TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች...

ዛሬ ጥዋት የሀዋሳ ከተማ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በከተማው የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙን ሪፖርት አድርገዋል።

ላለፉት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ነዳጅ ለማግኘት ፈተና ሆኗል፤ በከተማው ረጃጅም የሞተር እና የመኪና ሰልፎች አሉ ብለዋል።

ነዳጅ ለማግኘት መጉላላት እና የስራ መስተጓጎል የየእለት የህይወታችን አንዱ ክፍል ከሆነም ሰንብቷል ሲሉ አማረዋል።

በተመሳሳይ ነዳጅ ለማግኘት በመሰለፍ በሚያጠፉት ጊዜ በአማካይ እስከ 150 ብር እንደሚያጡ በባሕር ዳር አብመድ ያነጋገራቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች ገልፀዋል፡፡

እናተስ የት ከተማ ይህ ችግር አጋጠማችሁ?

#AMMA #TikvahFamilyHawassa
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደመወዝ ➡️ " አሁን ላይ ከኑሮ ወድነቱ ጋር ተደምሮ የደመወዝ መዘግየት እየፈተነን ይገኛል " - ሰራተኞች ➡️ " ችግሩ ይቆያል የሚል እምነት የለኝም " - የድርጅቱ አመራር ደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በበጀት ምክኒያት መፈተን ከጀመረ እንደቆየ የድርጅቱ ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። በዚህም ምክኒያት " ደሞዝ እየዘገዪ ተቸግረናል " የሚሉት ሰራተኞቹ " በ28 ሲገባ የነበረዉ ደሞዛችን…
" ... ደመወዛችን እየዘገየ መከፈሉን ተከትሎ መስራትም መኖርም አልቻልንም " - የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ሰራተኞች

የቀድሞዉ ደቡብ ክልል መበተኑን ተከትሎ በአራቱ ክልልሎች ማለትም፦
- በሲዳማ
- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
- በደቡብና
- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጀት እንዲተዳደር ፤ በክልሎች ፈቃደኝነት እና በመንግስት አቅጣጫ ተቀምጦለት ሁሉንም ክልሎች እንዲያገለግል ተወስኖ ስራዉን የቀጠለዉ የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሰራተኞቹን ደሞዝ በሰአቱ መክፈል እየቻለ እንዳልሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

በዚህ ወርም እንዳለፈዉ ወር የሰራተኛዉ ደሞዝ ዘግይቶ ከ12 ቀናት በኃላ ነው የተከፈለው።

የሰራተኞች ደመወዝ ዛሬ ከሰዓት ነው ያገባው።

ደመወዝ እየዘገየ በመከፈሉ የድርጅቱ ሰራተኞች አደጋ ላይ መውደቃቸዉንና ህይወታቸዉ እየተመሰቃቀለ መሆኑን  በመግለጽ  ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" አሁን ላይ ድርጅቱ የሰራተኛዉን ደሞዝ እያዘገየ ከመክፈሉ በተጨማሪ የስርጭት መቆራረጥና የሎጅስቲክስ ችግሮች እየተመለከትን ነው ፤ " የሚሉት የድርጅቱ ሰራተኞች " አመራሩ ስለችግሩ ሊያወያየን ይገባ ነበር " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ባደረገዉ ማጣራት የተከሰተዉ የደሞዝ መቋረጥ ፣ የስራ ማስኬጃ ጉድለትና የስርጭት መቆራረጥ ያመጣው የገንዘብ ችግር  ምክንያቱ ክልሎች የፈቀዱትን በጀት በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች ምክንያት መልቀቅ ባለመቻላቸዉ ነው።

ችግሩን ለመቅረፍ ድርጅቱ ከክልል አመራሮች ጋር ንግግር እያደረገ " ተስፋ የሚጣልበት መግባባት " ላይ መድረሱ ታውቋል።

ይሁንና ከሌሎች ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የተፈቀደዉ በጀት በአግባቡ እንደሚለቀቅ ቢገለጽም በሲዳማ በኩል አሁንም ምላሽ አልተገኘም።

የሲዳማ ክልል የድርጅቱ መቀመጫ እና መስራች ሆኖ ሳለ ስለምን ዝምታን መረጠ ? በማለት ለክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ተጠሪ አቶ አብርሀም ማርሻሎም ሆነ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሀላፊ የሆኑትን ዶክተር አራርሶን ገረመዉን ለማናገር የተደረገዉ ጥረት ሊሳካ አልቻለም።

#TikvahFamilyHawassa

@tikvahethiopia