TIKVAH-ETHIOPIA
የፌልትማን የግብፅ፣ ቱርክ እና የUAE ጉዞ ፦ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፣ ቱርክ እና ግብፅ እንደሚያማሩ ተሰምቷል። የጉዟቸው ዓላማ ደግሞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመምከር ነው። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤህ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራስ በሰጡት መግለጫ ፌልትማን ወደ ሦስቱ አገራት ጉዟቸውን የሚያደርጉት ከዛሬ ሐሙስ ህዳር…
#Update
ፌልትማን ታህሳስ 4 እና 5 ቱርክ ነበሩ።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ታህሳስ 4 እና 5 ቀን 2014 ዓ/ም ቱርክ፣ አንካራን ነበሩ።
በቆይታቸው ከቱርክ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው መክረዋል።
ፌልትማን የጋራ ግቦቻችን በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ነው ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
ፌልትማን በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ አፅንኦት በመስጠት የመስራት ፍላጎት ያላቸውን ሀገራት በሙሉ ሀገራቸው አሜሪካ በደስታ ትቀበላለች ብለዋል።
ህዳር 29 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በሰጠው መግለጫ ከህዳር 30 ጀምሮ ፌልትማን ወደ ግብፅ ፣ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ እና ቱርክ እንደሚጓዙ አሳውቆ ነበር፤ ከዚህ የሚኒስቴሩ መግለጫ በኃላ በይፋ የተገኘው መረጃ የቱርክ ጉዞ ሲሆን ፌልትማን ወደ ግብፅ እና ዩኤኢ ስለመሄዳቸው ፣ ሄደውም ከሆነ ስለምን እንደተወያዩ ይፋ የሆነ መረጃ መግኘት አልተቻለም።
@tikvahethiopia

Turkey 🤝 Africa
" ለጋራ እድገት እና ብልጽግና የጎለበተ ወዳጅነት "
3ኛው የቱርክ - አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ነገ በቱርክ ኢስታንቡል ይጀመራል።
ለዚሁ ጉባኤ የተለያዩ ሀገራት ባለስልጣናት ቱርክ እየገቡ ይገኛሉ። በዚህ ጉባኤ የ39 ሃገራት ሚንስትሮች እና 13 ፕሬዚዳንቶች ለመሳተፍ ከወዲሁ ማረጋገጫ ልከዋል።
" ለጋራ እድገት እና ብልጽግና የጎለበተ ወዳጅነት " በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የሁለት ቀን ጉባኤ ቅዳሜ ዕለት የቱርክ ፕሬዜድሬቺፕ ጣይብ ኤርዶሃን ንግግር ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።
በሌላ በኩል የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ለዚሁ ጉባኤ ቱርክ ከሚገኙት የኮትዲቯር (ካንዲ ካማራ) ፣ ቡሩንዲ (አምባሳደር አልበርት ሺንጊሮ) እና ዚምባብዌ (ፍሬድሪክ ሻቫ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ጆርጅ ፍሎይድን በጭካኔ የገደለው ፖሊስ ተፈረደበት። ባለፈው ዓመት በአሜሪካ፣ ሚኒሶታ ውስጥ ጆርጅ ፍሎይድን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው አሜሪካዊ የቀድሞ የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቻውቪን 22 ዓመት ከ6 ወር እስር ተፈረደበት። ፍርዱን ያሳለፉት ዳኛ ቻውቪን ይህ ቅጣት የተላልፈበት "የተጣለበትን እምነት እና ኃላፊነት በማጉደል እንዲሁም በታየው ልዩ ጭካኔ" ላይ የተመሠረተ መሆኑን ተናግረዋል። ቻውቪን እንደ…
#Update
በአሜሪካ ሚናፖሊስ ግዛት ጆርጅ ፍሎይድ አንገት ላይ ከ9 ደቂቃ በላይ በመንበርከክ ህይወቱ እንዲያልፍ ምክንያት የሆነው ፖሊስ ዴሪክ ቻውቪን ወንጀሉን መፈጸሙን አምኗል።
የ45 ዓመቱ ፖሊስ በፍሎይድ ግድያ ከ22 ዓመታት በላይ ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኛል።
ቻውቪን ከአቃቤ ህግ ጋር እያደረገ ባለው የቅጣት ድርድር አማካኝነት ትላንት ረቡዕ ከዚህ ቀደም ሰጥቶት የነበረውን የክሕደት ቃል ወደ እምነት ቃል አሻሽሏል።
በስምምነቱ መሰረት በመጪው ወር ሊደረግ የነበረውን የክስ መስማት ሂደት የሚቀር ሲሆን የቅጣቱ መጠን ዝቅ ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል።
ግለሰቡ 2 ክሶች ቀርበውበታል ፤ የመጀመሪያው ፍሎይድ እጁ በካቴና ታስሮ ባለበት ወቅት አንገቱ ላይ መንበርከክ ብሎም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላም አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኝ ባለመርዳት ነው።
ግለሰቡ ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ባሻገርም እ.ኤ.አ. በ2007 አንድ የ 14 አመት ታዳጊን በቁጥጥር ስር ባዋለበት ወቅት ስለጣሳቸው መብቶች ጭምር የጥፋተኝነት ቃሉን ሰጥቷል።
የፖሊስ አባሉ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ታስሮ እንዳለ ታውቋል። የሰጠው የጥፋተኝነት ቃሉ አሁን ካለው የእስር ግዜ በላይ ሊያረዝምበት እንደሚችል ይገመታል።
አቃብያነ ሕጉ ፖሊሱ ላደረሰው የሲቪል መብቶች ጥሰት ሕጎቹ እስከ 25 ዓመት ድረስ የሚደርስ የእስር ግዜ ጠይቀዋል።
በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ወቅት የነበሩት ሌሎች ሁለት ፖሊሶችም በመጪው መጋቢት ወር ክሳቸው መሰማት እንደሚጀመር ቢቢሲ ዘግቧል።

ከጃማ ደጎሎ እስከ ዓለም ከተማ ያሉ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ አግኝተዋል።
ከአንድ ወር በላይ ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩት የሚዳ መራኛ፣ ዓለም ከተማ፣ ፌጥራ፣ ሬማ፣ ደራ ጉንዶመስቀል እና ለሚ ከተሞች ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

#TechZone
ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599 ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599 ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
#Bank_of_Abyssinia
ባንካችን አቢሲንያ በሃገራችን የመጀመሪያው የሆነውን ለዓይነ ስውራን ታስቦ የተዘጋጀ በድምጽ የታገዘ የኤቲኤም አገልግሎት ለደንበኞቹ አቅርቧል።
አገልግሎቱ በ 4 የቋንቋ አማራጮች የቀረበ ሲሆን ዓይነ ስውራን ገንዘብ ወጪ ማድረግ፣ ገንዘብ ከሒሳብ ወደ ሒሳብ ማስተላለፍ ፣ የምስጢር ቁጥር መቀየር እንዲሁም ገንዘብ ውደ ቴሌብር ዋሌት መሙላት እንዲያስችላቸው ሆኖ የቀረበ ነው።
የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ!👇 https://t.iss.one/BoAEth
#አቢሲንያ #የሁሉም_ምርጫ

'' ኢትዮጵያን ለቅቄ የመውጣት ሃሳብ የለኝም '' - ኤድዋርድ ብራውን
የዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ዳይሬክተር #አሜሪካዊው ኤድዋርድ ብራውን ኢትዮጵያን ለቀው እንደማይወጡ አስታውቀዋል።
ብራውን ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል በዚህ ሳምንት ደግሞ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ገልፀዋል።
ሐሙስ ታህሳሰ 7 ደግሞ በአማሮ ፣ ገላና እና ሱሮበርጉዳ ወረዳ ዘለቄታዊ ሰላምን ለማምጣት በ500 ሺህ ዶላር የሚተገበር ፕሮጀክት አስጀምረዋል።
ዳይሬክተሩ የሀገራቸው አሜሪካ መንግስት ዜጎቹ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ እየወተወተ በሚገኝበት በአሁን ሰዓት እርሶ እንዴት ጥሪውን ሳይቀበሉ ቀሩ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል ምላሽ ሰጥተዋል።
ኤድዋርድ ብራውን ፥ " ያለሁት የኢትዮጵያን ህዝብ ለማገልገል ነው ደግሞም በጣም በማስፈልግበት ሰዓት መሆን ያለብኝ እዚሁ ነው ብዬ አምናለሁ፤ በመላ አገሪቱ ከህዝቡ እና ከመንግስት በኩል ከፍተኛ ድጋፍ ነው እየተደረገልን ያለው ስራዬን በአግባቡ እየሰራሁ ነው ስለዚህ ወዴትም አልሄድም " ሲሉ ነው የመለሱት።
መረጃው የአሐዱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው።

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ🚨
በሰሜን ሸዋ ዞን ውጊያ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የወዳደቁ ያልፈነዱ ጥይቶችና ፈንጆች በህጻናት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን የደብረ ብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።
ሆስፒታሉ የአካባቢው ማህበረሰብና አመራር ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
የደብረ ብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አስማረ ሳሙኤል፥ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ አካባቢ በውጊያ መሃል ያልፈነዱ ጥይቶች በእርሻ ቦታዎች ወድቀው እየተገኙ መሆኑን ጠቁመው ከትናንት በስተያ 4 ታዳጊ ወጣቶች ማሳ ውስጥ የወደቀ ጥይት ፈንድቶባቸው እግራቸውና እጃቸው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ሁለቱ በደ/ብርሃን ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ሁለቱ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ ሪፈር መባላቸውን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ዛሬ ከጀቦሃ አካባቢ አንድ የ13 ዓመት ልጅ መጫወቻ መስሎት የወደቀ ጥይት አንስቶ ሲቀጠቅጥ በተከሰተ ፍንዳታ 3 ጣቶቹ ተቆርጠው በሆስፒታሉ እየተረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላቸው ላሉ ተጎጂዎችም አስፈላጊው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ዶ/ር አስማረ ሳሙኤል፦
• ህወሓት መሽጎባቸው የነበሩ አካባቢዎችና የወዳደቁ መኪናዎች ላይ የተለዬ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
• ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ በእርሻ ቦታዎች አርሶ አደሩ በጥንቃቄ ምርቱን ሊሰበስብ ይገባል።
• በየአካባቢው ያሉ አመራሮችና የጸጥታ አካላት ህብረተሰቡን ማንቃትና አካባቢውን መፈተሽ አለባቸው።
• ወላጆች ልጆቻቸው ማንኛውንም የወደቀ ነገር አንስተው እንዳይቀጠቅቱ ሊመክሩ ይገባል።
• በአካባቢው ላይ በየማሳው የድሽቃ፣የሞርተርኛ ሌሎችም ጥይቶች የወዳደቁ በመሆኑ በባለሙያዎች ለቀማ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

" የታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስኪሆን ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ ይቀጥላል " - ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ። የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉ ይታወሳል።…
#Update
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የታሪፍ ማሻሻያ በነገው እለት ይፋ አደርጋለሁ ማለቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
ካለንበት የታህሳስ ወር ጀምሮ የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ይታወቃል።

ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ?
ከትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነገ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል።
ምክር ቤቱ በአውሮፓ ህብረት አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ የሚጠይቅ ረቀቂ የውሣኔ ሀሳብ ቀርቦለታል።
ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጋር በጥምረት ያደረጉት ምርመራ ውጤትም መነሻ አድርጎ ተጨማሪ ምርመራ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን እንዲሰማራ ይጠይቃል።
ዓለም አቀፍ መርማሪ ቡድኑ የ1 ዓመት ቆይታ እንዲኖረው የሚጠይቅ ሲሆን የሚላከው ቡድን ከሚያደርገው ምርመራ በተጨማሪ የሽግግር ፍትህ ተግባራዊ የሚያደርግበትን፣ ዕርቅና ተጠያቂነት የሚሰፍንበትን እንዲሁም ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸው ማገገም እንዲችሉ ምክረ ሃሳብ እና የቴክኒክ ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት እንዲኖረው ይጠይቃል።

ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ? ከትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነገ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል። ምክር ቤቱ በአውሮፓ ህብረት አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ የሚጠይቅ ረቀቂ የውሣኔ ሀሳብ…
" ኢትዮጵያ 🇪🇹 አትቀበለውም "
በነገው የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ኢትዮጵያ እንደማትቀበልና ተፈፃሚ እንደማይሆን አሳውቃለች።
ከትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነገ እንዲካሄድ የተጠራው ልዩ ስብሰባ የሚካሄድበትን ሥነ ሥርዓት አስመልክቶ የም/ ቤቱ ቢሮ ትላንት ውይይት አካሂዶ ነበር።
በውይይቱ ወቅት በተመድ የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ አምባሳደር ማሕሌት ኃይሉ ተገኝተው የኢትዮጵያ መንግሥትን አቋም በግልጽ አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ላይ የተጠራው ልዩ ስብሰባ የምክር ቤቱን የአሠራር ደንብ ያልተከተለና የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትን ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ለፖለቲካዊ ፍላጎቶች መጠቀሚያ የሚያደርግ እንዲሁም፣ ምክር ቤቱ አባል አገሮች ላይ መድሎ እንዲፈጽምና በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያዩ አሠራሮችን እንዲከተል በማድረግ ተቋማዊ ኃላፊነቱን የሚያረክስ እንደሆነ ተናግረዋል።
አባል አገሮቹ ይህን ያልተገባ አሠራር እና አንዳንድ አገሮች የሰብዓዊ መብትን ሽፋን በማድረግ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን በምክር ቤቱ በኩል ለማስፈጸም የሚያደርጉትን ጥረት በማውገዝ የምክር ቤቱ ተቋማዊ መርህዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
" በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያን አስመልክቶ የተጠራውን አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እና የዚህን ስብሰባ ውጤቶችን አይቀበልም " ብለዋል።
" በመሆኑም የተጠራቅ ልዩ ስብሰባ እና ምክር ቤቱ በዚህ ስብሰባ ውሳኔ እንዲሰጥበት ተብሎ የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ጋር በቀጥታ የሚጣረስ በመሆኑ ስብሰባውም ሆነ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡ እንዲሰረዙ እንጠይቃል " ሲሉ አምባሳደር ማህሌት ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ሪፖርተር

" በጥምረት የተካሄደውን ምርመራ እውቅና መንፈግ ነው " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ፕሬዚዳንት ናዛት ካን፣ ለሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት ግልጽ ደብዳቤ ፅፏል።
ኢሰመኮ በጻፈው ደብዳቤ፥ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል እስከ ፈረንጆቹ ሕዳር 3 ቀን 2021 ድረስ የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በሌላ አካል በድጋሚ እንዲጣራ ማድረግ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እና በኢትጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጥምረት የተካሄደውን ምርመራ እውቅና መንፈግ ነው ብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ምርመራ ተደርጎ በሪፖርት የቀረበውን ጉዳት በሌላ አካል ከማስደገምና ሂደቱን ከማጓተት፣ ቀደም ብሎ በወጣው የምርመራ ሪፖርት መሰረት ተጎጂዎች እንዲያገግሙ፣ ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ እንዲመለሱ እንዲሁም እንዲካሱ ብሎም ወንጀል የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ መሠራት ነበረበት ብሏል።
ኮሚሽኑ ሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እንደገና ይጣራ ከተባለ አጥፊዎቹ አካላት የፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመካድና እና ኮሚሽኑ የሰራውን ምርመራ ለማጣጣል ብሎም የኮሚሽኑን ተግባር ዝቅ የሚያደርግ ይሆናል ሲል ስጋቱን ገልጿል።
ሙሉ ደብዳቤው በዚህ ተያይዟል : ehrc.org/the-commission-calls-on-the-human-rights-council-to-support-the-implementation-of-the-joint-investigation-recommendations-and-to-encourage-ongoing-independent-investigations-in-ethiopia/