TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#America

" ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋም ሆነ አዲስ አበባ እንዲገባ አሜሪካ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም" - የአሜሪካ መንግስት

ከሰሞኑን የህወሓት ቡድን ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት ስለ አሜሪካ የተናገሩትን ንግግር በተመለከተ የአሜሪካ መንግስት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ምላሽ ሰጥቷል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በቃለ ምልልሱ ወቅት ፥ " የአሜሪካን አቋም ለመረዳት ከባድ ነው ። አንዳንዴ በሁለታችንም ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉ እያስፈራሩ ሰላም እንድናወርድ ይስገድዱናል፤ መልሰው ህወሓት አዲስ አበባ ከገባ ደም መፋሰስ ይኖራል ይሉናል ፤ በተመሳሳይ ጊዜ አዲስ አበባ የምትገቡ ከሆነ ሊፈጠር የሚችለውን ረብሻ ለማስቀረት እንዲቻል ሌሎች ፓርቲዎችን ጠርታችሁ አንድሁኑ ይሉናል፤ አሜሪካውያኑ ህወሓት አ/አ ቢገባ እንደድሮው ግትር ይሆናል የሚል ፍራቻ አላቸው ይሁን እንጂ አሜሪካ ውስጥ ያለው አስተሳሰብ ወጥ አለመሆኑን ማወቅ ጥሩ ነው " ሲሉ ነው የተናገሩት።

በዚህ ጉዳይ የአሜሪካ መንግስት ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል ፦

" ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋ ሆነ ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ አሜሪካ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም።

እኛ ለሁሉም ወገኖች በአደባባይ ሆነ በግልም የአሜሪካ አቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ግጭት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው በተደጋጋሚ ግልፅ አድርገናል።

የኛ ፍላጎት ህወሓት ለቆ እንዲወጣና ትግራይ ላይ ያለው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት የከበባ እግድ ሊባል የሚችል ሁኔታ አብቅቶ ማየት መሆኑን ልዩ ልዑኩ ፌልትማን ህዳር 14 አሳውቀዋል።

የእኛ ግብ ግጭቱ እንዲያቆም ፣ የመብቶች ጥሰት እና ሁከት እንዲያበቃ ፣ ድርድር ያለቅድመ ሁኔታ እንዲጀመር ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖርና ያንን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታዎች እንዲመቻቹ፤ ሁሉን አቃፊ የሆነ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀመር የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ብቸኛውም መንገድ ዴፕሎማሲ እንዲሆን መደገፍ ነው። "

@tikvahethiopia