TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል›› ሕወሓት

‹‹ትዕግሥት ሁሌ ስለማይሠራ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል›› ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል
.
.
የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ደብረ ጽዮን_ገብረሚካኤል ‹‹ሕገ መንግሥቱ እየተጣሰ ትዕግሥት የሚባል ነገር ሁሌ አይሠራም፣ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፤›› ሲሉ ለክልሉ ቴሌቪዥን ተናገሩ፡፡

በአገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ሕገ መንግስቱ የሚጣስበት እና በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ #ጥቃቶች የሚሰነዘሩበት ነው ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ሕወሓት 44ኛ አመት የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ እና ደጋፊዎቹ የምሥረታ በዓሉን የሚያከብሩት በኢትዮጵያ የተጀመረው ዕድገት ወደ ኋላ እየተቀለበሰ ባለበት ወቅት ነው ብሏል፡፡

ለተጠቀሰው ችግር ዋነኛው መንስኤ የኢሕአዴግ አመራር ውስጥ የተፈጠረው #አለመግባባት እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት መሆኑንም መግለጫው ይናገራል፡፡

‹‹የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል›› የሚለው የሕወሓት መግለጫ ትችቱን እንደሚከተለው ያቀርባል፡፡

‹‹በስመ ለውጥ ለአገራቸው ክብርና ሉዓላዊነት መረጋገጥ ዕድሜ ልካቸውን የደከሙና የለፉ የሚረገሙበትና የሚብጠለጠሉበት፣ በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዜጎች ላይ የተለያዩ በደሎችና ግፍ የፈጸሙ፣ እንዲሁም የአገራቸውን ሉዓላዊነት አሳልፈው የሰጡ ብቻ ሳይሆን፣ ከሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብረው አገርና ሕዝብ የወጉ የሚመሠገኑበትና ክብር የሚሰጥበት የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል፤››

ይሁን እንጂ የአገሪቱ ሁኔታ ሕወሓት ካወጣው መግለጫ በተቃራኒ እንደሆነ በርካቶች ይገልጻሉ።

ከምንጊዜውም የተሻለ ዴሞክራሲ የሰፈነበት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የቆሙበትና ቀደም ሲል ለተፈጸሙ ጥሰቶችም ፍትሕ የተሰጠበት መሆኑን የአገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ የውጭ መገናኛ ብዙኃንና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ በይፋ እየተናገሩ ናቸው።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና የዜጎች መፈናቀል መኖር እርግጥ ቢሆንም፣ የፖለቲካ ሽግግር ከዚህ የፀዳ ሊሆን እንደማይችል ነገር ግን ይህ ችግር እየደበዘዘ መሄድ እንዳለበትና በአሁኑ ወቅትም መረጋጋት መኖሩን ያስረዳሉ።

ሕወሓት በፖለቲካ ማዕከሉ ላይ የነበረው ተፅዕኖ በመቀነሱ የመገፋት ስሜት ሊጫነው እንደሚችል፣ ይኼንንም የሚያባብሱ የፖለቲካ ትግሎች በኢሕአዴግ ውስጥ መቀጠላቸው በግልጽ የሚታይ ቢሆንም፣ ጉዳዩን ከሕዝብ ጋር ማገናኘት ስህተት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ልሂቃን በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ የሚያነሱት ሐሳብ ነው።

የካቲት 13፣ 2011

ምንጭ - ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia