TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን በአብለጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ በ13 ተቃውሞ እና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የጸደቀው። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የፀደቀው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ማሻሻያዎች ተደረገበት ?

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚ አዋጅ በዛሬው ዕለት በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

የኮሚሽኑን መሪዎች በመሰየሙ ሂደት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ እጃቸው እንዳይገባ ሆኖ ነው የኮሚሽኑ የማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀው።

አገራዊ መግባባትን ለማምጣት ተከታታይ ምክክሮችን በማዘጋጀት እንዲሰራ ስልጣን የተሰጠውን ኮሚሽን የሚመሩ ኮሚሽነሮችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መርጠው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው እንዲያሾሙ በረቂቅ አዋጁ ተደንግጎ ነበር፡፡

ይህም የኮሚሽነሮችን #ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባል የሚል ተደጋጋሚ ትችት ሲዘነዘር ቆይቷል፡፡

በዚህም ምክንያት ረቂቅ አዋጁን ሲመረምር የቆየው ቋሚ ኮሚቴ ማሻሻያ እንደተደረገበት ተገልጿል።

በፀደቀው አዋጅ መሰረት እጩ ኮሚሽነሮችን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች እና ከሲቪክ ማህበራት ጥቆማ ይቀበላል ይላል፡፡

ጽኅፈት ቤቱ ጥቆማውን ከሰበሰበ በኋላ 14 የእጩዎች ዝርዝር ለይቶ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል።

ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እጩ ኮሚሽነሮችን በተመለከተ ውይይት ካደረጉ በኋላ ከ14ቱ 11ዱን መርጠው ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀድቃሉ ተብሏል።

ለኮሚሽኑ ደንብ እንዲያወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በረቂቅ አዋጁ ስልጣን ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ተሰርዞ ደንቡን የማውጣት ሥልጣን የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር እንዲሆን መደረጉም ታውቋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤፍም 102.1 ሬድዮ

@tikvahethiopia