#FDRE_Defense_Force
" በጉሙዝ ባህልና ወግ መሠረት በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ-መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከረ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራና ዳንጉር ወረዳዎች ከ3 ዓመታት በላይ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ1 ሺ በላይ አመራሮችና አባላት በጉሙዝ ብሔረሰብ ዕርቀ ሰላም ባህል "ማንገማ" መሠረት #ትጥቃቸውን_አስረክበው_እርቅ_አካሂደዋል።
የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ የሆኑት ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ በዕርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ " በጉሙዝ ባህልና ወግ መሠረት በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ-መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከረ ነው " ብለዋል።
ለፈፀሙት ቃለ-መሃላም ሁሉም ተገዥ በመሆን ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ቁርጠኝነቱን በተግባር ማሳየት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ ሌሎች ወረዳዎች የሚገኙ ህገወጥ ታጣቂዎችም የአፍራሽ ኃይሎችን ተልዕኮ ከማስፈፀም ተቆጥበው ቅድሚያ #ለሰላም ዕድል መስጠት እንደሚገባቸው ጥሪ አስተላልፏል።
#FDRE_Defense_Force
@tikvahethiopia