TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዳማ ፖሊስ ኮሌጅ‼️

በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ ለማስቀጠል የፖለቲካ ፓርቲዎች #ለሰላም_ቅድሚያ በመስጠት እንዲሰሩ በአዳማ ፖሊስ ኮሌጅ እየሰለጠኑ ያሉ የኦነግ የቀድሞ ታጣቂዎች ተናገሩ።

አዳማ በሚገኘው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ሥልጠና እየወሰዱ የሚገኙት የኦነግ የቀድሞ ታጣቂዎች አሁን ላይ የሚታየው ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረው መላው የኦሮሞ ህዝብ በተለይ ወጣቱ፣ አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል እና ደጋፊ አለመሆናቸውን የተናገሩት የቀድሞ ታጣቂዎቹ፥ አላማቸው ለህዝቡ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለሀገር እድገት መስራት መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እተሰጣቸው ያለው ስልጠናም በሁሉም ረገድ ብቁ እንዲሆኑ እየረዳቸው መሆኑንም ተናግረው፥ ቆይታቸውን አጠናቀው ሲወጡም በፖሊሳዊ ስነ-መግባር በመታነጸ ህዝብን እንደሚያገለግሉ ነው ያረጋገጡት።

ከዚህ ባሻገር አሁን የተጀመረው ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረው እና አስተማማኝ ሰላም በክልሉም ሆነ በሀገር እንዲረጋገጥ ሁሉም አካላት የበኩላቸውኝ ጥርት እንዲያደርጉ ጠይቀው፥ የፖሊቲካ ፓርቲዎችም በሰከነ መንገድ ተቀራርበው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዓለማየሁ እጅጉ ሰልጣኞችን በተመለከተ እንዳሉትም፥ በአሁኑ ወቅት አዳማ በሚገኘው የክልሉ ፖሊስ ኮሌጅ እየሰለጠኑ የሚገኙት ከኤርትራ የተመለሱ የኦነግ ሸኔ ጦር አባላት ሁሉም የኢትዮጵያ መንግስትን የሰላም ጥሪን ተከትሎ መግባታቸውን ገልጸው፥ ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ ከመቀላቀላቸው በፊት ታሃድሶ በመውሰድ በፍላጎታቸው መሰርት የገቡ ናቸው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፖሊስ ለመሆን የሚጠይቀውን መስፈርት በሙሉ ማሟላታቸውን አስርድረተዋል።

ኮሚሽነሩ አክለው እየተሰጣቸው ያለውን ስልጠናን በጥሩ ስነ-ምግባር እየተከታተሉ መሆኑን አስረድተው፥ ስልጠናቸውንም ተከታትለው ካጠናቀቁ በኋላ ምደባ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ በአሁኑ ወቅት አዳማ በሚገኘው ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ 746 የሚሆኑ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦነግ ሸኔ የቀድሞ ከኤርትራ የተመለሱ አባላት የኦሮሚያ ፖሊስ አባል ለመሆን በመሰልጠን ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት #በሰላማዊ_መንገድ ለመፍታት ሰላማዊ ድርድሮች እንዲጀመሩ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫ አስቀመጠ።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በማእከላዊ ኮሚቴዉ መካሄዱን የፍትሕ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ አስታወቁ።

ዶ/ር ጌዲዮን ፓርቲው ሰላማዊ ውይይት ለማድረግ ዉሳኔ አሳልፏል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተካሄደው ጦርነት መንግሥት ተገዶ የገባበት መሆኑን ገልፀው ፤ መንግሥት ይህንን ለመፍታት እየሠራ ስለመሆኑም አስረድተዋል ።

ፓርቲዉ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዳይኖር ታሳቢ በማድረግ #ለሰላም_ቅድሚያ_ይሰጣል ነው ያሉት።

ዶክተር ጌዲዮን እንዳሉት ፓርቲዉ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የሰላም አማራጩ፡-

1. ሕገ መንግሥታዊ እና ሕጋዊነትን የሚያስከብር መሆን አለበት፡፡

2. የሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ መሆን አለበት፡፡

3. በሀገር ዉስጥ መፍታት ካልተቻለ #በአፍሪካ_ሕብረት ጉዳዩ መታየት እንዳለበት በሥራ አስፈጻሚ እና በማእከላዊ ኮሚቴ ዉይይት ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል።

በተጨማሪም ትንኮሳዎች ካሉ ሕግ አስከባሪዉ አካል እርምጃ እንዲወሰድ ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል። ሕዝቡም ለዚህ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia