TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከኤሊ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በዓል አክብሮ የሚመለስ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከሪካሪ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

ዛሬ ዓመታዊውን የኤሊ ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ አክብረው ወደ ገረሴ ወረዳ በመመለስ ላይ የነበሩ አንጋሾችን ያሳፈረ ኤፍ ኤስ አር የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶቢስ ' ሞርካ ቀበሌ ' ላይ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለሕክምና ተልከዋል።

ምንጭ፦ የጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#UPDATE😷

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦

🇪🇸 በሰሜን ስፔን የሚገኙ በርካታ ክልሎች የኮሮና ወረርሽኝን ለመዋጋት የምሽት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ጥለዋል። የአስቱሪያስ እና የካንታብሪያ መንግስታት የምሽት ክለቦች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ያደረጉ ሲሆን አራጎን እና ናቫራ ደግሞ ባርና ሬስቶራንቶች ከእኩለ ሌሊት በኋላ በራቸው እንዲዘጋ አድርገዋል።

🇲🇾 ማሌዥያ ከኦሚክሮን ጋር በተያያዘ በስምንት የደ/ አፍሪካ አካባቢ ሀገራት ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አንስታለች። ከ8ቱ ሀገራት ደ/አፍሪካ፣ ዚምባብዌ፣ ሞዛንቢክና ማላዊ ያሉበት ሲሆን እገዳው የተነሳላቸው ሀገራት ከፍተኛ ተጋላጭ ተብለው ከተለዩት ውስጥ እንደሚቀጥሉ ተነግሯል።

🇨🇳 የኮቪድ-19 ስርጭት ለመቆጣጠር በቻይና ያንያን ከተማ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ትዕዛዝ ተላልፏል። በሌላኛዋ ከተማ ዢያን የተጣለው ሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ዛሬ 8ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን የ13 ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ የሆነችው ዢያን ከእንቅስቃሴ ውጭ ሆና ጭር ብላለች።

🇪🇹 የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ህብረተሰቡ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚመከሩ መከላከያ መንገዶችን ችላ በማለቱና ከፍተኛ መዘናጋት ውስጥ በመግባቱ በአሁኑ ጊዜ ወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረው ይህ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ህብረተሰቡ በኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ዙሪያ ግንዛቤውን እንዲያሳድግና ክትባቱን ጨምሮ ሌሎች የጥንቃቄ መንገዶችን እንዲያከብር ጠይቀዋል።

🇺🇸 የአሜሪካ የጤና ባለሥልጣናት ለኮሮና ቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች ራሳቸውን አግልለው የሚቆዩበት ጊዜ ከ10 ቀን ወደ 5 ቀን ማጠሩን አስታውቀዋል። ከ5 ቀን በኋላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛቸውን በማድረግ ወደህብረተሰቡ ተመልሰው መቀላቀል ይችላሉ ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia : አጫጭር መረጃዎች፦

- በአማራ ክልል ከውጭ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እየተደረገ ያለው ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ለኢዜአ አሳውቋል። ቢሮው እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ በአዲስ አበባ፣ ደሴ ፣ ላልይበላ ፣ ጎንደር እና ባህር ዳር በሚገኙ የቱሪዝም ጽ/ቤቶች ምዝገባ መጀመሩን ገልጿል።

- ወደ ሀገር ቤት ለመጡ ዳያስፖራዎች ዛሬ በወዳጅነት ፓርክ ይፋዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ይካሄዳል።

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚበርባቸው መዳረሻዎች ወደ አ/አ በሚጫኑ የእርዳታ ጭነቶች ላይ የ20% የታሪፍ ቅናሽ አድርጓል፤ እስከ መጋቢት 6/2014 ይቆያል።

- ንግድ ባንክ በደሴ ዲስትሪክት ስር ያሉ እና በወረራ ጉዳት የደረሰባቸውን 34 ቅርንጫፎች ዳግም ስራ አስጀምሯል። ከ34ቱ መካከል ደሴ፣ ኮምቦልቻ ፣ መቅደላ ፣ መካነሰላም ፣ ባቲ ...ቅርንጫፎች ይገኙበታል።

- የሶማሊ ክልል የአርብቶ አደር ልማት ቢሮ ከአደጋ ስጋት አመራር ቢሮ ጋር በመሆን ድርቅ በተከሰተባቸው 5 ዞኖች የእንስሳት መኖ አድርሷል። መኖው በ400 ሄክታር ማሳ ላይ የተገኘ በቆላማ አካባቢ አርብቶ አደር ልማት ማሻሻያ ፕሮጀክት ድጋፍና 250 ሄክታር የክልሉ አርብቶ አደር ልማት ቢሮ በምዕራብ ጎዴ ከዘራው ማሳ የተሰበሰበ፣ 150 ሄክታር በክልሉ እርሻ እና ምርምር የተገኘ ሲሆን አጠቃላይ 150 መኪና የእንስሳት መኖ ለ14 ወረዳዎች መላኩን SRTV ዘግቧል።

- የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ነገ ይጀምራል። ተመዛኞች ዛሬ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ በሚፈተኑበት ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ ወይም orientation መከታተልና የመፈተኛ ክፍላቸውን መለየት እንዳለባቸው ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : ቡጢ የተሰናዘሩት የጆርዳን ፓርላማ አባላት !

የጆርዳን የፓርላማ አባላት በቀጥታ ስርጭት ላይ እየተላለፈ በነበረ ስብሰባ ላይ ክርክራቸው እና የቃላት ምልልሳቸው ወደከፍተኛ ፍጥጫ ተቀይሮ ወደ ድብድብና ቡጢ መሰናዘር ሲገቡ ታይተዋል።

ይህም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

አባላቱ የሁሉንም ዜጎች የእኩልነት መብት በሚያረጋግጥ የሕገ መንግሥቱ ክፍል ላይ የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች እንዲደረጉ (የሴቶች እኩልነትን ጨምሮ) ሲወያዩ ነበር ተብሏል።

ክርክሩ የተነሳው 'የጆርዳ ሴቶች' የሚለው ቃል የሁሉንም ዜጎች የእኩልነት መብት በሚያረጋግጠው የሕገ መንግሥቱ ምዕራፍ ላይ በማከል ማሻሻያ እንዲደረግ ውይይት ሲደርግ ነው።

አንዳንድ የፓርላማው አባላት፣ በተለይም ሴቶች፣ ማሻሻያው በጆርዳናውያን መካከል በፆታ ላይ የተመሰረተ መድልዎ ይፈጥራል ብለውታል።

በርካታ የፓርላማ አባላት ማሻሻያውን “ ጥቅም የለውም ” ሲሉ በቁጣ ተቃውመዋል።

የቀረበውን ማሻሻያ በማስረዳት የምክር ቤቱ ህግ ኮሚቴ ሃላፊ አብዱልሙኒም ኦድዳት ' የጆርዳን ሴቶች ' የሚለው ቃል በህገ መንግስቱ ላይ ምንም አይነት አዲስ ድንጋጌ እንሌለውና ' የቋንቋ እኩልነት ' ለመፍጠር ታስቦ የተደረገ ብቻ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ኦድዳት በማስረዳታቸው ሊቀጥሉ አልቻሉም ብዙ የህግ አውጭዎች ማሻሻያውን በመቃወም ' የጆርዳን ሴቶች ' የሚለው ቃል እንዲሰረዝ ጠይቀዋል።

በኃላም በፓርላማው ውስጥ የነበረው የቃላት ምልልስ ተካሮ ፤ በአፈ ጉባኤው እና ምክትል አፈጉባኤው መካከል የስድብ ቃላት ልውውጥ ተደርጎ በቅፅበት ፓርላማው በቪድዮው ላይ እንደሚታየው ወደ ድብደብና ቡጢ መድረክ ተቀይሯል።

ሌሎች የተያዙ መርሀግብሮችም ተሰርዘዋል።

@tikvahethiopia
#ችሎት

3 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ ክስ መሰረተ።

ዐቃቤ ህግ የ #አስቸኳይ_ጊዜ_አዋጁን ተገን በማድረግ ስልጣንን አላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል የፈፀሙ 3 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ ክስ መስርቷል።

ክስ የተመሰረተባቸው ፦
1ኛ ተከሳሽ ኮንስታብል ተሰማ መለሰ በዲስፕሊን ጥፋት ከስራ የተሰናበተ
2ኛ ተከሳሽ ዋ/ሳጅን ፈንቴ ፈይሳ የፖሊስ መኪና ሾፌር
3ኛ ተከሳሽ ረ/ሳጅን ተስፋዬ በላይ የፖሊስ መኪና ተወርዋሪ ናቸው።

ተከሳሾች ምንድነው የፈፀሙት ?

ተከሳሾቹ በጥቅም በመመሳጠር ህዳር 03 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ12፡30 - 1፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በኮልፌ ቀራንዩ ክ/ከተማ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር 0228 በሆነችና 2ኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክራት የፖሊስ መኪና የግል ተበዳይ አቶ ዘሪሁን ሀይሉ ወደሚኖርበት መኖሪያ ቤት ይሄዳሉ።

1ኛ ተከሳሽ የፖሊስ አባል በመምሰል 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ የፖሊስ አባልነታቸውን ሽፋን በማድረግ ምርመራ የማከናወን እና የግል ተበዳይን የመያዝ የስራ ድርሻ ሳይኖራቸው እና ምንም አይነት ትዕዛዝ ሳይሰጣቸው 2ኛ ተከሳሽ የግል ተበዳይን “በወቅታዊ ጉዳይ ትፈለጋለህ” በማለት 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ወደ ግል ተበዳይ መኪና በመግባት 1ኛ ተከሳሽ ተበዳይን ያለምንም ጥያቄ 6 ወር ትታሰራለህ እኛ እንድንተባበርህ ከፈለክ 200 ሺ ብር ስጠን ብለው ይጠይቁታል።

በመጨረሻም 120 ሺ ብር እንዲሰጣቸው ተስማምተው 60 ሺ ብሩን 1ኛ ተከሳሽ ወደሚጠቀምበት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ ገቢ እንዲያርግ በማድረግ እና 10 ሺህ ብር በጥሬው በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ተቀብለው ከተከፋፈሉ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ሊቀበሉ ሲሉ በማህበረሰቡ እና በህግ አስከባሪ አካላት ተይዘዋል።

በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል። 

ዐቃቤ ህግ ከዚህ በፊት ታህሳስ 4/2014 ዓ.ም ተመሳሳይ ወንጀል በፈፀሙ አራት የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ክስ መስርቶ ተከሳሾች ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ መልስ በመስጠት የችሎቱን ብይን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ የሚታወስ ነው።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Ministry-of-Justice-12-29
#Kenya #USA #Somlia #Ethiopia

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ያለውን ሁኔታ ጨምሮ በቀጠናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በውይይታቸው ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆም አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና ረገጣ እንዲቆም እንዲሁም ጦርነቱ በድርድር መፈታት እንዳለበት ተስማምተዋል ተብሏል።

ብሊንከን ፥ ሀገራቸው አሜሪካ ለፕሬዝዳንት ኬንያታ እና የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆን የሽምግልና ጥረት ጠንካራ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል።

ሶማሊያን በተመለከተ የአገሪቱ ፌደራላዊ እና ክልላዊ መሪዎች የምክር ቤትና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ነጻ በሆነ መንገድ በአስቸኳይ ማካሄዳቸው አስፈላጊ እንደሆነ ብሊንከን አመልክተዋል።

የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብሌን ፕሬዝዳንቱ ፋርማጆ ለማገድ መሞከራቸውን ሀገራቸው አሜሪካ እንደምትቃወመው ገልፀው ሁሉም ወገኖች ችግሮችን ከሚያባብሱ ተግባራትና ንግግሮች እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
#SidamaPolice

የሲዳማ ክልል ፖሊስ የልዩ ኃይል አባላትን አስመረቀ።

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ፖሊስ ኮሚሽን ለመጀመርያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የሲዳማ ልዩ ሀይል አባላት በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የልዩ ኃይል አባላቱ ምርቃት የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው እየተካሄደው።

Credit : ሲዳማ ፖሊስ ኮሚሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን በአብለጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ በ13 ተቃውሞ እና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የጸደቀው። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የፀደቀው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ማሻሻያዎች ተደረገበት ?

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚ አዋጅ በዛሬው ዕለት በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

የኮሚሽኑን መሪዎች በመሰየሙ ሂደት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ እጃቸው እንዳይገባ ሆኖ ነው የኮሚሽኑ የማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀው።

አገራዊ መግባባትን ለማምጣት ተከታታይ ምክክሮችን በማዘጋጀት እንዲሰራ ስልጣን የተሰጠውን ኮሚሽን የሚመሩ ኮሚሽነሮችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መርጠው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው እንዲያሾሙ በረቂቅ አዋጁ ተደንግጎ ነበር፡፡

ይህም የኮሚሽነሮችን #ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባል የሚል ተደጋጋሚ ትችት ሲዘነዘር ቆይቷል፡፡

በዚህም ምክንያት ረቂቅ አዋጁን ሲመረምር የቆየው ቋሚ ኮሚቴ ማሻሻያ እንደተደረገበት ተገልጿል።

በፀደቀው አዋጅ መሰረት እጩ ኮሚሽነሮችን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች እና ከሲቪክ ማህበራት ጥቆማ ይቀበላል ይላል፡፡

ጽኅፈት ቤቱ ጥቆማውን ከሰበሰበ በኋላ 14 የእጩዎች ዝርዝር ለይቶ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል።

ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እጩ ኮሚሽነሮችን በተመለከተ ውይይት ካደረጉ በኋላ ከ14ቱ 11ዱን መርጠው ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀድቃሉ ተብሏል።

ለኮሚሽኑ ደንብ እንዲያወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በረቂቅ አዋጁ ስልጣን ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ተሰርዞ ደንቡን የማውጣት ሥልጣን የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር እንዲሆን መደረጉም ታውቋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤፍም 102.1 ሬድዮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከኤሊ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በዓል አክብሮ የሚመለስ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከሪካሪ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ። ዛሬ ዓመታዊውን የኤሊ ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ አክብረው ወደ ገረሴ ወረዳ በመመለስ ላይ የነበሩ አንጋሾችን ያሳፈረ ኤፍ ኤስ አር የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶቢስ ' ሞርካ ቀበሌ ' ላይ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል። በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለሕክምና ተልከዋል።…
#Update

ትናንት በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል።

በትላንትና ታህሳስ 19 ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ አክብረው የሚመለሱ ምዕመናንን አሳፍሮ ወደ ገረሴ ወረዳ በመመለስ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ደ/ህ 19406 ኤፍ ኤስ አር የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶቢስ በማዜ ብሔራዊ ፓርክ አካባቢ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ መግለፁ ይታወሳል።

ዛሬ የጋሞ ዞን ፖሊስ በሰጠው መረጃ የሟቾች ቁጥር 6 የደረሰ ሲሆን ሟቾቹ 3 ሴቶችና 3 ወንዶች ናቸው። 18 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ ይገኛሉ።

ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን በሰላምበር ፣ ወላይታ እና ሳውላ ሆስፒታሎች በህክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የአደጋዉ መንስኤ ከወንበር በላይ መጫን እና ጠጥቶ ማሽከርከር መሆኑን የጋሞ ዞን ፖሊስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ዛሬ 3ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን ምክር ቤቱ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

(ውሳኔዎቹ ከላይ ተያይዘዋል - ያንብቡ)

@tikvahethiopoa