TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሜቴክ ፕሮጀክቱን ተነጠቀ⬇️

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን (ሜቴክ) በግምባታ ሂደት ላይ የነበረዉና ይጠናቀቃል ተብሎ ከታቀደለት ጊዜ በኋላም መጠናቀቅ ያልቻለዉ የኦሞ ኩራዝ አንድ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ከሜቴክ መነጠቁን ዋልታ የዉስጥ ምንጮቼ ገልፀውልኛል ብሎ ዘግቧል፡፡

ከኩራዝ አንድ #በኋላ ግንባታቸዉ በቻይና ኩባንያዎች የተጀመሩት የኩራዝ አንድና #ሁለት ፕሮጀክቶች ግንባታቸዉ #ተጠናቆ ማምረት የጀመሩ ሲሆን #በሜቴክ ግንባታዉ የተጀመረዉ ኩራዝ አንድ ግን ግንባታዉ እስካሁን #አልተጠናቀቀም፡፡

©ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፅጌሬዳ_ግርማይ ስለፅጌሬዳ ግርማይ ግድያ ጓደኞቿ ምን አሉ ? አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ ከአባቷ ከአቶ ግርማይ ገ/መድን እና ከእናቷ ከወ/ሮ ያበሻ ያዘዘው በወልቃይት አድ ረመጽ ከተማ በ1993 ዓ/ም ነው የተወለደችው። የመሰናዶ ትምህርቷን በወልቃይት ጌታቸው አዘናው 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንደተከታተለች ፤ ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመመደብ በሆቴልና…
#ፅጌሬዳ_ግርማይ

የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን ግድያ በተመለከተ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ መረጃ ሰጥቷል።

ሰኞ ዕለት ህይወቷ ያለፈው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተጠረጠረ ተማሪ ትላንት ከሰዓት ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ምስክርነት የሰጡ የተጠርጣሪው #ሁለት_ጓደኞቹ የሚከተለውን ብለዋል :-

"ተማሪ ፅጌሬዳ ከተጠርጣሪ ወንጀለኛው ጋር ግንኙነት የነበራት ሲሆን በመሀል ውጪ የነበረ ጓደኛዋ ስለመጣ ግንኙነቱን ማቋረጥ እንደምትፈልግ ገልጻለታለች። በዚህም ተጠርጣሪው ደስተኛ እንዳልነበረና ዛቻና ማስፈራሪያ በጓደኞቿ በኩል ይልክላት ነበር።"

ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ከሁለቱ ጓደኞቹ በአንደኛው ስልክ በመደወል ወደ አስተዳደር ህንጻ አካባቢ እንድትመጣ አድርጓል።

በወቅቱ ስልክ ደዋዩና ሌላኛው ጓደኛው አብረውት ነበሩ። "ጉዳያችንን እኛ እንጨርሳለን እናንተ ሂዱ" ብሏቸው ብዙም ሳይቆይ በስለት እንደወጋት ጓደኞቹ ምስክርነት ሰጥተዋል።

ሟች ልቤን ብላ ስትጮህ በቅርብ ርቀት የነበሩ የግቢው ጥበቃ አባላት ደርሰው ለማምለጥ የሞከረውን ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውለውታል።

ተጠርጣሪው በሕግ ጥላ ስር ውሎ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ሲሆን ፍ/ቤት ቀጣይ ቀጠሮ እንደሰጠው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በድሩ ሂሪጎ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የሟቿ አስክሬን ትላንት ቤተሰቦቿ ወደሚገኙበት ወልቃይት ወረዳ አድ ረመጽ ከተማ መላኩንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በ20 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ተማሪ ፅጌሬዳ በዩኒቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
ለግል_መገልገያ_እንዲውሉ_ወደ_አገር_የሚገቡ_ወይም_ከአገር_የሚወጡ_ዕቃዎችን_ለመወሰን_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር.PDF
ለግል መገልገያ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆነው የሚገቡ ዕቃዎች የትኞቹ ናቸው ?

- ሲጋራ | መለኪያ ➤ ግራም |  የሚፈቀደው መጠን ➤ 200

- ሲጋር | መለኪያ ➤ በቁጥር |  የሚፈቀደው መጠን ➤ 20

- ብትን ትንባሆ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 250

- የአልኮል መጠጥ | መለኪያ ➤ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 2

- ለስላሳ ሽቶ | መለኪያ ➤ ሚሊ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 500

- ሽቶ | መለኪያ ➤ ሚሊ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 500

- #ሞባይል | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 2 (#ሁለት)

- #ላፕቶፕ | መለኪያ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን 1 (#አንድ)

- #የፎቶግራፍ_ካሜራ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- #ዊልቸር | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- #የእጅ_ሰዓት | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- የፂም ወይም የፀጉር መላጫ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- የፀጉር ማድረቂያ | መለኪያ ➤ በቁጥር |  የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- የፀጉር መተኮሻ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1

- መንገደኛው የሚጠቀምባቸው መድሃኒቶች እና የህክምና በቁጥር መገልገያዎች | መለኪያ ➤በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ ለአንድ ሰው በሚያስፈልግ መመጠን

- በጉዞ ወቅት ጥቅም ላይ የሚውሉ እና ለቤተሰብ የሚያገለግሉ ፣ ልብሦች፣ ጫማዎች፣ እና የፅዳት እቃዎች | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ ለአንድ ቤተሰብ ከሚያስፈልገው ያልበለጠ

የተሻሻለው የግል መገልገያ እቃዎች - የጉምሩክ መመሪያ https://t.iss.one/tikvahethiopia/73728

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ከ19 ወራት በኃላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን መንገደኞችን ጭኖ መቐለ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረው የመንገደኞች እና የቤተሰቦች ስሜት። #Peace #ETHIOPIA Photo Credit : Tigrai Television @tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአርብ ታህሳስ 21 ቀን  2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መቐለ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን  ወደ #ሁለት ከፍ ማድረጉን አስታውቋል።

በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ እንደሚጨምር ገልጿል።

አየር መንገዱ ደንበኞቹ ባሉበት ቦታ ላይ ሆነው በድረገፅ እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን አሳውቋል።

www.ethiopianairlines.com 
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ " የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና/ቻን " እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ዝግጅት ዛሬ ሞሮኮ ካዛብላንካ በሰላም መድረሱን የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

ቡድኑ ወደ ሞሮኮ ከመሄዱ በፊት በሀገር ውስጥ ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል።

በሞሮከ የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ለሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የሚያደርግ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ እና ሰኞ ከሞሮኮ #የቻን ቡድን ጋር #ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ውድድሩን የተመለከቱ መረጃዎችን በስፍራው ከሚገኙት የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት በ @tikvahethsport ማግኘት ይቻላል።

ፎቶ ፦ Tikvah Sport

@tikvahethiopia
#ኦዲት

#ለተከታታይ_ዓመታት ለተገኘበት በርከት ያለ የኦዲት ክፍተት ማስተካከያ ማድረግ እንደተሳነው የተገለፀው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከአመራር መቀያየር ባለፈ ጥብቅ ሪፎርም እንደሚስፈልገው የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታውቋል።

ይህንን ያስታወቀው፤ የሕ/ተ/ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2014 / 15 በጀት ዓመት ሒሳብ ኦዲት ላይ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ሲደረግ ነው፡፡

መስሪያ ቤቱ ምን አለ ?

ኮሚሽኑ ፦
📄ለሚፈጽማቸው ክፈያዎች ደረሰኝ ባለማቅረብ፣
📄ኮፒ ደረሰኝ መጠቀም፣
📃በኮፒ ደረሰኝ ሂሳብ ማወራረድ፣
📄ያልተፈቀደ ክፈያ በመፈጸም፣
📄ለተከፈለ ገንዘብ ማስረጃ ባለማቅረብ፣ እንዲሁም #በቢሊዮኖች ብር የሚቆጠር ተከፋይ እና ተሰብሳቢ ውዝፍ የኦዲት ሪፖርት ተገኝቷል።

- ከሳዑዲ ከስደት ለተመለሱ 102 ሺህ ኢትዮጵያውያን ለኪስ አበል እንዲሁም ለቤት ኪራይ 5.2 ሚሊዮን ብር ማስረጃ ሳይቀርብ ተከፍሏል። ተከፈለ ለተባለው ለዚህ ገንዘብ ሰነድ ማግኘት ባለመቻሉ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አልታቻለም።

- ለምግብ ዝግጅት ድርጅት ተብሎ የተከፈለና በወጪ የተመዘገበ 2.9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ዋጋው ከ65.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ 14 ሺህ ኩንታል ዱቄት " ናህሊ ዱቄት ፋብሪካ " ለተስኘ ድርጅት የተከፈለ ተብሎ የቀረበ ቢሆንም የቀረበው ደረሰኝ ግን ኮፒ ነው።

- በወጪ ሒሳብ ለተመዘገበ 79 ሚሊዮን ብር ለኦዲት ሥራ የሚፈለጉ የወጪ ማስመስከሪያዎች (ቫውቸሮች) ከደጋፊ ሰነዶች ጋር እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ማስረጃ ሊቀርብ አልቻለም።

- ያልተወራረደ 881.5 ሚሊዮን ብር ተሰብሳቢ ሒሳብ መኖሩ በኦዲት ሪፖርት ቢረጋገጥም፣ ከኦዲት ግኝት በኋላ የተወሰደ ማስተካከያ የለም።

➡️ በወቅቱ ያልተወራረደ 39.7 ሚሊዮን ብር ተከፋይ ሒሳብና ያልተከፈለ ሲሆን ከኮሚሽኑ መደበኛ በጀት 37.6 ሚሊዮን ብር በሥራ ላይ አልዋለም።

በተጨማሪም ፦

* ውኃ የሚያስገቡ እና ጣሪያቸው የሚያፈሱ መጋዘኖች ተገኝተዋል።

* በቆይታ ብዛት የተበላሸ ብስኩት ሳይወገድ በግምጃ ቤት ተገኝቷል።

* የቆይታ ጊዜያቸው የማይታወቅና በውስጣቸው ምን እንዳለ የማይታወቅ የታሸጉ 9 ኮንቴነሮች በመጋዘን ግቢ ውስጥ ተገኝቷል።

* የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ ፦
🔹ሴሪላክ የዱቄት ወተት፣
🔹የወይራ ዘይት፣
🔹የምግብ ዘይት፣
🔹ብዛት ያላቸውና ጊዜያቸው ያለፈባቸው ቴምሮች፣
🔹የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ተገኝቷል።

* በእህል መጋዘኖች ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሊያልፍ #ሁለት እና #ሦስት ወራት የቀራቸው አልሚ ምግቦች፣ ሳሙናዎችና እህሎች ተገኝቷል።

የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም የኦዲት ሪፖርት ላይ ለመምክር በተጠራው ውይይት አለመገኘታቸው ቋሚ ኮሚቴውን አስቆጥቷል።

በወቅቱ ውይይቱ ላይ የተገኙት ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ኮሚሸነሩ የቀሩት ሌላ ተልዕኮ ስለነበራቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ ምን አሉ ?

° ኮሚሽኑ ኃላፊዎችን #ከመቀያየር ባለፈ መሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልገዋል።

° በ2014 ዓ/ም የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ኦዲተሮች ለጊዜያዊ የኦዲት ሥራ የተረከቡትን ቢሮ ኦዲት አድርገው በሚወጡበት ጊዜ የኮሚሽኑ ሠራተኞች በመግባት #ሰነድ እያወጡ መሆኑን መረጃ አለኝ።

° ይህ ኮሚሽን ለፈጸማቸው ክፍያዎች ሰነድ ማቅረብ አለመቻሉ መሠረታዊ ችግሩ ነው።

° ከዚህ በፊት የበላይ ኃላፊው ቢታሰሩም ኮሚሽኑ ግን አሁንም ሰንኮፉ አልተነቀለም፣ በመሠረታዊነት ችግሩ አልተቀረፈም።

° በመጋዘኖች ውስጥ በሚገኙ ንብረቶች ከፍተኛ ችግር አለ። ገንዘቡ አንዴት እንደሚመጣ እናውቀዋለን ነገር ግን እዚህ ያለው ሥራ የተዝረከረከ ነው፡፡

° በ2013 ዓ.ም. #ድሬዳዋ እና #ሻሸመኔ በሚገኙ መጋዘኖች ከታዩ ችግሮች በመነሳት የኦዲት አስተያየት የተሰጠንባቸው ጉዳዮች በ2014 ዓ.ም በድጋሚ ኦዲት ሲደረግ በነበሩበት እንጂ ተስተካክለው አልተገኙም።

° " ደመወዝ የምንበላበት ተቋም ነው፣ ስለዚህ እዚያ ያለውንም ሥራ ልክ እንደ ቤታችን ማየት አለብን፡፡ ይህ ሁሉ ቁሳቁስ የሚገዛው በብድር ነው እናውቃለን፡፡ እዚህ አምጥተን በአግባቡ የማይውል ከሆነ፣ መሬት ላይ የሚደፋና ከጋዝ ጋር ተቀላቅሎ የሚበላሽ ከሆነ ሥራው ትርጉም አልባ ነው "

° በዚህ ውይይት ላይ ያልተገኙት #ኮሚሽነሩ የቀሩት ዕርዳታ ለማፈላለግ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ተቋሙ የተገኘውን ንብረት በተገቢው መንገድ ማስተዳደር ካልተቻለ፣ ዕርዳታ ማፈላለጉ ብቻ ትርጉም የሌለውና በቀዳዳ በርሜል ውኃ እንደመሙላት የሚቆጠር ነው።

የገንዘብ ሚኒስቴር ፤ የኢንስፔክሽን መምርያ ኮሚሽኑ በኮፒ ደረሰኝ ሒሳብ እንደሚያወራረድ በተደጋጋሚ ቢነገርም ሊስተካከል ባለመቻሉ ይህንን ያደረገ ኃላፊ መጠየቅ አለበት ብሏል።

More - https://telegra.ph/Reporter-12-14-2

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ "ሪፖርተር ጋዜጣ " መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
🚨 #ዲላ 🚨

ዛሬ በዲላ ከተማ 10 ሠዓት ገዳማ ንፋስ ቀላቅሎ በዘነበው ከባድ ዝናብ #ሁለት የአንድ ቤተሰብ #ህጻናት ህይወታቸው አልፏል።

2 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ቀላል ጉዳት የደረሰባቸውም ሰዎች አሉ።

ንብረት ላይም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል።

በርካታ ዛፎች እና በርካታ የኤሌክትሪክ ፖሎች ወድቀዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይልም ተቋርጧል።

ነዋሪው የኤሌክትሪክ ኃይል ተስተካክሎ ወደ ቦታው እስኪመለስ እንዲታገስና እራሱ ከተለያዩ አደጋዎች እንዲጠብቅ የከተማው አስተዳደር አደራ ብሏል።

@Tikvahethiopia