TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶክተር ደብረፅዮን‼️

የሀበሻ ወግ መፅሄት በህዳር እትሙ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ምእራብ ትግራይን ሲጎበኙ "ከአማራዎች ይልቅ #ሱዳኖች ይሻሉናል" ብለው ተናገሩ ብሎ ይዞ የወጣውን ዘገባ #እውነትነት ለማጣራት የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ #ሊያ_ካሳ ጋር የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ስልክ ደውሎ ነበር። እሷ እንዳለችው ዶ/ር ደብረፅዮን በፍፁም እንደዛ እንዳላሉ እና ንግግሩ ከየት እንደተወሰደ እንደማታውቅ ገልፃለች። አክላም: "የትግራይ ህዝብ ከአማራው፣ የአማራ ህዝብ ደግሞ ከትግራዩ ምን ያህል #የማይነጣጠል ህዝብ እንደሆነ ህዝቡ እራሱ በደንብ ያውቀዋል። ይህ ሆን ተብሎ #ለመነጣጠል የሚደረግ ጥረት እና የሚፈበረክ #ወሬ እንጂ የተባለ ነገር አይደለም። ምእራብ ትግራይ ዶ/ር ደብረፅዮን የሄደበት ግዜ ይታወቃል እናም የተናገረውም ይታወቃል። እንደዚህ አይነት ነገር ጭራሽ አላነሳም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia