TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የጫጫው አደጋ⬆️

ከደብረ ብርሀን ወደ አዲስ አበባ ቃሊቲ መናኸሪያ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ኮድ 3-አማ 12315 ሚኒባስ ከኮድ 3-ኢት 00 229 ኤኔትሪ ድንጋይ ማመላለሻ መኪና ጋር ዛሬ በ12-02-2011 ከቀኑ 6፡00 አካባቢ በአንጎለላና ጠራ ወረዳ አርሴማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ #በመጋጨታቸው የ8 ሰው ህይወት ወዲያው ሲያልፍ የ4 ተሳፋሪዎች ህይወት ደግሞ በደብረ ብርሀን ሪፈራል ሆስፒታል ከገቡ በኋላ
አልፏል፡፡

እንዲሁም በ4 ተጓዦች ላይ ከባድና በ2ቱ ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርም በአደጋው ህይወታቸው ላለፈና ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል ሲል የሰሜን ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በፌስ ቡክ ገፁ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡

በትራፊክ አደጋው በ15 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያጋጠመ ሲሆን በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላይ አካል ጉዳት አጋጥሟል፡፡

የትራፊክ አደጋው ልዩ ስሙ አዲግዳድ በተባለ ቦታ ላይ በትናትናው ዕለት እንዳጋጠመ ነው ተገለፀው፡፡

ምንጭ፡-Dimtsi Weyane
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 13/2011 ዓ.ም. #ሼር #Share @tikvahethiopia

የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች እያፈረሰ ውሏል።
.
.
በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ #ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡
.
.
ዛሬ ጠዋት ጠቅላ ፍርድ ቤት የፌደራል ፖሊስ አቤቱታን ውድቅ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የተሰጠላቸው አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያቤት ወርደዋል።
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናግረዋል።
.
.
ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ #በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ /ኢሳት/ ጋዜጠኞች ዛሬ ኢቢሲን ጎብኝተዋል።
.
.
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት  በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባም በአራት አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
.
.
አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
.
.
በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናግረዋል።
.
.
በለገጣፎ_ለገዳዲ ከተማ ቤታቸው #የፈረሰባቸው ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ፣ OBN፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia