TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ENDF

የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ ለህ/ተ/ም/ቤት እንዲላክ ተወሰነ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አሁን በሥራ ላይ ያለውን የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል።

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ውሳኔ ካሰለፈባቸው ጉዳዮች አንዱ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ ነው።

ምክር ቤቱ ፤ መከላከያ ሠራዊቱ የሪፎርም ስራ ውስጥ እንደሚገኝ አስታውሶ ይህን ሪፎርም የበለጠ ለማጎልበት እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ከመከላከያ ሠራዊቱ ወቅታዊ እና የወደፊት ግዳጆች ጋር የሚጣጣም የህግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ በሥራ ላይ ያለውን አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለም/ቤቱ መቅረቡን አመልክቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል #ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሙሉ ድምጽ እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

(የዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል)

@tikvahethiopia