TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ አህመድ ሽዴ⬇️

በአዲስ አበባ ከተማ ሰዎች ታፍሰው ተወሰዱ ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ የተሳሳተ መሆኑንና ህብረተሰቡን ለማደናገር የሚሰራ ስራ እንደሆነ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አቶ #አህመድ_ሽዴ
አስታወቁ።

ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት መግለጫ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

መንግስት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከመስከረም 2 ጀምሮ የፖለቲካ ኃይሎችን ለመቀበል በደጋፊዎቹ መካከል በተፈጠረው ያልተገባ #ፉክክር ግጭቶች መፈጠራቸውን አስታውሰዋል።

እየሰፋ ቤደው ግጭትም በቡራዩ 27 ሰዎች በአዲስ አበባ 28 በጥቅሉ 55 ሰዎች #ህይወታቸው እንዳለፈ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በቡራዩ ከተማ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመና 3 ሺህ 50 ሰዎችም መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

እነዚህን ግጭቶች የብሄር ማስመሰልና በማህበራዊና በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተዛቡ መረጃዎችን በማቅረብ ግጭቱን ለማባባስ እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል።

በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ከግጭቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው 170 ሰዎችና በቡራዩ ከተማ ደግሞ 390 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ሁከቱና ብጥብጡን ለማማባባስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ 1200 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ችግሩን ለመቆጣጠር የፍትህና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ችግሩ በቁጥጥር ስር እንደዋለ አስታውቀዋል።

#መንግስት በደረሰው የህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የተሰማውን #ሀዘን ሚኒስትሩ ገለፀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት ዋነኛው ተዋናይ #መንግስት ነው። በተለይም በአገሪቱ የሚያጋጥሙ ማንኛቸውንም ችግሮችን ደግሞ መንግስት በሃይል ሳይሆን #በትእግስትና #በሰላም የመፍታት ተግባር ደግሞ ዋነኛው ተግባር ነው ብለዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tivahethiopia
"የጎንደር ሃረገ ስብከት መንግስትን አስጠነቀቀ!"

#መንግስት ይህን #ሐጢአትም #ወንጀልም የሆነዉን ከኢትዮጵያዉያን ባህልና ሐይማኖት ስነልቦናም ጋር የማይጣጣመዉን #ግብረሰዶማዊነትን ለማስፋፋት በግብረሰዶማዉያን የተጀመረዉን እንቅስቃሴ #እንዲያስቆም የሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ጠየቀ፡፡ እንዲሀም ሲል የማስጠንቀቂያ መልዕክቱን ለመንግስት አስተላልፏል፡-

1) ጉብኝቱ ከሐይማኖት፣ ከህግ፣ ከሞራልና ከሃገሪቱ ባህል ጋር የሚጻረር ስለሆነ ፈቃድ እንዳይሰጠዉ፤ ከተሰጠዉም እንዲታገድ እንጠይቃለን፤

2) መንግስት በዚህ የጉብኝት መርሃ ግብር ላይ ያለዉን አቋም በአጭር ጊዜ ዉስጥ እዲያሳዉቀን እንጠይቃለን።

3) ይህ ሳይሆን ቀርቶ መርሀ ግብሩን ወደ ተግባር ለማዋል ቢሞክር ለሚፈጠረዉ ማንኛዉም ችግርና ቀዉስ መንግስት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

" ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል " - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ሲሚንቶ በነጻ ገበያ እንዲሸጥ ተወሰነ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዚህ በፊት የነበረው የሲሚንቶ ሽያጭ መመሪያ መቀየሩን ገለፀ።

መመሪያው የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሳበት እንደነበር ገልጾ በዚህም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ሲሚንቶን በቀላሉ እንዳያገኙ አድርጓቸው እንደነበር አሳውቋል።

በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል ነው ተብሏል።

የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ተገልጿል።

#መንግስት ከግብይቱ የወጣ ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም መንግስት ሽያጩ ያለ ደረሰኝ እንዳይካሄድ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ሚኒስቴሩ አሳውቋቃ።

በግብይቱ ውስጥም ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና ደረሰኝ ግዴታ መሆናቸውን የተጠቆመ ሲሆን እያንዳንዱ ፋብሪካ የተደራሽነት አድማሱን በማስፋትም አከፋፋዩን የመምረጥ ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።

ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል ብሏል ሚኒስቴሩ።

ከፋብሪካ ሲሚንቶ የሚወጣ ማንኛውም ተሽከርካሪ የመዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደሚኖርበት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳስቧል።

Credit : #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች [ቦጬሳ ቀበሌ - ጭሬ] ካለፈው እሁድ ረፋድ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱ እንዲሁም በዜጎች ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በአከባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦች አስታውቋል።

ግጭቱ በተቀሰቀሰባቸው ቦታዎች በርካታ ዜጎች መፈናቀላቸውን ገልጸው #መንግስት ለአከባቢው በቂ የሆነ ትኩረት እንዲሰጥ ፤ የዜጎችንም ደህንነት እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በአካባቢው ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተልን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

ወላጆች ስለ ት/ቤት ክፍያ ጭማሪ ምን አሉ ?

----

የካ አባዶ አካባቢ በሚገኝ አንድ ትም/ ቤት ልጃቸውን የሚያስትምሩ ወላጅ የልጃቸው ወርሃዊ ክፍያ 1450 ብር እንደነበና 65.7 በመቶ በመጨመር 2500 ብር እንደተደረገ ገልጸዋል። " ወላጆች እንዲጨምርብን አንፈልግም ነበር ግዴታ ከሆነም ከ30 በመቶ በላይ እንዳይጨምሩ ተከራክረን ነበር። " ያሉት እኚሁ ወላጅ " ት/ቤቱ ግን 80 በመቶ እንጨምራለን ብለው ወላጅ ባይስማማም 65.7 በመቶ ወስነዋል " ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

----

" መንግስት ካለ ለምን መጨመር የሚቻለውን ከፍተኛ ተመን አይወስንም ? " ሲሉ የጠየቁ አንድ የተማሪ ወላጅ " እመኑኝ በዚህ ሁኔታ ብዙዎች ት/ት ሊያቆሙ ይችላሉ " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

----

በአንድ የግል ት/ቤት ውስጥ ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ት/ቤቱ መንግስት ምንም ሊያስገድደው እንደማይችል እና ነፃ ገበያ እንደሆነ ተናግሮ ምንም ለውጥ እንደማናመጣ ነገረን ያሉ ሲሆን "  መንግሥት ስምምነት ሳይደረግ ዋጋ መጨመር አይቻልም ማለቱ ተስፋ ሰጥቶናል " ብለዋል ፤ እሳቸው ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት 78% መጨመሩንና በተርም / በሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀን 7600 እንከፍል የነበረውን 13324 ነው ያደረጉብን ሲሉ ገልጸዋል።

----

አንድ ወላጅ ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ት/ቤት የ65 በመቶ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን ገልጸው " በዚህ ኑሮ ውድነት ይህን ማድረግ ግፍ ነው ፤ የእኛ የወላጆች ገቢ ባላደገበት ይህ እንዴት ይድረጋል ፤ ለእኛስ አይታሰብም ወይ ? ሲሉ መልዕክታቸውን ልከዋል።

----

በኮ/ቀ በሚገኝ የአንድ የግል ትምህርት ቤት የወለጅ ኮሚቴ ነኝ ያሉ አንድ የቲክቫህ አባል " እንደ ኮሚቴ ተስማምተን የነበረው 200 እስከ 300 ጭማሪ ነበር ፤ ለምሳሌ በዚህ የት/ዘመን 1300 + 300 = 1600 ፤ 2016 ነበር የተስማማነው አሁን ግን 600 ጭማሪ አድርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል። " ይህ ለምን እንደሆና ምክንያቱን በግልፅ አላወቅንም " ያሉት እኚሁ የወላጅ ኮሚቴ " ለሚቀጥለው ዓመት 1900 ተብሎ በደብዳቤ አሰውቀውናል " ሲሉ አክለዋል። " ልጆቻችንን ከመስወጣተችን በፊት ትምህርት ቢሮ ክትትል ያድርግ !! " ሲሉ አደራ ብለዋል።

----

" መንግስት ውይይት ሳይደረግ መጨመር አይቻልም ብሏል ፤ ውይይት ሲባልስ #ስንት_ሠው_ተገኝቶ ነው ውሣኔ ማሣለፍ የሚችለው ? " ሲሉ የጠየቁ አንድ ወላጅ " ይህ በራሡ #ክፍተት ያለው አገላለፅ ነው፤ እንዳሻችሁ እንደማለት ነውና መንግስት የኑሮ ጫና የሚፈታተንን ሳያንስ ሌላ ጫና ለመሸከም የሚችል ጫንቃ የለንምና ፤ የፈጠራትን ክፍተት መንግሥት ራሡ ይዝጋት እንላለን " ብለዋል። "

----

በአንድ የግል ት/ቤት ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ፤ ት/ቤቱ በቀጣይ አመት ከ1300 ባንዴ 2700 ጭማሪ ማድረጉን እና ያልፈለገ መልቀቅ ይችላል እንዳሏቸው ገልጸዋል። " በዛላይ ቀጣይ አመት በተርም ነው ምከፍሉት አሉን " የሚሉት ወላጅ " ሁለት ልጆቼን ለማስተማር 2600 ከፍዬም አንገዳግዶኝ ነበር የባሰው መጣና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ  " ብለዋል።

----

" እኔ ልጄን የማስተምርበት ት/ት ቤት ወደ 120% ነው የጨመረው " ያሉ አንድ ወላጅ " ከአንድም ሁለት ጊዜ ከት/ት ቤቱ አሰተዳደር ጋር ብንሰበስብም መስማማት ላይ ግን መድረስ አልቻልንም። " ብለዋል። " እንደውም ት/ት ቤቱ መጀመሪያ 22ዐ% ነበር ያቀረበው ከብዙ ክርክር በኋላ ነው ወደ 120% የወረደው ሆኖም ግን ከዚህ በታች አሻፈረኝ ብሏል። ብዙ ወላጅም በጣም ተማሯል። " ሲሉ ገልጸዋል።

----

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነኝ ያሉ አንድ ወላጅ ፤ ልጃቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት 40 % ጭማሪ መደረጉን ገልጸው በዚህ ኑሮ ውድነት ፤ በዛ ላይ ሁለት / 2 / እና ከዛ በላይ ልጆች ያሏቸው ምን ይሆናሉ ? ሲሉ ሁኔታው እጅግ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል።

----

አንድ ወላጅ ልጆቻቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ከጭማሪ ጋር በተያያዘ ከወላጆች ጋር ስምምነት እንደሌለ ገልጸዋል። ትምህርት ቤቱ ግን " የፈለገ ልጆቹ ያስቀጥል፤  ያልተስማማ ሌላ ት/ቤት ይቀይር " የሚል ምላሽ መስጠቱን አመልክተዋል " መንግስት የሰጠው አቅጣጫ ወላጆች ሳይስማሙ ማለት የሹፈት ውሳኔ ነው ፤ ሌላ ትም/ቤት ፈልጉ ከተባለ ለልጃችን ስንል ሳንስማማ እንቀጥላለን ፤ #መንግስት ነው ይህን #መቆጣጠር ያለበት፤ እውነቴ ነው በዚህ አካሄድ ብዙ ልጆች ከትምህርት ውጪ ይሆናሉ። " ሲሉ ስጋታቸውን አስረድተዋል።

----

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ ወላጅ " ከክፍያ ጭማሪ በተያያዘ እኛ ወላጆች ምንም ባልተስማማንበት ሁኔታ ነዉ እየጨመሩ ያሉት ፤ በአካባቢያችን ከ50% በላይ ነዉ ጭማሪ የተደረገው እና የሚመለከተው አካል ከጊዜዉ ጋር ታሳቢ በማድረግ መፈትሔ እንዲሰጥ ። " ሲሉ ጠይቀዋል።

----

አንድ ወላጅ አምስት (5) ልጆቸውን በሚያስተምሩበት የግል ትምህርት ቤት በአመት አጠቃላይ 434 ሺህ ብር ሲከፍሉ እንደነበር አሁን ግን 100 % ጭማሪ (868,000 ብር) እንደሚደረግ እንደተነገራቸው ገልጸዋል ፤ መንግሥት በግል ት/ቤቶች እየተደረገ ያለውን ነገር እንዲከታተልና መፍትሄ እንዲፈልግ አደራ ብለዋል።

----

በአንድ የግል ትምህርት ቤት ልጃቸውን የሚያስተምሩ ወላጅ ትምህርት ቤቱ የ60,000 ሺህ ብር ጭማሪ ለማድረግ እንደወሰነና ለዩኒፎርም እና ለመሳሰሉት እስከ 30,000 ብር ጭማሪ እንደተደረገ አመልክተው የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

(ተጨማሪ ወላጆች የላኩይ መልዕክት በዚሁ ፅሁፍ ላይ #edit ተደርጎ ይካተታል)

በአጠቃላይ እጅግ በጣም በርካታ የተማሪ ወላጆች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መልዕክታቸውን ልከዋል።

የወላጆቹ ሃሳብ ሲጠቃለል ፤ በዚህ የኑሮ ጫና ወቅት እጅግ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ መንቀሳቀስ በምንም መልኩ ተቀባይነት እንደሌለውና ት/ቤቶችም ይህንን ተገንዝበው ማስተካከያ ማድረግ እንዳለብቸው የሚያሳስብ ነው።

ከምንም በላይ ደግሞ ፤ #መንግስት በሁሉም የግል ት/ቤቶች ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ዜጎችን ወደ ምሬት ውስጥ የሚከቱ ተግባራትን ማስቆም እንዳለበት የሚያገነዝብ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TayeDendea

አቶ ታዬ ደንደአ ትላንት በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ የስንብት ደብዳቤ አያይዘው ከለጠፉ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ጠንካራ ቃላትን ተጠቅመው ትችት ከሰነዘሩ በኃላ #በሕግ_ሊያስጠይቃቸው የሚችል ጉዳይ ይኖር እንደሆነ ተጠይቀው ነበር።

አቶ ታዬ ፤ " በሕግ መጠየቅ ምን ችግር አለው ፣ ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ " የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

በሕግ ሊጠየቁ የሚችልበት እድልም እንደሌለ ተናግረው ነበር።

ዛሬ የፀጥታ እና የደህንነት የጋራ ግብረኃይል አቶ ታዬን ደንደአን በሕግ ቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሲሆን መኖሪያ ቤታቸው ላይም ብርበራ አድርጓል።

ግብረ ኃይሉ አቶ ታዬ ደንደአን ፦

- በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሲፈፀሙ በነበሩ የሽብር ተግባራት በተለይም ደግሞ #ከእገታ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት አሳውቋል።

(አቶ ታዬ ደንደአ በ #ሰላም_ሚኒስቴር ውስጥ ሆነው በተለያዩ ጊዜ በሚፈፀሙ የእግታ ጉዳዮች እጃቸው እንዳለበት የታወቀው መቼ ነው ? ከዚህ ቀደም ታውቆ ከሆነ ለምን እስከዛሬ ዝም ተባሉ ለሚለው ጉዳይ የተብራራ ነገር የለም)

- የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰላምን ለማስፈን ከመስራት ይልቅ ከፀረሠላም ኃይሎች ጋር ተሳስረው ለጥፋት ተልዕኮ በህቡዕ ሲሰሩ ነበር ብሏቸዋል።

- መንግስት እና የፓርቲ መዋቅሩን በሴራ ለመናድ በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበር ብሏቸዋል።

- መንግሥት በሽብርተኝነት ከፈረጀው ከኦነግ ሸኔ አመራሮች እና በሽብር ወንጀል ከሚጠረጠሩ ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ትስስር ፈጥረው መንግስትን በአመፅ፣ በሽብርና በትጥቅ ለመጣል ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል ብሏል።

አቶ ታዬ ደንደአ ከሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን እና በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ትላንት ታሕሳስ 1 በኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተፃፈ ደብዳቤ ከስልጣን እንዲነሱ ተደርገዋል።

አቶ ታዬ ከስልጣን ለመነሳታቸው ምክንያቱ ጦርነት ተቃውመው ስለእርቅ ስለተናገሩ እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል። " በጦርነቱ ጊዜ ጦርነቱን ስደግፍ ሲያበረታቱኝ ነበር ሕዝቡ ይታረቅ ስንል ነው ያመማቸው " ያሉት አቶ ታዬ ሰላምን በመደገፌ ነው ከስልጣን የተነሳሁት ብለዋል።

ግብረ ኃይሉ ግን አቶ ታዬ ስልጣን ላይ ቁጭ ብለው እራሳቸው ያሉበትን #መንግስት እና #ፓርቲ ለመናድ መንግስትንም በሽብር ትጥቅ ለመጣል ከፀረሠላም ኃይሎች ጋር ሲሰሩ እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

ልክ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ሲያውቁ ደግሞ #ታጋይ ለመምሰል በየማህበራዊ ትስስር ገፆች ፀረ-ሰላም ፅሁፎችን እና ንግግሮችን ሲያስተላልፉ ነበር ብሏል።

@tikvahethiopia