TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#udate ሶማሌ ክልል⬇️

በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ሴቶች ለተለያዩ ጉዳቶች የተጋለጡ ሲሆን ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበርና ባለሙያዎችን ወደ ቦታው በመላክ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶች #የስነልቦናና ማበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

ከነዚህም መካከል ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው 7 ሴቶች ወደ አዲስ አበባ መጥተው አስፈላጊውን የተሀድሶ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ በተደረገው ጥረት ተጎጂዎች በዛሬው ቀን አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን አገልግሎቱን ወደሚያገኙበት ማዕከል እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ክብርት ወ/ሮ አስቴር ዳዊት የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እና የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ኤጀንሲ
(UN Women) የኢትዮጵያ #ተጠሪ በቦታው በመገኘት አቀባበል በማድረግ ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች አነጋግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia