TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አማራ ክልል‼️

የአማራ ክልል ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ነቅተው በመጠበቅ በሃገሪቱ ለተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ #ስኬታማነት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አስገነዘቡ።

የቢሮው ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል #አሳምነው__ጽጌ ትናንት ከወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለፁት በአገሪቱ ለተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ስኬታማነት የወጣቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡

ባለፉት ዓመታት አማራው በክልሉ ውስጥም ሆነ በሌሎች ክልሎች ማንነቱን መሰረት ያደረጉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሲፈፀሙበት መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ሊያረጋግጥ የሚችል የለውጥ ብርሃን እየታየ ቢሆንም ጥቅማቸው የተነካባቸው አካላት ለውጡን ወደ ኋላ ለመመለስ እየተንቀሳሱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

Via~አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia