TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Alert‼️

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢው የጥበቃና ደህንነት አሠራር ላይ ያላቸው ከፍተኛ #ተቃውሞ ከምሽቱ 4:30 አንስቶ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

በተለይም የተቋሙ ሴት ተማሪዎች፦ መብታቸው እንዲከበር፤ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፤ በግቢ ውስጥ የሚፈፀሙ ዝርፊያዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

🔹በሌላ በኩል የተቋሙ ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ከሚፈፀሙ ዝርፊያዎች በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው አካባቢ ያለው ዝርፊያ መንግስት በአስቸኳይ እንዲያስቆም እና ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

▫️በአሁን ሰዓት #የሀገር_መከላከያ_ሰራዊት እና #ፌደራል_ፖሊስ ወደ ዩኒቨርሲቲው በመግባት ተማሪዎችን ለማረጋጋት እና ለማነጋገር እየጣሩ ይገኛሉ። ከተማሪዎች እንደሰማነውም በነገው ዕለት ተማሪው የሚካፈልበት ስብሰባ ተጠርቷል።

ምንጭ፦በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tukvahethiopia
ትኩረት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል #መተከል አካባቢ ለሚገኙ የሀገራችን ዜጎች‼️ #ኢትዮጵያ #ETHIOPIA #ቤንሻንጉል

#መከላከያ_ሰራዊት
#ፌደራል_ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፌደራል_ፖሊስ

ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን በህገ ወጥ መልኩ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፋይናንስ ወንጀል ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው ለኤፍ ቢ ሲ እንደተናገሩት፥ ገንዘቦቹ በተለያየ ጊዜና በተለያየ ቦታ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ በጉምሩክ ኮሚሽንና በፌደራል ፖሊስ የተያዙ ናቸው። ከዚህ ውስጥ 2 ሚሊየን 486 ሺህ 500 የአሜሪካ ዶላር፣ 55 ሺህ 664 ፓውንድ፣ 25 ሺህ 670 የካናዳ ዶላር፣ 8 ሺህ 800 የአውስትራሊያ ዶላር፣ 19 ሺህ 700 ድርሃም፣ 18 ሺህ 390 ሪያል እና 24 የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦች መያዛቸውንም ተናግረዋል። ግለሰቦቹ ጉዳያቸው በምርመራ አልቆ በፍርድ ቤቱ መያዙንም ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፌደራል_ፖሊስ

"በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኮልፌ ካምፕ ፌደራል ወንጀል መከላከል አሻራቸውን በእንዲ መልኩ አሳርፈዋል። እጅግ ሚበረታታ ነው!" #ዊንታ