TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#udate ሳምንታዊ የመንግስት መግለጫ⬇️

በኢትዮጵያ #የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ።

የአገሪቷን ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው ሳምንታዊ የመንግስት አቋም መግለጫው አመልክቷል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ለህዝቦቿ ተስፋ ሰጪ ከመሆኑ በላይ ከአገር አልፎ ለአጎራባች የአፍሪካ አገሮች ጭምር ተምሳሌት መሆኑን የታወቁ የዓለም ፖለቲካ ተንታኞችና ተቋማት እየመሰከሩለት መሆኑን ጠቅሷል።

ይሁን እንጂ ለውጡን የማይደግፉ ቡድኖች አንዳንድ አደናቃፊ ተግባራትን ሲፈፅሙ እንደሚስተዋል አመልክቷል።

እነዚህ አካላት ከሰሞኑ በቡራዩ እና በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ባስነሱት ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ “የዜጎች ጥሪትም ወድሟል” ሲል አመልክቷል።

“የንፁሃን ዜጎችን ደም ማፍሰስ፣ አካል ማጉደል እና ለዓመታት ለፍተውና ደክመው ያፈሩትን ሃብት በመዝረፍና በማውደም፤ ሁሉም የሚረባረብለትን የለውጥ ጉዞ ለማጠልሸት መስራት ለማንም ትርፍ አያስገኝም” በማለትም አስገንዝቧል።

በመሆኑም በደረሰው ጉዳት ህዝብ እና መንግስት አዝነዋል ያለው የመንግስት መግለጫ “ድርጊቱ የየትኛውንም ብሄር የማይወክል እና ክስተቱ ለውጡን የሚያፋጥን እንጂ ሊያደበዝዝ አይችልም” ብሏል።

በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ማሸነፍና ሥልጣን መያዝ የሚቻለው የተሻለ ሃሳብ በማቅረብ ተወዳድሮ በማሸነፍ እንጂ #በአመጽና በኃይል ሊሆን እንደማይችልም በመግለጫው ተመልክቷል።

የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት ሁኔታ የአገሪቷን #ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲ ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ መንግስት ኃላፊነቱን ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህግ የበላይነት #መከበር በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቤንሻንጉል ክልል⬇️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኦዳ ዳለቲ እና በጉባ አልመሃል ላይ በተፈጠሩ ግጭቶች 69 ተጠርጣሪዎችን #በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ መንግስት #የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከፌደራልና ከአጎራባች ክልሎች ጋር እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የከልሉ መንግስት የህግ የበላይነት ለማስከበር #ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛልም ብለዋል፡፡

ነሐሴ 26 እና 27 2010 ዓ'ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኦዳ ቢልዲጊሉ ወረዳ ዳለቲ ቀበሌ ላይ በተፈጠረው ግጭት 48 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ የማጣራት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ግጭቱ በቤኒሻንጉልና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አከባቢ ላይ የተከሰተ በመሆኑ የማረጋጋት ስራዉንም ሆነ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር
የማዋል ሂደቱ በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ ነዉ አቶ ማሃመድ የተናገሩት፡፡

በተመሳሳይም መስከረም 3 2011 ዓ.ም በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሃል ቀበሌ ላይ በደረሰዉ ጥቃት 21 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተካሄደባቸዉ ይገኛል፡፡

ሰኔ 17 እስከ 21 በአሶሳ ከተማ፣ በሽርቆሌ ወረዳ እና በማኦኮሞ ልዩ ወረዳ ላይ ተከስቶ በነበረዉ ግጭት በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸዉ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑንም አቶ መሃመድ ገልፀዋል፡፡

#በአሶሳ ከተማ እና በሸርቆሌ ወረዳ ላይ ተከስቶ በነበረዉ ግጭት ከ 1 መቶ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የኦፕሬሽ ስራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ጥረት እያደረገ ነዉ ያሉት ሃላፊዉ ከፌደራል መንግስት የተላከ ቡድን እንዳለም ተናግረዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀልን በጋራ እንከላከል‼️

የዜጎች ነፃነት ሳይሸራረፍ ይከበር ዘንድ #የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ግድ ይላል። ወንጀልን መርምሮ ወንጀለኛን ከማስቀጣት ደግሞ ወንጀልን ቀድሞ መከላከል ይሻላል።

ማንኛዉም ዜጋ በሚከተሉት ቁጥሮች ጥቆማ መስጠት ይችላል!

የፌዴራል ፖሊስ፦
0115543678/
0115526303/
0115543681/
987

አዲስ አበባ ፖሊስ
0111110111/
991

ኦሮሚያ ፖሊስ፦
0118722020/
0113692452

አማራ ፖሊስ፦
0582201327

ደቡብ ፖሊስ፦
+251462212870

እነዝህ ስልኮች 24 ሰዓት ክፍት ናቸዉ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀረሪ ክልል⬇️

የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ህገ ወጥነትን ለማስቀረት የሚሰራ ኮሚቴ ማቋቋሙን የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ገልፀዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕስ መስተዳር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ አገራችን በለውጥ ውስጥ እንዳለች ትላንት በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለውጡን የማይፈልጉ ጥቅማቸው የተነካ አካላት በእምነትና በጎሳ #ግጭት ለመፍጠር እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በክልላችንም አልፎ አልፎ ይኸው ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልፀዋል ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በመቀጠልም #የህግ የበላይነትን ለማስከበር በክልሉ ምክር ቤት የሰላም ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ የተከማቸውን #ቆሻሻ አስመልክቶም የከተማዋ ነዋሪዎች እስካሁን ላሳዩት #ትእግስት ምስጋና አቅርበው ቆሻሻው በቀጣዮቹ ሁለት
ቀናት ውስጥ ይወገዳል ብለዋል፡፡

በፀጥታው በኩል #ከቄሮ እና #ፋኖ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ባሉበት ቦታ #ሰኞ ምክክር እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጠ/ሚ ፅ/ቤት‼️

መንግስት #የህግ_የበላይነትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ አቋም መያዙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት አስታወቀ፡፡

ሴክሬታሪያቱ ዛሬ በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ ላይ እናዳለው በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ከህግ ያፈነገጡ ሁኔታዎች ይስተዋላሉ፡፡

መንግስት ይህን ሁኔታ ለማስቆም ቁርጠኛ አቋም ይዟል ብሏል ሴክሬታሪያቱ፡፡

የህግ የበላይነትን ለማረጋገጡ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ነው የሚለው አስተያየትም የተሳሳተ መሆኑን ነው ሴክሬታሪያቱ የገለፀው፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄዱ ያሉት ሪፎርሞች ለአገራዊ ችግሮች አገር በቀል መፍትሔዎች የማበጀት ዓላማ ያላቸው መሆናቸውንም ጠቅሷል ሴክሬታሪያቱ፡፡

አገራዊ ለውጡ ከውስጥም ከውጭም ትልቅ እውቅና የተቸረው ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ድጋፍም እያስገኘ ያለ ነው ብሏል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ አስተማማኝ ሰላምን በማስፈን የሕዝብን #ደኅንነት ማስከበር የመንግሥት ቀዳሚ ተግባር ነው! #ሕገ_ወጦችና ወደሕግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

🔹🔹ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት🔹🔹
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ #የህግ_የበላይነትን በማስከበር የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ መሆኑን የአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች ተወካዮች ተናግረዋል።

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዴኦ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት አቶ ነጉሱ ጥላሁን #በጌዴኦ ላሉ ተፈናቃዮች የዕለት ምግብ ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት #ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። መንግሥት የዕለት ደራሽ ምግብ ለሚያስፈልጋቸው #ድጋፍ ለማድረግ ከፌደራል እና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከዚህ ቀደምም ሲሰራ ቆይቷል፤ በዚህም እንዲቋቋሙ የተደረጉ እንዳሉም ገልጸዋል።

ነገር ግን አሁንም #የዕለት_ደራሽ_ምግብ ያልደረሳቸው ዜጎች እንዳሉ እና ችግር ላይ እንደወደቁ መንግሥት ተረድቶ የዕለት ምግብ ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶት ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ዜጎችን በማቋቋም፣ #የህግ_የበላይነትን በማረጋገጥ የሚደርሱ ማፈናቀሎችን ማስቆም መቻል ላይ መንግሥት ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia