TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዲስ አበባ የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 100 ሺ ደብተርና 100 ሺ እስክርቢቶ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ የሲዳማ ተወላጆች ላደረጉት የደብተርና የእስክርቢቶ ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Via #MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር

ባለዲግሪው መፃህፍት አዟሪ በብልሽት ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ ለስራ እንዲሆነው ከከተማ አስተዳደሩ ተበረከተለት!

ከተመረቀ በኋላ ለአራት አመታት መፃህፍት በማዞር ህይወቱን ሲመራ የነበረው ወጣት አንዷለም ይስሃቅ ከከተማ አስተዳደሩ ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረ ተሽከርካሪ በኢ/ር ታከለ ኡማ ተበርክቶለታል።

ወጣቱ ደርሶበት በነበረው የአእምሮ ህመም ችግር ሳይበገር እና ስራ ጠባቂ ሳይሆን እራሱን ለመለወጥ ያደረገው ጥረት ለብዙዎች አርአያ የሚሆን እንደሆነም ተነግሯል።

በጥቂት ጊዚያት ውስጥም በከተማዋ ያለ አገልግሎት የቆሙ ሌሎች 700 የሚሆኑ አንበሳ የከተማ አውቶብሶችን ወደ ተንቀሳቃሽ ሱቆች በመቀየር በከተማዋ ለሚገኙ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ለመስጠት ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።

ይህ ተግባር በአንድ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ለወጣቶች ስራ የመፍጠር ግዙፍ እቅድ አካል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በችግሮች ሳይበገሩ ራሳቸውን ለመቀየር እየሞከሩ ያሉ ወጣቶችን ለማበረታታት አላማ ያደረገ ተግባር ነው።

Via #mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ በሰሩዋቸው ስራዎች ምክንያት የተበረከተላቸውን የ MICE Champion Award ተረክበዋል፡፡ የማይስ የአሸናፊዎች ሽልማቱ በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ ዲያስፖራ ቱሪዝም ኮንፍረንስ ላይ የተበረከተ መሆኑ ይታወሳል፡፡

Via #MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbeba በዛሬው ዕለት ቀን 9:20 ላይ ኤግዚቢሽን ማእከል ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ የ78 ሰዎች መኖርያ የሆኑ 14 ቤቶች መውደሙ ተሰምቷል። ግምቱ 7 ሚልየን ብር የሆነ ንብረትም ተቃጥሏል። ተጎጂዎች ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙም ታውቋል። •አመሻሹን ደግሞ አ/አ አንዋር መስጅድ ዙርያ እሳት ተነስቶ የነበረ ሲሆን አሁን በቁጥጥር ስር መዋሉ ለማወቅ ተችሏል። Via Abdurahim…
#AddisAbeba

የጠቅላይ ሚንስትሩ የመሠረተ ልማት አማካሪ አቶ ዣንጥራር አባይ እና ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ትናትና ምሽት ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ያጋጠመውን አከባቢ ተመልክተዋል፡፡ ትናትና ምሽት ከኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ የ20 አባወራዎች መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡

ለእሳት አደጋ ተጎጂዎቹ ጊዜያዊ መጠለያን ጨምሮ ፍራሽ፣ ብርድልብስ እና ሌሎች መገልገያዎች አቅርቦት መሟላቱ ተነግሯል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደረም በከተማዋ ውስጥ ያሉ ባለሃብቶችን በማስተባበር በ20 ቀናት ውስጥ አዲስ ቤት በመገንባት ቤታቸውን በቃጠሎ ላጡ ነዋሪዎች እንደሚያስረክቡም ኢንጅነር ታከለ ኡማ መናገራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via #MayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ከተማ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ እንደተደረገበት የከተማ አስተዳደሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

በአዲሱ ማሻሻያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1-3 ሰአት እንዲሁም ከሰዓት ከ 10:30-12:00 ውጪ ባሉ ሰዓቶች እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።

እስካሁን በነበረው ህግ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው።

#MayorOfficeAA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ማሳሰቢያ ለአ/አ መንግስት ሰራተኞች!

የአዲስ አበባ የመንግሥት ሠራተኞች ከቤታቸው እንዲሠሩ የተላለፈው ውሳኔ የጤና ፣ ፖሊስ ፣ ኤሌክትሪክ ፣ ውሃ ፣ ትራንስፖርት ፣ መንገድ፣ ኮንስትራክሽን እና ደረቅ ቆሻሻ አገልግሎትን አይመለከትም ተብሏል።

#MayorOfficeAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት በነገው ዕለት ይደረጋል።

በተመረጡት መንገዶች ላይ የመከላከያ መድሃኒት ርጭት ወይንም ዲስኢንፌክት የማድረግ ስራ የሚከናወን ይሆናል።

በዚህም መሠረት፦

- መስቀል አደባባይ - ቦሌ ፣
- መስቀል አደባባይ - ጦር ሃይሎች ፣
- መስቀል አደባባይ - 6 ኪሎ ፣
- ከመስቀል አደባባይ - ጎተራ - ሳሪስ
- ከመስቀል አደባባይ - መገናኛ ፣
- ከብሄራዊ - ሜክሲኮ፣
- ከሱፐር ማርኬት - ካዛንችስ - ኡራዔል ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - አምባሳደር - መስቀል አደባባይ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - ፓስተር፣
- ከምኒልክ አደባባይ - 4 ኪሎ - መገናኛ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - 6 ኪሎ ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - አውቶብስ ተራ ፣
- ከምኒልክ አደባባይ - ተክለሃይማኖት
ያሉት መንገዶች የመድሀኒት ርጭት የሚካሄድባቸው ይሆናል።

የፀረ-በሽታ አምጭ ተዋህስ መድሀኒት ርጭት ሚካሄድባቸው መንገዶች 41 ኪሎ ሜትር የሚሽፍኑ ናቸው። በዚህ ምክንያትም የተጥቀሱት መንገዶች ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ለአገልግሎት ዝግ የሚሆኑ ይሆናል።

#MayorOfficeAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጃንሜዳው አትክልት ተራ ነገ ስራ ይጀምራል!

አትክልት ተራ ሲሰጥ የነበረው የግብይት አገልግሎት ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር የከተማ አስተዳደሩ በወሰነው መሠረት ጃንሜዳን የማዘጋጀት ሥራው መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።

በዚሁ መሠረት የአትክልት ተራ ከነገ መጋቢት 29/2012 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚዘጋ እና በጃንሜዳ የተዘጋጀው የአትክልት ግብይት ቦታ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቁት ምክትል ከንቲባው ነጋዴዎች እና በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች የኅብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የተወሰነውን ይህን ውሳኔ ማክበር እንደሚኖርባቸውም አሳስበዋል።

#MayorofficeAA #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የፍራፍሬ እና የሰብል ምርቶች ወደ ሸማች ማህበራት ሱቆች መግባት መጀመሩ ተገልጿል። የከተማዋ ነዋሪዎችም ምርቶቹን በተመጣጠነ ዋጋ ማግኘት የሚችሉ ይሆናል።

ምርቶቹ ወደ 800 ሸማች ማህበራት ሱቆች በብዛት እየገቡ ያሉት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያየዘ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር እና ህብረተሰቡም በዝቅተኛ ዋጋ ማግኘት እንዲችል ነው።

#MayorOfficeAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FederalPoliceCommission

በጉለሌ ክፍለከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ መስሪያ ቤቱ የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እናስፈጽማለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሰንሰለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ከተገልጋዮቹ ጋር በመሆን ባደረገው ተከታታይ ክትትል በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ህብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችለውን አገልግሎት ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት አካላትን በማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል ለህዝብ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ #MayorofficeAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia