#EthiopiaNationalDialogue
በቱርክ-አፍሪካ አጋርነት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከቱርክ መንግስት የዜና ወኪል አናዶሉ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።
አምባሳደር ሬድዋን በቃለምልልሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ ልታካሂደው ባቀደችው ውይይት ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር እንዲኖር እየተንቀሳቀሰች ነው ብለዋል።
የሀገሪቱን ውስጣዊ የፖለቲካ ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈታ ለማስቻል አወዛጋቢ ህገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን ጭምሮ ሁሉም አጀንዳዎች ለብሄራዊ ውይይት እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ፥ ብሄራዊ ውይይቱ ህገ መንግሥቱን እስከማሻሻል እና ህዝበ ውሳኔን (ሪፈረንደም) እስከመፍቀድ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችል ተናግረዋል ሲል አናዱል አስነብቧል።
በብሄራዊ ውይይቱ ውስጥ የTPLFን ተሳትፎ በተመለከተ ፣ አሁን ላይ ቁርጥ ያለ ነገር ለመናገር ከባድ መሆኑን እና TPLF ብቸኛው የትግራይ ሕዝብ ተወካይ አለመሆኑን ተናግረዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ህወሓት የመንግስትን የሰላም እና እርቅ ጥረቶች ውድቅ እንዳደረጋቸው አስታውሰዋል።
ቡድኑ ትጥቁን ከፈታ እና ተፈላጊ ወንጀለኞችን ለመንግሥት አሳልፎ ከሰጠ በብሄራዊ ውይይቱ ላይ የመሳተፍ ዕድሉ ሊኖረው ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።
https://www.aa.com.tr/en/africa/-ethiopia-vows-to-table-all-agendas-including-referendum-in-national-dialogue/2452338
@tikvahethiopia