'' ኢትዮጵያን ለቅቄ የመውጣት ሃሳብ የለኝም '' - ኤድዋርድ ብራውን
የዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ዳይሬክተር #አሜሪካዊው ኤድዋርድ ብራውን ኢትዮጵያን ለቀው እንደማይወጡ አስታውቀዋል።
ብራውን ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል በዚህ ሳምንት ደግሞ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ገልፀዋል።
ሐሙስ ታህሳሰ 7 ደግሞ በአማሮ ፣ ገላና እና ሱሮበርጉዳ ወረዳ ዘለቄታዊ ሰላምን ለማምጣት በ500 ሺህ ዶላር የሚተገበር ፕሮጀክት አስጀምረዋል።
ዳይሬክተሩ የሀገራቸው አሜሪካ መንግስት ዜጎቹ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ እየወተወተ በሚገኝበት በአሁን ሰዓት እርሶ እንዴት ጥሪውን ሳይቀበሉ ቀሩ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል ምላሽ ሰጥተዋል።
ኤድዋርድ ብራውን ፥ " ያለሁት የኢትዮጵያን ህዝብ ለማገልገል ነው ደግሞም በጣም በማስፈልግበት ሰዓት መሆን ያለብኝ እዚሁ ነው ብዬ አምናለሁ፤ በመላ አገሪቱ ከህዝቡ እና ከመንግስት በኩል ከፍተኛ ድጋፍ ነው እየተደረገልን ያለው ስራዬን በአግባቡ እየሰራሁ ነው ስለዚህ ወዴትም አልሄድም " ሲሉ ነው የመለሱት።
መረጃው የአሐዱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia

👍5