TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አሜሪካ #ቪዛ

" አንዳንድ ተጓዦች የቪዛ ቃለመጠይቅ ቀጠሮ ለማግኘት ከ6 ወር እስከ አንድ ዓመት ድረስ ይፈጅባቸዋል "

ለጉብኝት ፣ ለሥራ ወይም ለመኖር ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ የሚጠይቁ አመልካቾች ከ1994ቱ የሽብር ጥቃት ወዲህ " እጅግ የተራዘመ " ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው ሰሞኑን ከወጡ የሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መረጃዎች እንደሆነ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

አንዳንድ ዓለምአቀፍ ተጓዦች የቪዛ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ለማግኘት ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት እንደሚፈጅባቸው ተናግረዋል።

በካቶ ኢንስቲትዩት የስደተኞች ፖሊሲ ኃላፊ ዴቪድ ቤየር ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል፤ " በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲዎች ለ2 ዓመታት መዘጋታቸውና ቪዛ ‘መስጠት ማቆማቸው የፈጠረው ችግር ነው’ " ብለዋል።

“ በወረርሽኙ ምክንያት የተከማቸ ሥራ አለ፤ ከአንድ ዓመት በላይ ቀጠሮ ያስፈለገውም ለዚሁ ነው ” ሲሉ አክለዋል።

የቀጠሮ ርዝመት ከኤምባሲ ኤምባሲ ቢለያይም ‘አሁን ያለው ሁኔታ ግን ከ1994ቱ የሽብር ጥቃት ወዲህ የከፋ ነው’ ሲሉ ቤየር ገልፀዋል።

ከጥቃቱ ሁለት ዓመታት በኋላ ጉዳይ ለማስፈፀም የሚወስደው ጊዜ ሦስት ሳምንት ያህል እንደነበር አንድ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ በወቅቱ ለአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተናግረው ነበር።

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ሠንጠረዥ እንደሚያሳየው ለአንዳንድ ቪዛ አመልካቾች ቃለ መጠይቅ ለማደረግ ከ1 ዓመት በላይ ሲወስድ የንግድና የጉብኝት ቪዛ አመልካቾች ደግሞ ከ6 ወራት በላይ እንደሚጠብቁ ተገልጿል።

አሜሪካ ለ40 ሃገሮች ተጓዦች ያለ ቪዛ ገብተው ለዘጠና ቀናት እንዲቆዩ እንደምትፈቅድ የአሜሪካ ሬድዮ ጣቢያ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia