TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🤔

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃደኛ አለመሆን የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት እያደረግኩት ባለው ጥረት ላይ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስነብቧል።

የቢሮ ኃላፊ አቶ አሥራት አዳሮ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፦

" በክልሉ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ #ባለሙያዎችንና #ኃላፊዎችን የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ትምህርታቸውን ባጠናቀቁበት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ በመሄድ ማስረጃዎቹ ሐሰተኛ ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለውን ለማጣራት ሙከራ ብናደርግም የግል ትምህርት ተቋማት ፈቃደኞች አይደሉም፡፡

ከ5 እና 6 ወር በኋላ ተመልሳችሁ ኑ የሚል ምላሽ ስለሚሰጡን ወደ ትምህርት ተቋማቱ የምንልካቸው ባለሙያዎች ለእንግልት እየተዳረጉ ነው።

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የትምህርት ጥራትን ከመጉዳትም ባሻገር የተማረ የሰው ኃይል በተፈለገው ቦታ ላይ እንዳይሠራና ጥራት ያለው አገልግሎት ለኅብረተሰቡ እንዳይሰጥ የሚያደርግ ነው።

በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተቀጥረው በሥራ ላይ በሚገኙ #አመራርና #ባለሙያዎች ሕዝቡ ትክክለኛ አገልግሎት እንዳያገኝ ሲያደርጉ ነበር ፤ ክልሉ የሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የትምህርት መረጃን አጣርቶ በሚያገኘው ውጤት መሠረት ከሥራ እና ከደመወዝ ከማገድ ባሻገር በሕግ እንዲጠየቁ ይደረጋል።

የማጣራቱን ውጤት ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ6ቱም ዞኖች የተጠቃለሉ መረጃዎችን በማደራጀት ምን ያህል አመራርና ባለሙያ በሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥሮ ሲሠራ እንደነበር ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል።  "

#EPA

@tikvahethiopia