" የታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስኪሆን ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ ይቀጥላል " - ትራንስፖርት ቢሮ
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱን በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናት ይፋ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስኪሆን ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎችም የታሪፍ መጠኑ ይፋ ሳይሆን ምንም ዓይነት ዋጋ ባለመጨመር አገልግሎቱን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል።
ምንጭ፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እስከ ከሜሴ ያለው መስመር ጥገና ተጠናቋል። ከካራቆሬ - ከሜሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹንና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ከሥርጭት ኔትወርክ መስመሮች ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ በርብርብ ሲሰራ ቆይቶ ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል ማግኘት ችለዋል፡፡ ከደብረብርሃን ኮምቦልቻ ድረስ ያሉት ከተሞች…
" ኮምቦልቻና ደሴ ኤሌክትሪክ ዛሬ ማግኘት እንዲችሉ በርብርብ እንሰራለን "- የኢ.ኤ.ኃ. የጥገና ባለሙያዎች
በሸዋ ሮቢት - ኮምቦልቻ መስመር የተጎዳውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የሚጠግነው የጥገና ቡድን አባላት የኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ዛሬ ኤሌክትሪክ ማግኘት እንዲችሉ በርብርብ እንሰራለን ብለዋል።
የጥገና ቡድኑ ትናንት ምሽት የጥገና ሂደቱን፣ በየከተሞቹ የደረሰውን ጉዳትና የህብረተሰቡን ስሜት የተመለከተ አጠቃላይ ግምገማ ካደረገ በኋላ ዛሬ የኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ የቻለውን ያህል ጥረት እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል፡፡
የጥገና ቡድኑ ትናንት ከካራቆሬ - ከሜሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና አጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል።
የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ የቴክኒክ ቡድኑ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከሸዋሮቢት እስከ ከሚሴ ያለውን መስመር ጠግኖ ለአገልግሎት ለማብቃት ያደረገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
አቶ ሀብታሙ ፥ " ከባድ መስዋዕትነት በመክፈል የህዝቡን ችግር ለመፍታት ያደረጋችሁትን ርብርብ ተቋማችንና ህብረተሰቡ ሁሌም ሲያስታውሰው ይኖራል " ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

#NewsAlert
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
መንግስት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ይሁኝታ አግኝቶ ሲመረጥ ቃል ከገባባቸው አገራዊ ጉዳዮች መካከል ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ህዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ አካታች አገራዊ ምክክሩን ተግባራዊ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቧል።
ምክር ቤቱም በቀረበው የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።
#PMOEthiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" የጦር አውሮፕላኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል " - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር
በጥቁር ባህር በኩል #የሩሲያን ድንበር አቋርጠው ሊገቡ የነበሩ #የፈረንሳይ እና #የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በSU-27 የሩሲያ ጄቶች ተጠልፈው መመለሳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እኤአ ታህሳስ 9 የሩሲያ የኤሮስፔስ መቆጣጠሪያ ሲስተም በራሪ አካላት ጥቁር ባህርን አልፈው ወደ ሩሲያ ድንበር እየበረሩ እንደሆነ ማመላከታቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ተጠቅሷል።
የሩሲያ ኤርክራፍት በረራ ቡድን ወደሩሲያ ድንበር አቅጣጫ ሲበሩ የነበሩት Mirage-2000 ጀትና ከፈረንሳይ አየርና ስፔስ ሃይል የመጣች የፈረንሳይ Rafale ጄት እንዲሁም የአሜሪካ ጦር CL-600 ያሳተፈ የጥናት እንቅስቃሴ ነበር ተብሏል፡፡
የፈረንሳይ KC-135 አውሮፕላን ነዳጅ የምትሞላ እና እጀባ የምታደርግ በጥቁር ባህር ላይ ሲበሩ እንደነበር መግለጫ አመልክቷል፡፡
የጦር ጄቶች አማካኝነት የጦር አውሮፕኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል ያለው መግልጫ የሩሲያ ውጊያ ጄቶች የጦር አውፕላኖቹን ከድንበር ወደ ኋላ ከመለሱ በኋላ በሰላም መመለሳቸው ተገልጿል።
መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።
ቪድዮ : የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር

#ጥንቃቄ
" የተሸከርካሪ ሰሌዳን እናስጨርሳለን በማለት ገንዘብ ከሚጠይቁ ግለሰቦች ተጠንቀቁ " - የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
የተሸከርካሪ ሰሌዳን እናስጨርሳለን በማለት ገንዘብ ከሚጠይቁ ግለሰቦች ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የተሸከርካሪ ሰሌዳን ህትመትና ስርጭት ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በውክልና ተረክቦ ስራውን በማከናወን ላይ ያለው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት መልዕክቱን አስተላልፏል።
የድርጅቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን አምባቸው በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ የተሸከርካሪ ሰሌዳን በህጋዊ መንገድ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር በመስጠት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የተፈጠረው የህትመት ስርጭት አከናዋኝ የባለቤትነትን ለውጥ በመጠቀም አንዳንድ ግለሰቦች የሰሌዳ ቁጥር የሚፈልጉ አሽከርካሪዎችን ጉዳይ እናስፈፅማለን በማለት የማታለል ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን አንስተው እነዚህን ወንጀለኞች ለማጋለጥ ድርጅቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ስራውን ከመረከቡ በፊት በቀን በአማካኝ 300 የሰሌዳን ቁጥሮች ይታተሙ እንደነበር ገልፀው በአሁኑ ጊዜ የዕረፍት ቀናትን ጨምሮ በምሽት ክፍለ ጊዜ ህትመትና ስርጭት በመከናወኑ በቀን በአማካኝ ከ3 ሺህ በላይ የተሸከርካሪ ሰሌዳዎችን በመታተም ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጉዳይ እናስፈፅማለን በማለት ገንዘብ የሚጠይቁ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ህብረተሰቡ ለፖሊስ መጠቆም አለበት ያሉት አቶ ሰለሞን አምባቸው ድርጅቱ በተቀላጠፈና በአጭር ጊዜ በህጋዊ መንገድ የሁሉንም ዓይነት ተሸከርካሪዎች የሰሌዳ ቁጥር እያተመ በማሰራጨት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

#CustomsCommission
" የጀመርነውን እርምጃ አጠናክረን እንቀጥላለን " - የጉምሩክ ኮሚሽን
የጉምሩክ ኮሚሽን ፥ የግል መገልገያ እቃዎችን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ለማስገባት ለመንገደኞች የተፈቀደውን መመሪያ ተገን አድርገው ከመመሪያው ውጭ በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተመላላሽ መንገደኞች በመንግስት ገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ ጫና እያደረሱ በመሆኑ የተጀመረው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኮሚሽነር ደበሌ ፥ የዓለም አቀፍ መንገደኞች ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ይዘዋቸው ስለሚመጡ እና ከቀረጥ ነጻ ስለተፈቀዱ ብሎም ስላልተፈቀዱ የግል መገልገያ እቃዎችን ለመወሰን ከዚህ በፊት መመሪያ ቁጥር 51/2010 ጸድቆ ስራ ላይ መዋሉን ጠቅሰዋል፡፡
ኮሚሽኑ ባደረገው ጥናት መሰረት ከመመሪያው ዓላማ ውጭ አንዳንድ ተመላላሽ መንገደኞች በህገወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው መንግስት በዘርፉ የሚያገኘውን ገቢ እንዲያጣ እና በንግድ ስርዓቱም ላይ ፍትሀዊ ውድድር እንዳይኖር እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
እነዚህ በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተመላላሽ መንገደኞች የሚያደርጉት የገንዝብ ዝውውር በህጋዊ የፋይናንስ ተቋማት የሚከወን ባለመሆኑም ህገወጥ የገንዝብ ዝውውር እንዲስፋፋ፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስና የንግድ ስርዓቱ እንዲታወክ እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።
መመሪያውን ተላልፈው የተገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እና ወደ ህጋዊ የንግድ መረብ እንዲገቡ ኮሚሽኑ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ አለመቻላቸውን ኮሚሽነር ደበሌ ገልጸው በእነዚህ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ከሌሎች የጸጥታ አካላትም ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

#CustomsCommission " የጀመርነውን እርምጃ አጠናክረን እንቀጥላለን " - የጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ኮሚሽን ፥ የግል መገልገያ እቃዎችን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ለማስገባት ለመንገደኞች የተፈቀደውን መመሪያ ተገን አድርገው ከመመሪያው ውጭ በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተመላላሽ መንገደኞች በመንግስት ገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ ጫና እያደረሱ በመሆኑ የተጀመረው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል…
#CustomsCommision
የጉምሩክ ኮሚሽን አድርጌዋለሁ ባለው ጥናት " መመሪያ 51/2010 " ሽፋን በማድረግ በህገወጥ ንግድ ላይ የመንግስት ሰራተኞች ፣ የአየር መንገድ አስተናጋጆችና የራሱ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ተሳታፊ መሆናቸውን አሳውቋል።
በእነዚህ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ ገልጿል።
ምንጭ፦ ጉምሩክ ኮሚሽን
@tikvahethiopia
የጉምሩክ ኮሚሽን አድርጌዋለሁ ባለው ጥናት " መመሪያ 51/2010 " ሽፋን በማድረግ በህገወጥ ንግድ ላይ የመንግስት ሰራተኞች ፣ የአየር መንገድ አስተናጋጆችና የራሱ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ተሳታፊ መሆናቸውን አሳውቋል።
በእነዚህ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ ገልጿል።
ምንጭ፦ ጉምሩክ ኮሚሽን
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኮምቦልቻና ደሴ ኤሌክትሪክ ዛሬ ማግኘት እንዲችሉ በርብርብ እንሰራለን "- የኢ.ኤ.ኃ. የጥገና ባለሙያዎች በሸዋ ሮቢት - ኮምቦልቻ መስመር የተጎዳውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የሚጠግነው የጥገና ቡድን አባላት የኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ዛሬ ኤሌክትሪክ ማግኘት እንዲችሉ በርብርብ እንሰራለን ብለዋል። የጥገና ቡድኑ ትናንት ምሽት የጥገና ሂደቱን፣ በየከተሞቹ የደረሰውን ጉዳትና የህብረተሰቡን ስሜት የተመለከተ…
#Update
ኮምቦልቻ ከተማ ኤሌክትሪክ ማግኘቷ ተገልጿል።
ደሴም ኤሌክትሪክ እንድታገኝ በምሽት ርብርቡ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።
@tikvahethiopia
ኮምቦልቻ ከተማ ኤሌክትሪክ ማግኘቷ ተገልጿል።
ደሴም ኤሌክትሪክ እንድታገኝ በምሽት ርብርቡ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኮምቦልቻ ከተማ ኤሌክትሪክ ማግኘቷ ተገልጿል። ደሴም ኤሌክትሪክ እንድታገኝ በምሽት ርብርቡ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update
ደሴ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኘች።
ደሴ ዛሬ ማታ 4:30 ላይ ኤሌክትሪክ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።
@tikvahethiopia
ደሴ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኘች።
ደሴ ዛሬ ማታ 4:30 ላይ ኤሌክትሪክ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።
@tikvahethiopia
#GreyImport
ረጅም ሰአትዎን ተቀምጠው ወይም መኪና እየነዱ ያሳልፋሉ? አንግዲያዉስ Memory Foam Seat Cushion እና Lumbar Support Pillow ይዘንልዎት መጥተናል። call 0929088890
የመቀመጫ Cushion 850 ብር
የጀርባ Pillow 750 ብር
ያሉበት ድረስ በነፃ እናደርሳለን Made in Turkey
- ቢሮ ተቀምጠው ለሚሰሩ፣ ለሹፌሮች በጣም አስፈላጊ
- እግር ላይ የሚፈጠር ጫናን የሚቀንስ
-የወገብ ፣ የጀርባ አና የዳሌ ህመምን የሚቀርፍ
አድራሻ ~ቦሌ መዳሃንያለም

" ... በህገወጥ ወረራ የተያዙ መሬቶች የፍርድ ቤት እግድ ምክንያት ወደ መሬት ባንክ መመለስ እንዳለባቸው ይፍ ተደርጓል " - አ/አ ከተማ አስተዳደር
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ10 ክ/ ከተሞች በተደረገ የመሬት ዳሰሳ ጥናት 560,233.00 ካሬ በህገወጥ ወረራ የተያዙ መሬቶች የፍርድ ቤት እግድ ምክንያት ወደ መሬት ባንክ መመለስ እንዳለባቸው ይፍ ተደርጓጋ።
በኦዲት ግኝቱ መሰረት ፍርድ ቤት እግድ የጣለባቸው ምንም አይነት የልማት ተግባር ያልተከናወነባቸው ባዶ መሬቶችንም ጨምሮ ሲሆን እግድ የተሰጣቸው ሰዎችም ምንም አይነት የባለመብትነት መረጃም ሆነ ማስረጃ የሌላቸው መሆኑን ከኦዲት ሪፖርቱ ማረጋገጥ ተቸሏል።
ከተማ አስተዳደሩ ፥ " ሕግ እና ስርዓት የማስከበር ስራችን ህገወጥ የመሬት ወረራን ጨምሮ መተግበር አለበት ብሎ በጽኑ ስለሚያምን ጉዳዮ የሚመለከታቸው አካላት ህግና ስርዓትን ተከትለው ሀላፊነት በተሞላው ሂደት ሊሰሩ ይገባል " ብሏል።

" የነዳጅ ችግር የሚባል ነገር የለም " - ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ
ባለፈው ሀሙስ በኢትዮጵያ የተመድ ቢሮ ማስተባበሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጋራ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
መግለጫውን የሰጡት በተመድ በኩል ዶ/ር ካትሪን ሱዚ በኢትዮጵያ በኩል የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ነበሩ።
በመግለጫው ላይ ህወሓት ስለዘረፋቸው የኮምቦልቻ እና ደሴ UN መጋዘኖች፣ ትግራይ ክልል ገብተው ስለቀሩት ተሽከርካሪዎችና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ነበር።
ኮሚሽነር ምትኩ ፥ ተመድ እርዳታ ጭነው ትግራይ ገብተው ስለቀሩት ተሽከርካሪዎች መመለስን አስመልክቶ ምንም ያደረገው እንቅስቃሴ እንደሌለና ተሽከርካሪዎቹ ከትግራይ ያልተመለሱት በነዳጅ እጥረት እንደሆነ የሚነገረው ከእውነት የራቀ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮሚሽነር ምትኩ፥ የፌዴራል መንግሥት መቐለን ለቆ ሲወጣ 400 ሺህ ኩንታል ስንዴ፣ 2.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይትና 14 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ትቶ እንደወጣ አስታውሰዋል።
" በቂ ነዳጅ የለም የተባለው ተቀባይነት የሌለው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
አክለው፥ " እኛ ባለን መረጃ ሽረ እና መቐለ ላይ በብላክ ማርኬት ዋጋ ነው ነዳጅ እየሸጠ ያለው TPLF እራሱ፤ ኮምቦልቻን በወረረበት ሰዓትም ከኮምቦልቻ ዴፖ በርካታ ነዳጅ ወስዷል። ስለዚህ የነዳጅ ችግር የሚባል ነገር የለም " ብለዋል።
እርዳታ ለማድረስ ወደ ትግራይ የሄዱ ከ1 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ዛሬም ድረስ እንዳልተመለሱ እና ህወሓት እየተገለገለባቸው እንደሆነ ትላንት ተገልጿል።
https://telegra.ph/MoFA-Ethiopia-12-10

" መምህራን እና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በማህበራዊ አገልግሎት ይሰማራሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ዝግ ሆነው መምህራንና ተማሪዎች በተለያዩ ስራዎች ህዝባቸውን እንዲያግዙ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ መምህራን እና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ ይሰማራሉ። ሰብል መሰብስብ፣ በግንባር…
#Update
የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የፊታችን ሰኞ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ።
ተማሪዎች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ የተሳተፉበት የአንድ ሳምንት የማህበራዊ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስኬታማ እንደነበር ዛሬ መግለጫ የሰጠው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ አሳውቀዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ በዘመቻው ላይ ለተሳተፉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከፊታችን ሰኞ ከምሮ መምህራኑ እና ተማሪዎች ወደ መደበኛ ትምህርታቸው እንደሚመለሱ አመልክተዋል።
ተማሪዎቹ በበጎ ፍቃድ ስምሪታቸው ያለፈውን ጊዜም ለማካካስ እንደየትምህርት ቤቶቹ ባህሪ እንቅስቃሴ እንደሚደረግም ተገልጿል።