#Afar
ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሥርዓትን በማሻሻል ሃሳብ ላይ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የውይይት መድረክ አካሄደ።
በኢትዮጵያ ያለው ትምህርት ስርዓት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ውይይት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እያተከናወነ ይገኛል።
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው ውይይት 4ኛው መድረክ መሆኑን በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ገልፀዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፥ ለወደፊት የትምህርት ሥርዓቱ ምን መምሰል እንዳለበት በአገሪቱ ዉስጥ በሚገኙ 47 የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች ጋር መወያየታቸውን ገልፀዋል
የትምህርት ሥርዓቱን ለማሻሻል አበይት ነጥቦችን በማንሳት ከሠመራ ዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር ሰፋ ያለ ጊዜ የወሰደ ውይይት እንደሚደረጉ አብራርተዋል።
ሚኒስተር መ/ቤቱ ይህን አይነት መድረክ አጠናክሮ በማስቀጠል የሀገሪቱን የትምህርት ስርአት በማሻሻል የሚታሰበውን እድገት ማስመዝገብ የሚችል ምሁራንን ማፍራት እንዲቻል በትጋት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአፋር ቆይታቸው የወደሙ የትምህርት ተቋማትን ተዘዋውረው ተመልከተዋል፤ ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው)
@tikvahethiopia

የፀጥታ ኃይሎች ዝግጅት ...
የዓመታዊዉ የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅ/ገብርኤል ገዳም በሰላም እንዲከበር የጸጥታ ኃይሉ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳውቋል።
የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ፦
- ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፤
- ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣
- ከኦሮሚያ ፖሊስ፣
- ከድሬዳዋ ፖሊስ
- ከሀረሪ ፖሊስ የተውጣጣ በዕዝ የሚመራ የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ከአካባቢው አስተዳደር አካለት ጋር ጥምረት በመፍጠር በቂ ዝግጅት ማድረጉ ተገልጿል።
የአካባቢው ህብረተሰብ ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግላቸውና የተለየ ሁኔታም ሲያጋጥም በአካባቢው ለሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች በፍጥነት ጥቆማ እንዲሰጥ እንዲሁም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
መረጃውን ከEOTC TV ነው ያገኘነው።

#UNSC
ከዚህ በፊት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስበስባ የተቀመጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚቀመጥ ታውቋል።
ምክር ቤቱ ዛሬ በ “any other business” ስር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ የሚወያይ ሲሆን ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት ፦
🇪🇪 ኢስቶኒያ
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇮🇪 አየርላንድ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ ናቸው።
የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ ጉዳይን በተመለከተ ለፀጥታው ም/ ቤት አባላት አጭር ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።
በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጊዜ አንስቶ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን የዛሬው ስብሰባ ባለፈው ሳምንት የተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ አካሂዶ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ የመብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች አካል እንዲቋቋም በድምጽ ብልጫ ከወሰነ በኋላ ነው።
https://www.securitycouncilreport.org/whatsinblue/2021/12/ethiopia-meeting-under-any-other-business.php

TIKVAH-ETHIOPIA
#MoH የጤና ባለሞያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 27 ድረስ ይሰጣል። በህክምና ፣ ነርሲንግ ፣ ጤና መኮንን ፣ ፋርማሲ ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ፣ ሚድዋይፈሪ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያዎች ተመርቀው የጤና ሚኒስቴር የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ለተመዘገቡ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው የሚሰጠው ከታህሳስ 21-27/2014 ዓ.ም…
#Update
የጤና ባለሞያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ፦
ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 27/2014 ዓ.ም የሚሰጠውን የጤና ባለሞያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ፦
- ጅግጅጋ፣
- ነቀምት፣
- ዲላ፣
- ሰመራ እና ደሴ የመፈተኛ ከተሞች የመረጡ ተመዛኞች የመፈተኛ ከተማ ማስተካከያ መድረጉን ጤና ሚኒስቴር ዛሬ አሳውቋል።
ተመዛኞች ከዚህ በታች በተያያዘው ሊንክ ላይ የተመደቡበት የመፈተኛ ከተማ እና የፈተና ማዕከል መመልከት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል : https://www.moh.gov.et/site/HPCAL_Announcement

የቀጠለው የሱዳን ታቃውሞ ... ሱዳን ውስጥ አሁንም ተቃውሞ ቀጥሏል። ዛሬ ካርቱም ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የጥቅምት 25ቱን (እኤአ) ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ወጥተው ነበር። ሰልፉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰው ቁጥር የተሳተፈበት ሲሆን የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተሰምቷል። ባለፈው ወር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ቢመለሱም ወደራዊ…
#Sudan
የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ ትላንት እሁድ እለት በነበረው ተቃውሞ አንድ ሰው በጥይት ተመቶ መገደሉን አሳውቋል።
ትላንት በሱዳን መዲና ካርቱም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል።
ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሐን የመሩት ጦር በጥቅምት ወር መፈንቅለ መንግስት ማድረጉን ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ስልጣናቸው ቢመለሱም ሊበርድ አልቻለም።
ለተቃውሞ አደባባይ የሚወጡ ሱዳናውያን ሙሉ በሙሉ የሲቪል አስተዳደር እንዲኖር እና አል ቡርሃንም ከሥልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ መልዕክቶችን በተለያየ ጊዜ አሰምተዋል።

#France #Ethiopia
ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች።
ድጋፉ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል፣ በሦስቱ ክልሎች ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ አሳውቋን።

የኢትዮጵያ የውጭ እዳ በ2 በመቶ ቀነሰ።
በመጀመሪያው ሩብ ከውጭ የተለቀቀ አዲስ ብድር ከ5 አመት ወዲህ ዝቅተኛው ነው ተብሏል።
መንግስት በ2014 በጀት አመት መጀመሪያ ሩብ ለተወሰደ ብድር ከፍተኛ ክፍያ መፈፀም ችሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር የእዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ይፋ ያደረገው የ2014 የመጀመሪያ ሩብ አመት የአገሪቱ የእዳ ሁኔታ መግለጫ እንዳነሳው በተጠቀሰው ጊዜ የአገሪቱ የውጭ እዳ በሁለት በመቶ ቅናሽ አሳይቶ 29.05 ቢሊየን ዶላር ላይ ተቀምጧል፡፡
የውጭ እዳ መጠን ባለፈው በጀት አመት መጠናቀቂያ ላይ ከነበረው 29.52 ቢሊየን ዶላር በመስከረም ማብቂያ የ466.9 ሚሊየን ዶላር ቅናሽ ያሳየ ነው፡፡
ለዚህም አገሪቱ ለተወሰደ ብድር የከፈለች የገንዘብ መጠን ከተለቀቀ አዲስ ብድር በከፍተኛ ሁኔታ መብለጡ እንደ ምክንያት ተጠቅሷል፡፡
በ2014 የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ኢትዮጵያ 607.51 ሚሊየን ዶላር ለተወሰደ ብድር በክፍያ መልክ ያወጣች ሲሆን ከዚህም ውስጥ 155.38 ሚሊየን ዶላሩ ለወለድ የቀረው 452.12 ሚሊየን ዶላር ደግሞ ለዋና እዳ የተከፈለ ነው፡፡
በአንፃሩ ወደ አገሪቱ የገባ አዲስ ብድር በአብዛኛው ከአለም ባንክ የመጣ ሲሆን መጠኑም 137.74 ሚሊየን ዶላር ብቻ ነው፡፡ ይህ መጠን ካለፈው አምስት አመት ወዲህ ከተለቀቁ የብድር መጠኖች እጅግ አነስተኛ መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ሰነድ ያብራራል፡፡
አዲስ የተለቀቀው የብድር መጠን አገሪቱ በተጠቀሰው ጊዜ ከከፈለችው አንፃር የ470 ሚሊየን ዶላር ልዩነት አለው ወይም ኔጌቲቭ ነው፡፡
የውጭ እዳ መጠን በመስከረም መጨረሻ ከጠቅላላ የስራ ውጤት (GDP) አንጻር 26.6 በመቶ ሲሆን ከጠቅላላው የመንግስት እዳ የ 51.3 በመቶን ድርሻ ይይዛል፡፡
በተጠቀሰው ጊዜ አጠቃላይ የመንግስት እዳ 56.65 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ከጠቅላላ የስራ ውጤት (GDP) ድርሻው 52 በመቶ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ የእዳ መጠን 27.6 ቢሊየን ዶላር አካባቢ ነው፡፡
ምንጭ፦ ካፒታል ጋዜጣ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA
👩⚕️👨⚕️የጤና አገልግሎት ሰራተኞች
🏥 የጤና አገልግሎት ተቋማት እና
🚑 የህክምና መጓጓዣዎች በሁሉም ሁኔታ ውስጥ መከበር አለባቸው።
አምቡላንሶችን 🚑 አያዘግዩ። የጦር መሳሪያዎችን በጤና አገልግሎት ተቋማት ውስጥ ይዘው አይግቡ። የጤና አገልግሎት ተቋማት መጠቃት / መዘረፍ የለባቸውም። የጤና አገልግሎት ሰራተኞች በፍፁም ጥቃት ሊደርስባቸው አይገባም።
#ያስተውሉ 👉 የጤና አገልግሎት ሰራተኞች ለየትኛውም አካል አይወግኑም። ስራቸው ህይወት ይታደጋል ፤ ስራቸውን ያከናውኑ !
#ICRC

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 6 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,145 የላብራቶሪ ምርመራ 681 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 138 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#EthiopiaNationalDialogue
በቱርክ-አፍሪካ አጋርነት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከቱርክ መንግስት የዜና ወኪል አናዶሉ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።
አምባሳደር ሬድዋን በቃለምልልሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ ልታካሂደው ባቀደችው ውይይት ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር እንዲኖር እየተንቀሳቀሰች ነው ብለዋል።
የሀገሪቱን ውስጣዊ የፖለቲካ ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈታ ለማስቻል አወዛጋቢ ህገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን ጭምሮ ሁሉም አጀንዳዎች ለብሄራዊ ውይይት እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ፥ ብሄራዊ ውይይቱ ህገ መንግሥቱን እስከማሻሻል እና ህዝበ ውሳኔን (ሪፈረንደም) እስከመፍቀድ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችል ተናግረዋል ሲል አናዱል አስነብቧል።
በብሄራዊ ውይይቱ ውስጥ የTPLFን ተሳትፎ በተመለከተ ፣ አሁን ላይ ቁርጥ ያለ ነገር ለመናገር ከባድ መሆኑን እና TPLF ብቸኛው የትግራይ ሕዝብ ተወካይ አለመሆኑን ተናግረዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ህወሓት የመንግስትን የሰላም እና እርቅ ጥረቶች ውድቅ እንዳደረጋቸው አስታውሰዋል።
ቡድኑ ትጥቁን ከፈታ እና ተፈላጊ ወንጀለኞችን ለመንግሥት አሳልፎ ከሰጠ በብሄራዊ ውይይቱ ላይ የመሳተፍ ዕድሉ ሊኖረው ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።
https://www.aa.com.tr/en/africa/-ethiopia-vows-to-table-all-agendas-including-referendum-in-national-dialogue/2452338

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ግብዓት ማሰባሰብ ተጀምሯል።
በህ/ተ / ም/ቤት የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ የተለያዩ ግብዓቶችን አሰባስቧል፡፡
በይፋዊ የውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትና የተለያዩ የሲቪክ ማህበራት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በውይይቱ መግቢያ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ማቋቋሚያ አዋጁን አስመልክተው አጭር ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን፤ የማቋቋሚያ አዋጁን አስፈላጊነት፣ እስካሁን ያለፈባቸውን ሂደቶች እንዲሁም የኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነት ላይ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
ለሀገራዊ መግባባት የሚጠቅሙ አጀንዳዎች መለየት፣ የሚሳተፉ አካላትን መለየት፣ የምክክር መድረኮችን ማሳለጥ፣ ከምክክር መድረኮቹ የተገኙ ምክረ ሀሳቦችንና የአተገባበር ስልታቸውን የሚጠቁም ሰነድ ማዘጋጀት እንዲሁም ተግባራዊነታቸውን መከታተል ከሚቋቋመው ኮሚሽን የሚጠበቁ ዋና ዋና ተግባራት ስለመሆናቸው ጠቁመዋል፡፡
ከየተቋማቱ የመጡት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለሚቋቋመው ኮሚሽን ይጠቅማል ያሉትን መልካም ተሞክሮዎቻቸውን በማጋራት ሊገጥም ይችላል ያሉትን ስጋት ጠቁመዋል፡፡
በሚቋቋመው ኮሚሽን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የኮሚሽነሮች አሰያየም ላይ ተደጋጋሚ አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን፤ በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 9/10 ስር ኮሚሽኑ ዝርዝር ሪፖርት በማዘጋጀት ለመንግስት ያቀርባል የሚለው ሀሳብ ኮሚሽኑን በመንግስት ተጽእኖ ስር ሊከተው ይችላል የሚሉና ተመሳሳይነት ያላቸው የገለልተኝነት ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ #HPR

#MarakiEngraving
🎄ዘመን ተሻጋሪ ጊዜ ማይሽረው ልዩ ስጦታ🎄
🎁ከእንጨት የተሠራ Postcard
☎️0953144144 / 0915089555
📌አድራሻ- መገናኛ ገነት ኮሜርሻል 4ኛ ፎቅ 412
👇join our channel
https://t.iss.one/maraki_engraving
🎄ዘመን ተሻጋሪ ጊዜ ማይሽረው ልዩ ስጦታ🎄
🎁ከእንጨት የተሠራ Postcard
☎️0953144144 / 0915089555
📌አድራሻ- መገናኛ ገነት ኮሜርሻል 4ኛ ፎቅ 412
👇join our channel
https://t.iss.one/maraki_engraving
#AddisAbaba : በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የሮባ ዳቦ ቤት - ገርጂ መብራት ሀይል የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣ አስታውቋል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ካለው አጠቃላይ 973 ሜትር ርዝመት ውስጥ ከ100 ሜትር በላይ የሚሆነው በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ለረጅም ጊዜ ግንባታው ተቋርጦ ቆይቷል።
የወሰን ማስከበር ችግሩ ከተፈታ በኋላ ቀሪውን የግንባታ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ አሁን ላይ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መጠናቀቅ መቻሉ ከሮባ ዳቦ ቤት በገርጂ መብራት ወደ ጃክሮስ አካባቢ ለሚደረገው ጉዞ አቋራጭ መንገድ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ ከሚገነባቸው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ መንገድ በታቀደለት ግዜ ገደብ እንዳይጠናቀቅ የወሰን አለመከበር ማነቆ ሆኗል።
የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀከት በአሁን ሰአት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
በህዳር 2011 ዓ.ም የተጀመረው የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ አስፋልት መንገድ ፕሮጀከት አጠቃላይ ርዝመቱ 5.6 ኪ.ሜትር እና 25 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡
አሁን ላይ 2.7 ኪ.ሜትር የሚሆን የአስፋልት ማልበስ ስራ፣ ሰብ ቤዝ ፣ ድጋፍ ግንብ፣ የፓይፕ ቀበራ ፣ የእግረኛ መንገድና ተያዥ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

#ቪድዮ የኡጋንዳ ጦር ከጎረቤቱ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ሃይሎች ጋር በመሆን በ Allied Democratic Force (ADF) ታጣቂ ቡድን ላይ በጋራ የአየር ድብደባ እና የመድፍ ጥቃት መፈፀሙን ትላንት አሳውቋል። ዛሬ ደግሞ ኡጋንዳ ይህን የታጠቀ ቡድን ለማደን እና ለመቅጣት ጦሯን ድንበር አሻግራ ወደ ኮንጎ መላኳ ተሰምቷል። የኡጋንዳ ባለስልጣናት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በካምፓላ ለደረሰው…
#Update
የኡጋንዳ እና የኮንጎ ዴሞክራቲኮ ሪፐብሊክ ሠራዊት ጥምረት በኮንጎ ምስራቃዊ ግዛት ውስጥ የሚገኙ አማጽያንን ጠንካራ ይዞታዎች መደምሰሳቸውንና 35 አማጽያንን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አስታውቀዋል።
ከሁለቱ አገሮች የተውጣጣው ጦር “ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሰሜን ኩቩ እና ኢቱሪ ክፍለ ግዛት ውስጥ የሚገኙ አዳዲስ የጠላት ሰፈሮችን ” ማጥቃታቸውን የኮንጎ ጦር ሠራዊት ባወጣው መልዕክት አስታውቋል፡፡
እኤአ ህዳር 30 የሁለቱ አገሮች ጥምረት ጦር እምርጃ መውሰደ ከጀመረ ወዲህ፣ ብዙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በዩጋንዳና ኮንጎ ውስጥ ለደረሰው የሽብር እልቂት ተጠያቂ የሆነውን የተባበሩት ዴሞክራቲክ ኃይሎች ወይም ADF እየተባለ የሚጠራውን የአማጽያን ቡድን መደምሰሱን ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል።
ADF በዩጋንዳና ኮንጎ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች ተጠያቂ የተደረገ ድርጅት መሆኑም ይታወቃል።