TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
#Tigray

" በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ ነው " - ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

ዛሬ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ክልል ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን አሳውቀዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ የፌዴራል መንግስት ህወሓትን ከሽብርተኝነት ፍረጃ መሰረዙ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ፕሬዜዳንትነት የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ትግበራ ለመግባት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ስለመግለፃቸው ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ህወሓት ከሽብርተኝነት መዝገብ ስለመሰረዙ ምን አሉ ?

" በዛሬው ዕለት ህወሓት ከሽብር መዝገብ ተሰርዟል። ስለሆነም ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራው የሚጀምርበት ሁኔታ ተሟልቷል።

#በጀት የማዘጋጀትም ይሁን ሌሎች #ከእስረኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የወንጀል ክሶችን በማንሳት እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በሁለቱም ወገን በኩል ግኝኑነት ተጀምሯል።

በመሆኑም በበኩላችን በጓድ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራዎቹ እንዲሳኩ ለማድረግ ሁሉንም አቅማችንን በማቀናጀት ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን።

የትግራይ ህዝብም በሁሉም አቅሙ የጊዜያዊ አስተዳደራችን ደግፎ እንዲሰማራ ጥሪ እናቀርባለን። "

ዶ/ር ደብረፅዮን ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምን አሉ ?

" የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፋጠን አሸባሪነት የሚለው ሳይነሳ ቀድመን ነው እየሰራን የመጣነው። ጊዜያዊ መንግስቱን ለማቋቋም በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መምጣታቸውን ሁሉም ሲከታተለው የነበረ ጉዳይ ነው።

ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ ሁሉም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በተመለከተ አጀንዳው አድርጎ እንዲሰራ በውስጥም በውጭም መድረኮችን በማዘጋጀት ተሰርቷል።

ኮንፈረንስ በማዘጋጀት እና ከኮንፈረስን በኃላ ምርጫዎችን በማካሄድ ሊያካትታቸው የሚገባ ፈፃሚ አካላት እንዲመረጡ ተደርጓል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ #ህወሓት እና #ባይቶና ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ሰራዊት ፣ የትግራይ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚሳተፉ አካላት ተሟልተን ለማዕከላዊ መንግስቱ አሳውቀናል። "

ዶ/ር ደብረፅዮን #ህወሓትን በተመለከተ ምን አሉ ?

" ድርጅታችን ህወሓት የትግራይ ግዛታዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ሰላም የሰፈነባትና ብሔራዊ ክብሯ የተጠበቀች ትግራይን ለመገንባት ሁሉንም አቅሙን በማቀናጀት የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚታገልበት ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!! "

@tikvahethiopia
#ባይቶና

ቦርዱ ባይቶና መስራች ጉባኤ እንዲየከናውን ወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፤ የብሔራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ፓርቲ አደራጅ ኮሚቴ ዐዋጁን መሠረት በማድረግ የመሥራች ጉባዔውን እንዲያከናውን ውሳኔ አሳልፏል።

ቦርዱ ፤ ዛሬ ለነ ኪዳነ አመነ በላከው ደብዳቤ ፓርቲው ጥቅምት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ያደረገው የመስራች ጉባኤ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተቀመጡትን መስፈርቶች በማሟላት የተከናወነ ባለመሆኑ በጉባኤ የተከናወኑ የአመራር ምርጫም ሆነ የፀደቁ ሰነዶችን እውቅና ያልሰጠ መሆኑን አሳውቋል።

ምርጫ ቦርድ፤ የፓርቲው አደራጅ ኮሚቴ አዋጁን መሰረት በማድረግ የመስራች ጉባኤውን እንዲያከናውን ወስኗል።

(ይህ ውሳኔ የተላለፈበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ባይቶና

በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው  "ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የተባለ የፓለቲካ ድርጅት ሙሉ እውቅና ማግኘቱ አስታውቋል።

በእነ ዶ/ር ፀጋዛኣብ ካሕሱ ከሚመራው " ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የፓለቲካ ደርጅት ተነጥሎ የወጣው ባይቶና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሙሉ እውቅና ማግኘቱን ገልጿል።

በእነ ክብሮም በርሀ እና ኪዳነ ኣመነ የሚመራው  " ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) " የፓለቲካ ፓርቲ ጥር 22/2016 ዓ.ም ባሰራጨው መረጃ እንዳመለከተው ፤ ከጥቅምት 17 - 18 / 2016 ዓ.ም መስራች ጉባኤ ማካሄዱ አስታውሶ " ከብዙ ውጣ ውረድ ሁሉም መስፈርቶች በሟሟላት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሙሉ እውቅና አግኝቻለሁ " ብሏል።

ድርጅቱ ለሁሉም አመራሮቹ ፣ ለአባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ለመላው የትግራይ ህዝብና የትግል አጋሮቼ ላላቸው የአንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ማስተላለፉ የዘገበው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                          
@tikvahethiopia            
#ባይቶና

" በትግራይ ያጋጠመው ፓለቲካዊ ብልሽት የሚያጠራ ብሄራዊ እርቅ ያስፈልጋል " - ባይቶና ፓርቲ 

ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የፓለቲካ ፓርቲ በክልሉ ወቅታዊ የፓለቲካ ሁኔታ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ " በትግራይ ያጋጠመው ፓለቲካዊ ብልሽት የሚፈታ ብሄራዊ የእርቅ ምክር ቤት ያስፈልጋል " ብሏል።

ብሄራዊ የዕርቅ ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲቋቋም የጠየቁት የባይቶና ፓርቲ ሊቀመንበር ክብሮም በርሀ ፥ ምክር ቤቱን የማቋቋም ሃላፊነት ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ይሰጥ ብሏል። 

የትግራይ ጥቅም የሚያረጋግጥ ብሄራዊ ዕርቅ ማካሄድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የገለፁት ሊቀመንበሩ እርቅ ሲባል በልሂቃን መካከል የሚፈፀም እንደሆነ  አብራርተዋል። 

" የተፈጠረው መገፋፋት የትግራይ ብሄራዊ ጥቅም ወደ አደጋ እያስገባው ነው " ያሉት አቶ ክብሮም " ከመጠፋፋት ፓለቲካ ወጥተን የሰለጠነ ፓለቲካ ማራመድ አለብን " በማለት ተናግረዋል። 

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ የአንድ ቡድን ሳይሆን የጀግኖች ደም ባረጋገጠው የፕሪቶሪያ ስምምነት እውቅና ያለው ነው " ያሉት አቶ ክብሮም " ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንዳሻን የምንገነባውና የምናፈርሰው ሳይሆን ፀጋዎቹን አሟጠን በመጠቀም የህዝባችን ድህንነት ማረጋገጠረ አለብን ' ማለታቸው ቲክሻህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል። 

@tikvahethiopia