀድሞውንም ሙሌት ከጀመራችሁ አደጋ ይፈጠራል፣ ጉድ ይፈላል ሲሉ ነበር ይህ ፉከራ የተለመደ ቢሆንም አሁን ግን ያረጀና ጊዜው ያለፈበት ሆኗል።

በህዳሴ ግድቡ ውኃው ተርባይኑን አንቀሳቅሶ አልፎ ስለሚሄድ መጠኑ ስለማይቀንስ፣ ሱዳኖች የግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመር ሊያስደስታቸው እና ሊያከብሩት ይገባል። "

@tikvahethiopia