TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢትዮጵያ ከፍላዋለች ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አክብሮታል " - ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ

በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ እህት የሆነችው ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ አሁን ላይ በስደት #በካናዳ_ሀገር የምትገኝ ሲሆን የወንድሟን ህልፈት በሰማችበት ወቅት እራሷን ስታ ሆስፒታል እንደነበረች ተናግራለች።

ድምፃዊት ትዕግስት ፤ የወንድሟን ህልፈት ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ላሳየው ልዩ ክብር ምስጋናዋን አቅርባለች።

ወንድሟን እስላም ፣ ክርስቲያኑ ፤ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ ፣ አማራው አንድም ሳይለያይ አልቆሶ በክብር መቀበሩን የገለፀችው ትዕግስት ባየችው ነገር እንደተፅናናች ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ እየጠፋ ያለው የሰው ህይወት ይቆም ዘንድና ሁሉም ወደ ፍቅር እንዲመለስ እያለቀሰች ተማፅናለች።

ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ ፦

" ... ወንድሜን ኢትዮጵያ ከፍላዋለች። እግዚአብሔር ይመስገን የኢትዮጵያ ህዝብ አክብሮታል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት አክብሮታል።

እንደ ንጉስ በክብር ተቀብሯል።

ፌንት አድርጌ ሆስፒታል ነበርኩኝ ፤ ወንድሜ ለኔ ልጄ ነው ፤ የስደት ጓዴ ነው፤ ሁሉ ነገሬ ነው። የጀግና ሞት ነው የሞተው፤ እንደ ንጉስ ነው የተቀበረው።

የማስተላልፈው መልዕክት ፤ ወንድሜ እንዲሁ እንደ ንጉስ እንደተቀበረ  ፤ #ኢትዮጵያን እንዳለ እንደዘፈነ ፤ ኢትዮጵያን እንደወደደ የክብር ሞት ነው የሞተው የኢትዮጵያ ህዝብም ብድሩን መልሶለታል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ፤ ኢትዮጵያን ሰላም ያድርጋት።

ነገር ግን አንድ የሚያመኝ ነገር ወንድሜ እንዲህ እንደ ንጉስ ተከብሮ ተቀብሮ እንዲህ አንጀቴ ፣ ልቤ የተቆረጠ ፤ የሚያልቀው ህዝብ ፣ ምንም በማያውቀው ፣ ደጉ ባለሀገሩ ፣ ምስኪኑ የሚጨፈጨፈውስ ... ስለነሱ ነው መልዕክቴ።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደድሯችን #አንድ ልንሆን ይገባል፤ ሞት ሊቆም ይገባል። እኔ ወንድሜ በክብር ተቀብሮ እንደዚህ ያመመኝ ተዋግቶ በማያውቀው ተጋድሎ የሚሞተው ህዝብ ፤ ለእሱ ህዝብ ሞት ሊቆም ይገባል ነው መልዕክቴ።

ወንድሜማ እንደ ንጉስ ነው የተቀበረው ግን እንደዛም ሆኖ አንጀቴ ተቆርጧል። ማዲንጎ ኢትዮጵያን ነው ያሳየው እስላም፣ ክርስቲያኑ ፤ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ ፣ አማራው ሁሉ አልቅሶ ነው የቀበረው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግ ህዝብ ነው።

እባካችሁ ወገኖቼ ፣ ወንድሜ እንዲህ በክብር ተቀብሮ እንኳን አዝኛለሁ አንጀቴ ተቆርጧል፤ እያየች ልጇ የሚገደልባት እናት አባት ፣ እህት ወንድም የሚያልቅው እባካችሁ ... እባካችሁ ሞት ይቁም ኢትዮጵያ ላይ ፤ እግዚአብሔርን አምላክን ፍሩ ፤ ሁላችንም እንፍራ ወደ ፍቅር እንምጣ።

ማዲንጎ ይጠበቃል ዱብእዳ ነው የሆነብኝ፤ ቀኝ እጄ ነው የተቆረጠው ... በሰው ሀገር ፌንት ነው ያደረኩት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ አፅናናኝ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እንደዛ ሲሆንለት ሳይ ፣ ህዝቡ እንደዛ ሲወጣ አንድ አደረጋት ፣ #አንድ_ናት_ኢትዮጵያ እያለ ዘፍኖ ቀብሩ ላይ እስላም ፤ ክርስቲያን ሳይል ሁሉም አንድ ሆኖ ኦሮሞው ፣ ትግራዩ አንድ ሆኖ ነው አልቅሶ የቀበረው እናም ይሄ ህዝብ ፍቅር ነው የሚያስፈልገው ፤ ለእሱ ስንል መታሰቢያነቱ ለወንድሜ ይሁን አንድ ያድርገን እባካችሁ ፤ #ሞት_ይብቃን !! "

(ድምፃዊት ትዕግስት አፈወርቅ ፤ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ላይ ለሚሰራጨው " ታዲያስ አዲስ " ለተሰኘው የሬድዮ ዝግጅት ከሰጠችው ቃል የተወሰደ)

@tikvahethiopia