TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገው በዉይይቱ ላይ በሙስሊም ተወካዮች ከተነሱት ነጥቦች መካከል፦ - በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች የመስጂድ መሬትን በህጋዊ መንገድ የማግኘትና የመሥራት እንዲሁም ለተሠሩት መስጂዶች ካርታና የማስፋፊያ መሬት የማግኘት ሁኔታ ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉ በዝርዝር ተብራርተዋል። - የሸገር ከተማ አሰተዳደር ከፕላን…
#Update

" ሕዝበ ሙስሊሙ ያቀረባቸውና የሚያቀርባቸው የመስጂድ ጥያቄዎች #በፕላኑ መሠረት ምላሽ ይሰጣል " - አቶ ሽመልስ አብዲሳ

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በተደረገው ውይይት በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኩል የተጠቀሱት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው ፦

1. ቀደም ብሎ በጉዳዩ ላይ ዉይይት አለመደረጉ ስህተት መሆኑን ገልጸዋል።

2. በተፈጠረው ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡት ሙስሊሞች ማዘናቸውን ገልጸዋል።

3. የሸገር ከተማ የሃይማኖትን እሴትን መሠረት አድረጎ እንደሚገነባ እና የእሰልምናን ጨምሮ የሌሎችም ቤተእምነቶችም ተቋማት በብዛት በሸገር ከተማ ፕላን ዉስጥ እንደተካተቱ።

4. አስፈላጊውን የቤተእምነት መሥሪያ መሬቶችን በፕላኑ መሠረት ለምዕመኑ እንደሚሰጥና በቆርቆሮ ሳይሆን የከተማዋን ፕላን የሚመጥን በርካታ ዘመናዊ መስጊዶች በከተማው እንዲሰሩ እንደሚፈልጉ።

5. በሸገር ከተማ ላይ በሀገር ደረጃ ሊጠቀስ የሚችል ትልቅና ዘመናዊ መስጂድና ለሌሎች እምነት ተቋማት መሥሪያ ቦታ እንደሚሰጥ።

6. በሸገር ከተማ ለኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የሚሆን መሬት እንደሚሰጥ።

7. ሸገር ከተማ ከ20 እስከ 30 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያላት፥ ዘመናዊና በፕላን ብቻ ግንባታ የሚካድባት ከተማ ሆኖ ለመግንባት ሕግ ወጥ ግንባታን መከላከል፥ የተገነቡትን #ማፍረስ_እንደሚቀጥል ለዚህ ሂደት የእምነት ተቋማት ተባባሪ እንዲሆኑ እንፈልጋለን ብለዋል።

8. አዲሱ የሸገር ከተማ ፕላን ወደ ተግባር እስኪገባ ድረስ ሙሉ ለሙሉ መኖሪያ ቤቶች ባልፈረሱባቸው አከባቢዎች ለሚኖሩ ሙስሊሞች በጊዜያዊነት የሚሰግዱባቸው መስጊዶች የኦሮሚያ ክልል መጅሊስና የሸገር ከተማ አስተዳደር በጋራ በመጋገር መስጂድ መሥሪያ ቦታ እንዲያዘጋጁ።

9. የሸገር ከተማ ማስተር ፕላን በመጪው ሀምሌ ወር ወደ ተግባር ማዋል ከመጀመሩ በፊት በማስተር ፕላኑ ለእምነት ተቋማት የተዘጋጀውን ስፍራዎችን የሙስሊም ተወካዮች ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ ቀድመው ፕላኑን እንዲመለከቱና እንዲያረጋግጡ፡፡

10. በሸገር ከተማ ሕዝበ ሙስሊሙ ያቀረባቸውና የሚያቀርባቸው የመስጂድ ጥያቄዎች በፕላኑ መሠረት ምላሽ እንደሚሰጥ።

11. ሸገር ከተማን ጨምሮ በመላው ኦሮሚያ ክልል ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው የእምነት ተቋማት እና የመቃብር ሥፍራ መስጠት እንደሚቀጥል።

12. በሸገር ከተማ ዉስጥ ካሉት ስምንት መቶ (800) የሁሉም እምነት ተቋማት መካከል 656(ስድስት መቶ ሀምሳ ስድስት) የሚሆኑት ከፕላን ዉጭ የተሠሩ በመሆናቸው እነዚህን የሚገነባውን ከተማ ፕላን የማይመጡትን የተለያዩ ቤተእምነቶችን ወደ በሕጋዊና ከተማውን በሚመጥኑ ተቋማት ለመተካት የሚደረገውን ሂደት የኦሮሚያ ክልል መጅሊስም ባለበት የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አቅሙን በማጠናከር በዉይይት የእምነት ተቋማቱ ራሳቸው መፍረስ ያለባቸውን እንዲያፈርሱ እንጂ ከአሁን በኋላ መንግስት በራሱ ማፍረስ እንደሚያቆም ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

@tikvahethiopia