TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ብሄራዊ ቤተ መንግስት

የብሄራዊ ቤተ መንግስት የማያቀው ከ300 በላይ #የስልክና #የኢንተርኔት መስመሮችን ጨምሮ ለግለሰቦች በሚውሉ መስተንግዶዎች ምክንያት በየዓመቱ #ከ11_ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም ሲውል መቆየቱ ተገለፀ።

በአሰራር ክፍተት #ሲመዘበሩ የነበረ በርካታ ሚሊየን ብሮች ግምት ያላቸው ወጪዎችን ማስቀረት መቻሉንም የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደር አስታውቋል።።

በችግሮቹ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 31 ግለሰቦች ላይ #እገዳ የተጣለ ሲሆን፥ ቤተ መንግስቱ አሰራሩን በአዲስ መልክ በማደራጀት ክፍተቶቹን የማስተካከል ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል።

በስሩ ከአስር በላይ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ቤተ መንግስቶችን የሚያስተዳድረው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደር በዋነኝነት ሶስት ዋና ዋና ተግባራትን ይፈጽማል።

ከቤተ መንግስት ጋር ተያይዞ የሚገኙ ቅርሶችን መጠበቅና መከባከብ፣ ትላልቅ መስተንግዶዎችን ማከናወን እና ቤተ መንግስቱ ገቢውን በማሳደግ ራሱን በተሻለ ደረጃ እንዲያስተዳደር የሚሉ ናቸው።

የሀገሪቱ ርእሰ ብሄር መቀመጫ የሆነው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አስተዳደሩ የተሰጠውን ሀላፊነት ሲወጣ ቢቆይም ለረጅም ጊዜያት ከመመሪያና አሰራር ውጪ የሆኑ ተግባራት ሲፈጸሙበት መቆየቱን በጥናት ማረጋገጥ ተችሏል።

ባለፉት 9 ወራት በተሰራው የማጣራት ስራ ቤተ መንግስቱ በአስተዳደር ሂደት ውስጥ የሚያቀርባቸውን የመስተንግዶ አገልግሎቶች ለግለሰቦች ፍላጎት ማስፈጸሚያነት  እንዲውል በማድረግ በየዓመቱ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ሲደረግ ቆይቷል።

ከስልክ፣ ኢንተርኔትና ኢ ቪድዮ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ ቤተ መንግስት የማያገቃቸው ከ300 በላይ አካውንቶች በስሙ በየዓመቱ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ሲከፈል መቆየቱም ተደርሶበታል።

እነዚህ በማሳያነት የተነሱት ችግሮችና የተመዘበረ የገንዘብ መጠን ለማሳያነት የቀረቡ እንጂ በገንዘብ ያልተተመነና በአገልግሎት የሚገለጹ ሌሎች ጉድለቶችም እንደነበሩ ማረጋገጥ ተችሏል።

የገንዘቡም መጠን ሆነ የአገልግሎቱ ጉድለት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን፥ ይህም ወደ ገንዘብ ሲለወጥ በ100 ሚሊየን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ሲመዘበር ቆይቷል ማለት ነው።

የብሄራዊ ቤተ መንግስት ችግሮቹን ከመለየት ባለፈ ድርጊት ፈጻሚዎች የሚባለኩት በአመራር ላይ የነበሩና ከአመራር የተሰናበቱ 31 ግለሰቦችን ለይቶ አግዷቸዋል።

ድርጊቱን በማስቆም ለተጠያቂነቱ ኮሚቴ በማዋቀር የማጣራት ስራን እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።

ሌላው በብሄራዊ ቤተ የግዢ ስርአት ውስጥ የነበሩ ክፍተቶች በርካታ ግዢዎች እየተፈጸሙ ለአገልግሎት ከማዋል ይልቅ በመመጋዘን የማከማቸት ችግር ይታይ ነበር።

የተገዛው እቃ በመከማቸቱ እየተበላሸ ሌሎች በተለይም የውጪ ግዢዎችን በተከታታይ እየፈጸሙ መጠን እየቀናነሱ ማስገባትም ሌላኛው ችግር ነበር።

የበርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መየሆነው የብሄራዊ ቤተ መንግስት የንብረት አያያገዝ ችግሩም ሀብቶቹ እንዲባክኑ እየሆነ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆታቸውን ያስታወቀው የብሄራዊ ቤተ መንግስቱ አስተዳደር፥ አሁን ላይ ወደ መፍትሄው እርምጃ መግባቱንም አስታውቋል።

በሂደቱ ተጨማሪና የተሻሉ አሰራሮችን መዘርጋትና ወደ ተግባር ማስገባነት የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።

የብሄራዊ ቤተ መንግስት በቅርቡ ለህዝብ ክፈት እንዲሆን ለማድረግ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩም መሆኑን ሰምተናል።

ቤተ መንግስቱ ያሉትን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀምና እድሳት የሚያስፈልጋቸውንም በማደስ በአጭር ጊዜ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia