TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ET302

መጋቢት 1/2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች የፊታችን ማክሰኞ እዚሁ ሀገራችን ላይ በሚደረግ የመታሰቢያ መርሐ-ግብር ለመታደም ይሰባሰባሉ ተብሏል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሌላ መረጃ፦

የዮርዳኖስ ንጉስ አብደላ 2ኛ በኅዳሴ ግድብ ድርድር ግብጽን እንደምትደግፍ ለሳሜሕ ሽኩሪ እንደነገሯቸው የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። አብደል ፋታሕ አል–ሲሲ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አብደል ፋታሕ አል–ቡርሐን በስልክ ተነጋግረዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ዛሬ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከተቋቋመ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።

በውይይቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ቢገባ የካ ኮተቤ ሆስፒታል ሌሎች ሥራዎች አቁሞ ሕክምና እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ዶክተር ሊያ «በዚህ ሆስፒታል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ባለሙያዎችን በማሰልጠን ሥራዎች እየተሰሩ ነው» ብለዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥቂት ስለ ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሒ፦

ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሒ 'ነበድ' የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለቤት ናቸው። ከሚኖሩበት ብሪታኒያ የተመለሱት በቅርብ ሲሆን ባለፈው ወር የሰላም ሚኒስቴር "የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም አምባሳደር" ብሏቸዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲሱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነር!

አቶ ፀጋ አራጌ የሥነ–ምግባርና ጸረ–ሙስና ኮሚሽነር ሆነው ዛሬ ጥዋት ተሹመዋል። ሹመታቸው 11 ተቃውሞ 6 ድምጸ ተዓቅቦ ገጥሞታል። የሰሜን ወሎ አስተዳዳሪ፣ የአማራ ከልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ ነበሩ።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA

በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋጠ ሰዎች 6ኛዋ የብሪታኒያ ኤምባሲ ባልደረባ መሆናቸውን አምባሳደር አላስቴር ማክፊል አረጋግጠዋል። የኤምባሲው ባልደረቦች መረጃው እንደደረሳቸው ለጤና ሚኒስቴር ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

#EsheteBekele #UKinEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወደ አፍሪካ እና በማደግ ላይ ያሉ አገሮች እየገሰገሰ ነው። የጤና አግልጋሎቶቻቸው በጣም ደካማ ናቸው። ካደገው ዓለም ጠንካራ ድጋፍ ይሻሉ። ያን ድጋፍ ከተከለከሉ አደገኛ ጣጣ ይገጥመናል። አገሮች አቅም ሳይኖራቸው ቀርቶ ቫይረሱ [COVID-19] በቁጥጥር ሥር ሳይውል ከቀረ እንደ ሰደድ እሳት ሊዛመት ይችላል። በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ሊሞቱ ይችላሉ" - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የሆኑት የማነ ገብረመስቀል በኤርትራ በኮሮና ተሕዋሲ መያዙ የተረጋገጠ የመጀመሪያው ሰው መገኘቱን አሳውቀዋል። ቫይረሱ የተገኘበት በዱባይ አየር መንገድ ዛሬ ከኖርዌይ ወደ አስመራ የተጓዘ የ39 አመት ጎልማሳ ላይ ነው።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ቴድሮስ ድንቅ ስብዕና ያለው ሰው ነው። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ሳለ ጀምሮ አውቀዋለሁ። የዓለም ጤና ድርጅት ችግሮች የሉበትም የሚል ካለ ድርጅቱን አይከታተልም ነበር ማለት ነው። በእርሱ አመራር ጥሩ ሰርተዋል" - ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HumanRightsWatch

በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ወቅት ይሁነኝ ብሎ ኢንተርኔት ማቋረጥ አሊያም መገደብ ገዳይ ሊሆን ይችላል ሲል ሒዩማን ራይትስ ዎች አስጠነቀቀ። ድርጊቱ በርካታ መብቶችን ይጥሳል ብሏል። እነ ኢትዮጵያ ሕይወት ለማዳን በአፋጣኝ አገልግሎቱን እንዲመልሱ ጠይቋል።

ሒዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው ኢትዮጵያ ፣ ባንግላዴሽ ፣ ሕንድ እና ምያንማር የኢንተርኔት ግልጋሎት ያቋረጡ ናቸው። በኢትዮጵያ በወለጋና ጉጂ ዞኖች የተቋረጠው ኢንተርኔት እና ስልክ ሥራ እንዲጀምር የጤና ባለሙያዎችና ፓርቲዎች ጭምር እየጠየቁ እንዳለ ይታወቃል።

https://www.hrw.org/news/2020/03/31/end-internet-shutdowns-manage-covid-19

#EsheteBekele Pic : #BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia