#AddisAbaba
ትናንት ምሽት 5 ሰዓት ተኩል ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ወረዳ 7 ኢንዱስትሪ መንደር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሰብ በማሽን ተይዞ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።
እንደ አዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መረጃ ፤ ከሜድሮክ ድርጅቶች በአንዱ ውስጥ ሰራተኛ የሆነው ሟቹ ትናንት ምሽት አሸዋ በሚፈጭ ማሽን ላይ ስራውን እያከወነ በነበረበት ወቅት በማሽኑ ተይዞ ወዲያው ህይወቱ አልፏል።
አስከሬኑን ከማሽኑ ለማላቀቅ አልተቻለም ነበር፡፡
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን ከማሽኑ አላቀው ማውጣት የቻሉት ለ2 ሰዓት ከፈጀ ጥረት በኋላ ነው።
የትናንቱ በማሽን ላይ የደረሰው አደጋ ጉዳይ በህግ ተይዟል ተብሏል።
በሌላ በኩል ፤ ትላንት በሸገር ከተማ አሸዋ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወና ወሀ ባቆረ ጉድጓድ ውስጥ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አልፏል።
ሟቾቹ ዕድሜያቸዉ 19 እና 23 ነው።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አንደኛውን ወጣት አስክሬን አውጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን እድሜው 19 ዓመት የሆነው ወጣት አስክሬን የአካባቢው ህብረተሰብ አስቀድሞ አውጥተውታል።
ክፍት የተተወው ጉድጓድ ውሃ ያለበት በመሆኑ አንደኛው ግለሰብ ለመታጠብ ብሎ ገብቶ ተንሸራትቶ ወደ ውሃው ውስጥ ይገባል ፤ የዚህን ሰው መግባት የተመለከተው ሌላው ግለሰብ ደግሞ እርሱን ለማውጣት ሲል ወደ ጉድጓዱ በመግባቱ የሁለቱም ህይወት ወዲያው አልፏል፡፡
#ShegerFM102.1
@tikvahethiopia

😭2.67K😢214❤130🕊82😱64🙏41🥰13😡11🤔5
" ለውይይት በራችንን ከፍተን እየጠበቅን ነው " - ገቢዎች ቢሮ
" ቀን እና ቦታው ከተነገረን ህጋዊነታችንን የሚያረጋግጥ ዶክመንት ይዘን ለመነጋገር ዝግጁ ነን " - ማኅበራቱ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በኢትዮጵያ የሂሳብ እና የኦዲት ቦርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው 863 የሂሳብ ባለሙሞያዎችና ኦዲተሮች ያቀረቡት የሂሳብ ሪፖርት በማሳነስና በመሰወር የቀረበ ነው ሲል ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ፍቃድ መንጠቅ የደረሰ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል።
" የገቢ ግብርን በማሳነስና በመሰወር የተሳሳተ የሂሳብ ሪፖርት አቅርበውልኛል እርምጃ ይወሰድባቸው " ብሎ በሚዲያ ያስተላለፈው መረጃ የኦዲተርነት ሙያን ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ መክተቱን የሂሳብና የኦዲተሮች ማህበራት ተናግረዋል።
በቅርቡ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከወንኩት ባለው የቅድመ ኦዲት ስራ " ባለፈው ዓመት ብቻ 36,729 የታክስ መዝገቦች ገቢ በማሳነስና በመሰወር የሚቀርቡ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ " ብሏል።
በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሂሳብ እና የኦዲት ቦርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው 863 የሂሳብ ባለሙሞያዎችና ኦዲተሮች 824ቱ ባለሞያዎች ያቀረቡት የሂሳብ ሪፖርት በማሳነስና በመሰወር የቀረበ በመሆኑ፤ በቦርዱ ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ፍቃድ መንጠቅ የደረሰ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ቢሮው ጠይቋል።
ይህን ተከትሎ 3 የሂሳብና የኦዲተሮች ማኅበራት ተፈፀመ የተባለው ስህተት በቦርዱ ሳይረጋገጥ መረጃው በሚዲያ መተላለፉ አግባብነት የሌለውና ሙያውንም ኪሳራ ውስጥ የከተተ ነው ሲሉ መግለጫ አውጥተዋል።
በመግለጫቸውም " ባለሙያዎቹ ይቀጡልኝ " የሚለው ጥያቄ ላይ ምንም ቅሬታ እንደሌላቸው ጠቅሰው ይሁንና በሚዲያ የተላለፈበት አግባብ አሳሳች የነበረ በመሆኑ መረጃው ከሚዲያዎችና መረጃ ቋቶች ላይ እንዲወርድ ጠይቀዋል።
ይህንንኑ ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውንና በጉዳዩ ዙሪያ ለመነጋገር የገቢዎች ቢሮን በደብዳቤ መጠየቃቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ የሂሳብ አዋቂዎችና ኦዲተሮች ማህበር፣ የውጭ ኦዲተሮች ማህበርና የአካውንቲንግ ሶሳይቲ ኦፍ ኢትዮጵያ ማህበር ናቸው።
በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ምን ምላሽ ሰጠ ?
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለውይይት ለመቀመጥ የማህበራቱን ህጋዊ እውቅና እና የአባላት ዝርዝር በህጋዊ መንገድ እንዲቀርብለት ጠይቋል።
የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ሰውነት አየለ ለማኅበራቱ አመራሮች በስልክ በመደወል ህጋዊ እውቅናቸውን እንዲያቀርቡ ነግረናል ያሉ ሲሆን ለውይይት በራችንን ከፍተን እየጠበቅን ነው ሲሉ ለሸገር ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
ቢሮው 863 የሂሳብ ባለሙያዎች ይቀጡልኝ ሲል ለኢትዮጵያ የሂሳብና የኦዲት ቦርድ ማቅረቡን ተከትሎ በሚዲያ የወጣው መግለጫ በተመለከተ፥ አቶ ሰውነት በስም ዝርዝር የተነሳ የለም በማለት የተሰራው ስራ በአዋጅ በተቀመጠው መሰረት እንደሆነ አስረድተዋል።
አክለውም " እስካሁን በስም ዝርዝር ያወጣነው ነገር የለም ያሉ ሲሆን 490 የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጥልን 333 ደግሞ ፈቃዳቸው ይሰረዝ 39ኙ እውቅና ይሰጣቸው ያልነው በደፈናው ነው " ብለዋል።
ማጣራቱ ከተጠናቀቀ እና ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በስም ዝርዝር ይፋ እንደሚደረግም አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል።
ማኅበራቱ በቢሮው ምላሽ ላይ የሚያነሱት ጥያቄ ምንድነው ?
ማኅበራቱ " በደብዳቤ ለጠየቅነው ጥያቄ በደብዳቤ ምላሽ አልተሰጠንም " ያሉ ሲሆን በስልክ ቅድመ ሁኔታውን እንዲያሟሉ እንደተነገራቸው እና መቼ እንደሚወያዩ ቀጠሮ እንዳልተሰጣቸው ለሸገር ኤፍ ኤም ገልፀዋል።
የውጪ ኦዲተሮች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ማሞ ለሁለቱ ማህበራት ፕሬዚዳንቶች " እውቅናን እና የአባላትን ዝርዝር በህጋዊ መንገድ አረጋግጣችሁ አምጡ " የሚል ቅድመ ሁኔታ በስልክ እንደተነገራቸው አረጋግጠዋል።
የማህበራቱን እውቅና ማረጋገጫ ማቅረብ እንደሚቻል " የማህበራቱን አባላት ዝርዝር ግን ይዞ መቅረብ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘነውም " ብለዋል።
በተጨማሪ አቶ ሚሊዮን " ' ህጋዊነታችሁን የሚያረጋግጥ ዶክመንት በዚህ ቀን ይዛችሁ ኑ እና እንወያይ ' የሚል ሃሳብ አልተሰጠም " ያሉ ሲሆን " በደብዳቤም በፅሁፍም ምንም ነገር አልተባለም " ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ሚሊዮን፥ ቀን እና ቦታው ከተነገራቸው ማኅበራቱ ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ዶክመንት ይዘው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

❤147🤔28🕊15😭14😡12🙏8🥰7😱4😢4
" ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አነስተኛ ሆኖ እያለ ከፍተኛ የገቢ ግብር ስለሚቆረጥባቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንዳያሟሉ ሆነዋል " - ኢሰማኮ
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵዊያን ሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ አሳሳቢነቱ ቀጥሏል ሲል አሳውቋል።
ኮንፌዴሬሽኑ ይህን ያለው በመጪው ሀሙስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ136ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀንን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
ኢሰማኮ " የዋጋ ግሽበት የደመወዝ ተከፋዩን የመግዛት አቅም በእጅጉ እንዳዳከመው ነው " ብሏል፡፡
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እስካሁን አለመወሰኑን ያስታወሰው ኮንፌዴሬሽኑ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አነስተኛ ሆኖ እያለ ከፍተኛ የገቢ ግብር ስለሚቆረጥባቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንዳያሟሉ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ " አንዳንድ አሰሪዎች፣ የማህበር መሪዎች ለአባሎቻቸው ስለቆሙ ወይም ለአባሎቻቸው መብት ስለተከራከሩ ብቻ ከስራ ይባረራሉ፣ ይዋከባሉ ወይም ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ " ብለዋል፡፡
" ኑሮ የከበዳቸውን ተቀጣሪ ሰራተኞችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላኩ ጥያቄዎችን በተመለከተ በተደረገው ውይይት ጥያቄያችን ተቀባይነት አግኝቶ ለሚመለከታቸው ሚኒስትሮች ተላልፎ ተሰጥቷቸዋል ፤ ሆኖም የተወሰኑ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ቢሆንም መሰረታዊና ቁልፍ የሆኑ የሰራተኛ ጥያቄዎች አልተመለሱም " ሲሉም ገልጸዋል።

👏1.14K❤130😭84😢56🙏51🕊21💔15🥰12😡10