TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FightCOVID19

"ኮሮና ቫይረስን በመግታት ረገድ የቻይና መንግሥት ጠንካራ አመራር ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ግልጽ አሰራር መዘርጋት ፣ መረጃ #በፍጥነት ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም ህዝቡን ማሳተፍ ቫይረሱን ለመከላከል ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው። ቫይረሱ ድንበር ዘለል በመሆኑ በጋራ ጥረት ሊቆም ይገባል፤ የምናደርገው ትብብር የበለጠ ሊጠናከርም ይገባል" -በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 298 ደረሱ!

በጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የሚያዙ ሰዎች ቁጥር #በፍጥነት እየጨመረ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 498 የላብራቶሪ ምርመራ 83 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸቅ ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 298 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት አምስት (5) ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ከአላማጣ ወደ መቐለ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ መስመር #በፍጥነት እየተጠገነ እንደሚገኝ ኢ.ዜ.አ. ከስፍራው በፎቶ ዘገባ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TikvahFamily

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር በተያያዘ በርካታ ጉዳዮች እየተነሱ እንደሆነ ይታወቃል።

የቲክቫህ - ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትም ጉዳዩ በዛው ዕለት አልያም በቀጣዩ ቀን የሚመለከታቸው አካላት በመነጋገር #በፍጥነት_ይፈቱታል በሚል በትኩረት ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ቀናት አልፎ አሁን ላይ ምዕመኑ ሰልፍ እስኪወጣ አስገድዶታል።

ዛሬ ምዕመኑ በአንዳንድ መስጂዶች በሰልፍ ድምፁን አሰምቷል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት " ሆን ተብሎ በሚመስልና በዘመቻ መልኩ የረመዳን ፆም ወቅትን ጠብቆና አንዳንድ ትምህርት ቤቶች፤ ተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ ጭምር ትምህርት ቤት ውስጥም አትሰግዱም ፤ ወጥታችሁም (ከግቢ) አትሰግዱም ብለዋቸዋል " ሲል ይገልጻል።

አንዳንድ የትምህርት ቤት አስተዳደሮችም ተማሪዎቹን ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነ " ተንኳሽ ንግግር " ተናግረዋቸዋል ብሏል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምንም እንኳን ስለጉዳዩ በግልፅ ያለው ነገር ባይኖርም ትምህርት ከማንኛውም ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴ ነጻ በሆነ ሁኔታ መካሄድ አለበት ሲል አሳውቋል።

ዛሬ የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲሁም አጠቃላይ ከሰሞኑ የነበሩትን ሁኔታዎች በሚመለከት ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በዝርዝር ቀርቧል ፤ ያንብቡ 👇https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-08

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሀገራችን በተለይ በአዲስ አበባ እጅግ በጣም ሙስና ስር ከሰደደበት አንዱ የመሬት ዝውውር ጉዳይ ነው። በዚህ ሂደት አንዳንድ የአስተዳደሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ደላላ ሆነው የተገኙበት ጊዜ መኖሩ ተጠቁሟል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ " " በመሬት ጉዳይ…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ከተናግሩት ፦

" ... በአዲስ አበባ ከተማ በእጅ መንሻ፣ በዝምድናና በተለያዩ ህገወጥ አካሄዶች ጉዳዮቻቸው #በፍጥነት የሚፈጸምላቸው ሰዎች አሉ። በአንጻሩ ደግሞ ህግን ተከትሎ የሚመጣው ደንበኛ ሲንገላታ ይስተዋላል። ችግሩ በተለይ በክ/ከተሞችና ወረዳዎች ላይ ሰፊውን ህዝብ ለእንግልት እየዳረገው ነው። በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ አፋጣኝ ማስተካከያዎችን እየወሰደ ይገኛል። "

#EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ፣ የተመድ ተወካዮች ፣ የሀገራት አምባሳደሮች ከትግራይ ክልል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ይዘው ተመልሰዋል።

ከዚህ ቀደም መልዕክተኞቹ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ የመብራት፣ የቴሌኮም፣ የባንክ እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን #በፍጥነት ወደነበረበት መመለስ ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።

በዚህም የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በዓለማቀፍ ማህበረሰቡ ተወካዮች በኩል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ልከዋል።

ደብዳቤው ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ስልክ ፣ ባንክ፣ መብራት እና የመሳሰሉትን ለመመለስ እና አገልግሎት እንዲጀምሩ ለማድረግ ወደ ክልሉ ገብተው ለሚሰሩ አካላት የደህንነት ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው።

በዚህ #የደህንነት_ማረጋገጫ አገልግሎቶችን ወደነበረበት መመለስ ለማስጀመር ምንም አይነት መሰናክል ሊኖር አይገባም ተብሏል።

ተጨማሪ https://www.eeas.europa.eu/eeas/ethiopia-eu-and-us-special-envoys-visit-mekelle-tigray_en

@tikvahethiopia