TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ⬆️

#የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች በ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ለመሳተፍ በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ለጉባዔው ተሳታፊዎች የባህላዊ ቁርስ( #ቡርሳሜ ) ግብዣ አድርገዋል። የሀገር ሽማግሌዎቹ ከእንሰት የተዘጋጀውን ቡርሳሜ የተሰኘ ባህላዊ ቁርስ ከእርጎ ጋር ለተሳታፊዎቹ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬆️

ኢህአዴግ #በሃዋሳ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤው በድል ማጠናቀቁን እና ዶ/ር #አብይ_አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ #ደመቀ_መኮንን ደግሞ የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ያስደሰታችው መሆኑን ተከትሎ የሲዳማ ሽማግሌዎች እና የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በሃዋሳ ስታዲየም ዳኤ-ቡሹ በማለት ፍቅራቸውን በመግለጽ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል። #የሲዳማ ሽማግሌዎችም ደማቅ በሆነው የቄጠላ ሥነ-ሥርዓት በመታጀብ መልካም የሥራ ዘመን ይሁንላችሁ በማለት ከልብ የመነጨ #ምርቃታቸውን አቅርበውላቸዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ~ሲዳማ!

የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው ግጭት ሕይወታቸውን ያጡ የወላይታ ብሔር ተወላጆች ቤተሰብ ላይ ለቅሶ በመድረስ #አጽናንተዋል፡፡

ረጅም ዘመናትን የዘለቀው የሁለቱ ህዝቦች #ትስስር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የሟች ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡

የሲዳማ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች በሐዋሳና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት ልጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን በሞት ለተለዩ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በደረሱበት ወቅት ከሟች ቤተሰቦች አንዳንዶቹ እንደተገለጹት ሁለቱ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተሳስረው፣ ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር የሚቀሰቅሱ አካላት ሊገስጹ ይገባል ብለዋል፡፡

በሰኔ 8 2010 ዓ.ም በሀዋሳ እና አከባቢው በተከሰተው ግጭት የሰው ህይወት በመጥፋቱ እጅግ ማዘናቸውን የሟች ቤተሰቦች ገልፀው እርቀ ሰላም እንዲወርድ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት፣ አስታራቂ ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ዳጋቶ_ኩምቤ እንደተናገሩት የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ለዘመናት ተከባብረውና ተቻችለው አብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

የሁለቱ ህዝቦች ታሪካዊ ትስስር በአንድ መድረክ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በሁለቱ ህዝቦች መካከል በተከሰተው ግጭት ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ከመጥፋቱም በላይ በሰው አካል ላይ ጉዳት ያደረሰ፣ በርካታ ንብረት የወደመበት እና በርካታ ሰው የተፈናቀለበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ጥፋት ሁለቱንም ህዝቦች የማይወክል ጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች የራሳቸውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት ሆን ብለው ግጭቱ የብሔር ይዘት እንዲኖረውና የህዝቦቹ ትስስር #እንዲሻክር ያደረጉት ነው ብለዋል፡፡

#የሲዳማ_ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት በወላይታ ሶዶ በመገኘት ወገኖቻቸውን በሞት ላሰጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ ለመድረስና ለማጽናናት የመጡበት ዋናው ዓላማ የሁለቱ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነታቸውንና አብሮነታቸውን ለማደስ ነው፡፡

የወላይታ እና የሲዳማ ህዝቦች ረጅም ዘመን የቆየው አንድነትና አብሮነት ቀጣይነት አንዲኖረው ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የሀገር ሽማግሌዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የሁለቱ ህዝቦች አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የሟች ቤተሰቦችን የማጽናናት ሥራ በባህላዊ የዕርቅ ስርዓት ተከናውኗል፡፡

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ.ም የወላይታ ብሔር የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ሐዋሳ በማቅናት በሲዳማ ብሔር በኩል በግጭቱ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ላይ ለቅሶ በመድረስ እንደሚያጽናኑ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ Wolaita ZONE Culture,tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiop
Audio
#update በወላይታና በሲዳማ ብሄር መካከል እርቀ ሰላም የማውረድ እንቅስቃሴ #ቀጥሏል፡፡ የወላይታ አገር ሸማግሌዎች በግጭቱ የተጎዱ #የሲዳማ_ተወላጆችን #ሃዋሳ ሄደው በባህላዊ ሥርዓት ያፅናኑ ሲሆን የሲዳማ ሸማግሌዎችም ወላይታ ሶዶ በመሄድ ጠይቀዋል፡፡ በቀጣይም እርቀ ሰላም የማውረድና የይቅርታ ሥርዓት ከህዝብና #ከወጣቶች ጋርም ይፈፀማል ተብሏል፡፡


ምንጭ፦ voa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወላይታ ብሄር ተወላጆች ውይይት አደረጉ፦

"የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችንን በማዘመን ሚዲያ ለህዝቦች ትስስርና ለሀገር ግንባታ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ከማድረግ ባሻገር በህዝቦች ዘንድ ግጭት የሚቀሰቅሱ መረጃዎችን #ባለማሰራጨት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት።"
.
.
"የወላይታ ብሔር ተወላጆች #ከሌሎች ህዝቦች ጋር ቀድሞ የነበረውን ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት እና የመቻቻል እሴታቸውን በማጠናከር ለሰላምና ለሀገር #ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከት አለባቸው፡፡"
.
.
"በወላይታ እና #በሲዳማ ህዝቦች መካከል የተፈጠረውን የሰላም፣ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶችን ለማስቀጠል ተከታታይ ያለው ህዝብን የማወያየት ሥራ ይሰራል።"
.
.
"የወላይታ እና #የሲዳማ ህዝቦች ትስስር በጊዜያዊ ግጭቶች #የሚሸረሸር ሳይሆን ትናንትም የነበረ #ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ ስለሆነም ሰላም በዋጋ የማይተመን ትልቅ ሀብት ስለሆነ እጅ ለእጅ ተያይዘን ድህነትን ለማሸነፍ ልንሠራ ይገባል ብለዋል፡፡"
.
.
"የወላይታ እና ሲዳማ ህዝቦች የግጭት ታሪክ የሌላቸው ከመሆናቸውም ባሻገር በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ ህዝቦች ናቸው፡፡"
.
.
"ሰላም ለአንድ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ የወላይታ ብሔር ተወላጆች በሚኖሩበት አከባቢ ለሀገር ሰላም የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።"

ሀዋሳ ጥር 04/05/2011

https://telegra.ph/የወላይታ-ብሔር-ተወላጆች-01-12
ሀዋሳ-የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ‼️

#የሲዳማ_ክልል_ጥያቄ የሕዝቤ ውሳኔ ቀን መዘግየት አስመልክቶ በቀን 14/6/2011 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው ሰልፍ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት #ማጠናቀቁን የሲዳማ ዞንና የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች በጋራ በሰጡት መግለጫቸው አስታውቀዋል።

የሰልፉ ዓላማ የሲዳማ ሕዝብ በክልልነት የመደራጀት መብት አስፈላጊውን ሕጋዊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ በቀን 12/3/2011 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢቀርብም እስከ አሁን ድረስ ሕዝቤ ውሳኔ የሚካሄድበት ቀን ተወስኖ ምላሽ ባለመሰጠቱና በመዘግየቱ የሚካሄድ ሰልፍ መሆኑን ለማወቅም ተችሏል።

"ሕገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር" በሚል መሪ ቃልና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ በዕለቱ ከጧቱ 1:00-6:00 ሰዓት ድረስ መነሻውን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገ በሲዳማ ዞን አስተዳደር- በአሮጌው መናኸሪያ -በተስፋዬ ግዛው ሕንጻ-በመሳይ ሆቴል አቋርጦ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሳረጊያ የሚደረግ ይሆናል።

በሰልፉ ላይ ከሲዳማ ዞን ሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ ሰልፈኞች የሚሳተፉ መሆኑን በመግለጽ ሰልፉም በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከተለያዩ ፀጥታ አካላትና ከሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን በመግለጫው አክሏል።

ኀብረተሰቡም ይህን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ የራሱንና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና ማንኛውንም ዓይነት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለፀጥታ አካላት ፈጥኖ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ ቀርቧል።

ከዚህም በተጨማሪ: በሰላማዊ ሰልፉ መነሻ-መድረሻ እንዲሆኑ በተፈቀዱ መንገዶች ላይ ማንኛውም ዓይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የማይፈቀድ መሆኑንና የሰላማዊ ሰልፍ ትዕይንት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለትራፍክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሚሆን ተገልጿል።

ከዚህ ውጭ በቡድንም ሆነ በተናጠል የከተማውን ኀብረተሰብ ሰላማዊ እንቅስቃሴና የሰላማዊ ሰልፉ ሠላማዊ ህደቱን ማወክ የተለያዩ #የጦር_መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት፣በሰልፉ ወቅት በሕግ #የተከለከሉ ድርጊቶች መፈፀም በጥብቅ የተከለከሉ ሲሆን ተፈጽሞም ሲገኙ የፀጥታ አካሉ አስፈላጊውን ሕጋዊ #እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ኃላፊዎቹ በመግለጫቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

በማጠቃለያም ሕዝባዊ ትዕይንቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ኀብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንዲሰራ በድጋሚ ጥሪ በማቅረብ ኃላፊዎቹ መግለጫቸውን አጠቃለዋል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን ከተሞች #የስራ_ማቆም አድማ በመደረግ ላይ ይገኛል። የስራ ማቆም አድማው የተጠራው ኢጄቶ በመባል በሚታወቁ የሲዳማ ወጣቶች ሲሆን፣ አላማውም #የሲዳማ_ክልልነት ጥያቄን የሚወስነው ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ መጠየቅ ነው። በሀዋሳ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የተዘጉ ሲሆን ትራንስፖርት ሙሉ ለሙሉ አልተቋረጠም። መከላከያን ጨምሮ የክልሉ ፖሊስ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለማስከፍት የሞከሩ ሲሆን፣ በአንዳድ አካባቢዎች ከወጣቶች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተጎድተዋል። የስራ ማቆም አድማው ለሶስት ቀናት ይቀጥላል ተብሏል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን ሀዋሳ🔝

#የሲዳማ_ሴቶች ብቻ የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ሰላማዊ ሰልፉ የሲዳማ የክልል ጥያቄነት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ሲሆን፥ የሲዳማ ሴቶችም እርጥብ ቅጠል በመያዝ ሰላማዊ ሰልፉን እያካሄዱ ይገኛል።

ሰላማዊ ሰልፉ በሲዳማ ዞን አስተዳደርና በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን፥ ሰልፈኞቹም የሲዳማ ህዝብ ክልል ለመሆን የጠየቀው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ ባለማግኘቱ ስሜታቸውን በመግለፅ መልዕክት እያስተላለፉ ነው።

ሰላማዊ ሰልፉ የሲዳማ ብሔር አባቶችና ወጣት ወንዶች የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ካደረጉት የቀጠለ ነው ተብሏል።

በአሁኑ ሰልፍ ተሳታፊ የሆኑ የሲዳማ ብሔር እናቶችና ወጣት ሴቶች የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ የወንዶች ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የእነርሱም ጭምር በመሆኑ፥ ያላቸውን የትግል አጋርነት ለማሳየትና ስሜታቸውን ለመግለፅ አደባባይ መውጣታቸው ተገልጿል።

ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማትም የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

ምርጫ ቦርድ #የሲዳማ_የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውስኔ መስጫ ቀንን ይፋ አደረገ። ቦርዱ ዛሬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውስኔ መስጫ ቀን ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ/ም እንዲሆን ተወስኗል።

ቦርዱ ለዚህ ስራም ከነሀሴ 30 ቀን 2011 ዓም አንስቶ 8ሺህ 460 ምርጫ አስፈጻሚዎችን እንዲሁም 1 ሺህ 692 የህዝበ ውሳኔ ደምጽ መስጫ ጣቢያዎችን አደራጃለሁ ብሏል። ለህዝበ ውሳኔው ስራ ማስኬጃ 75 ሚሊዮን 615 ሺህ ብር የሚያስፈልግ ሲሆን ወጪውን የደቡብ ክልል ምክር ቤት ይሸፍናል ተብሏል።

Via #EthioFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia