TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EU #AU

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት ከቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ጋር ተገናኝተው መከሩ።

ቻርልስ ሚሼል እንደገለፁት ከሆነ ምክክሩ በትግራይ ግጭት ዙሪያ ሲሆን ፤ ዘላቂ እና ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት በሚደረግ አስቸኳይ ጥረት ላይ ነው ትኩረቱን አድርጎ የነበረው።

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ፤ " የቀጠናውን መረጋጋት ለማረጋገጥ የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US : አሜሪካ TPLF ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጣ በድጋሚ አሳሰበች። ዛሬ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ከአማራ እና አፋር ክልል እንዲወጣ፤ ወደ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ የሚያደርገውን ግስጋሴ እንዲገታ አሳስቧል። ሚኒስቴሩ TPLF በከተሞች ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ከመተኮስ እንዲቆጠብ ያሳሰበ ሲሆን ሁሉም ወገኖች ያለ ምንም…
#US #EU #USEmbassyAA

አሜሪካ በድጋሚ ተኩስ እንዲቆምና ድርድር እንዲጀመር ጠየቀች (ይህን ስትል በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለተኛዋ ነው)

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው ጦርነት አሜሪካን እጅግ እንዳሳሰባት አሳውቀዋል።

ብሊንከን ጦርነቱ በስፋት መዛመቱ ሰብዓዊ ቀውሱን እንደሚያከፋው ጠቁመዋል።

ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በድርድር ላይ የተመሠረተ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉም በመግለጫቸው ላይ አሳስበዋል።

ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነር ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ሁሉም ወገኖች ያለ ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱን እንዲያቀላጥፉ እና የጥላቻ ንግግሮችን እንዲያቆሙም አሳስበዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ህብረቱ እምነቱን ገልጿል።

በሌላ መረጃ ፦

አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ በሰሜን ኢትዬጵያ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጿል።

በአማራ ክልል፤ ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ ግጭት ተባብሷል ብሏል።

በአማራ እና በአፋር የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንን መከታተል እንዳለባቸው ፤ ግጭት በሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ካሉም ለመጠለል መዘጋጀት እንዳለባቸውና እነዚህን አካባቢዎች መልቀቅ ሊያስቡበት እንደሚገባ አብቆ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#EU #RUSSIA

የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በሩስያ የነዳጅ ግብይት ላይ ማዕቀብ ጣሉ።

27ቱ አውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት በሩስያ የነዳጅ ግብይት ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ይፋ አድርገዋል።

አባልሃገራቱ በግዙፉ የሩስያ ባንክ ስቤር ባንክንም ከዓለማቀፉ የባንኮች የክፍያ ስረዓት ወይም ስዊፍት ማስወጣታቸውን አስታውቀዋል።

በስምምነቱ መሰረት ወደ አውሮፓ የሚገባው የሩስያ ነዳጅ ሁለት ሶስተኛው እንደሚታቀብ የህብረቱ ፕሬዚደንት ቻርለስ ሚሸል ተናግረዋል።

ማዕቀቡ " የሩስያ የፋይናንስ ምንጭ በከፍተኛ ደረጃ በማንኮታኮት " ሩስያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ገትታ ከሀገሪቱ ለቃ እንድትወጣ ያስገድዳታል " ሲሉ ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስም " ስምምነቱ የጋራችን ነው " ብለዋል። ነገር ግን ከሃያ ሰባቱ ሃገራት መካከል ፦
➡️ ሃንጋሪ ፣
➡️ ስሎቫኪያ ፣
➡️ ቼክ ሪፐብሊክ እና ቡልጋሪያ ከሩስያ ነዳጅ ማስገባት #እንደማያቋርጡ አስታውቀዋል።

ይህንኑ በተመለከተ የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የነዳጅ ማዕቀቡ የህብረቱ አጀንዳ መሆን የለበትም ሲሉም ተቃውሟቸውን አሰምተው እንደነበር የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#EU

ዛሬ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ በሉግዘምበርግ ይመክራል።

ስብሰባውን የህብረቱ የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል በሊቀመንበርነት ይመሩታል የተባለ ሲሆን በሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ላይ የሚወያይ ቢሆንም የኢትዮጵያ ጉዳይም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል ተብሏል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ በአጀንዳነት የተያዘው፤ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ስር ነው።

የአውሮፓ ካውንስል ለዚሁ ስብሰባ ያዘጋጀው ሰነድ የኢትዮጵያ ሁኔታ " የተወሰነ መሻሻል " እንደታየበት ቢጠቅስም አሁንም ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁሟል።

ዘላቂ የተኩስ አቁም፣ የኤርትራ ወታደሮች መውጣት፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የፈጸሙን ተጠያቂ በማድረግ ረገድ መሳካት የሚኖርባቸው በርካታ ጉዳዮች እንደሚቀሩ በዚሁ ሰነድ ላይ ሰፍሯል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ የህብረቱ የሰብዓዊ መብቶች ልዩ መልዕክተኛ ኤይሞን ጊልሞር ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

Credit : https://ethiopiainsider.com/2022/7198/

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #EU

የአውሮፓ ህብረት (EU) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ዣኔዝ ሌናርቺች ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ የመጡት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ዙርያ ያሉ ሁኔታዎችን ለማየት ነው።

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ትላንት ዣኔዝ ሌናርቺች በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ላላት አጋርነት ትልቅ ትኩረት እንደምትሰጥ እና ከኮሚሽኑ እና ከአባል ሀገራቱ ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር እየሰራች መሆኑን አቶ ደመቀ ተናገረዋል።

አቶ ደመቀ ፤ በግጭት ለተጎዱ ወገኖች እየተደረገ ያለን የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትን በተመለከተ ለትግራይ ክልል የሚደርሰው ዕርዳታ ተመድ በሳምንት 500 የጭነት መኪኖች ከያዘው ግብ ባለፈ የማድረስ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረው አጋር አካላት የአማራ እና አፋር ክልሎችምንም ጨምሮ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገውን ድጋፍ እንዲያፋጥኑ ጠይቀዋል።

ኮሚሽነር ዣኔዝ ሌናርቺች ፤ መንግስት በዚህ ረገድ የሚያደርገውን ጥረት ያደነቁ ሲሆን ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ አጋሮች ተጨማሪነዳጅ፣ ጥሬ ገንዘብ እና ሌሎችም ድጋፎች ወደ ትግራይ ክልል እንዲሄዱ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁለቱ አካላት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ግጭት ጊዜ በተከሰቱት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን የተጠያቂነት እርምጃ፣ ይህንን የሚያረጋግጥ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በማቋቋም እና በሰብአዊ መብት አያያዝ እና በተመድ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን ላይ ስላሉ ጉዳዮች ተወያይተዋል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #EU የአውሮፓ ህብረት (EU) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ዣኔዝ ሌናርቺች ኢትዮጵያ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ የመጡት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ዙርያ ያሉ ሁኔታዎችን ለማየት ነው። የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ትላንት ዣኔዝ ሌናርቺች በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ላላት…
#EU

ዣኔዝ ሌናርቺች ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ ከተማ በማቅናት ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር መክረዋል።

የአውሮፓ ህብረት (EU) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ትላንትና በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ከመከሩ በኃላ ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው ክልሉን ከሚያስተዳድሩት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር መክረዋል።

በውይይቱ የተለያዩ የጋራ ጉዳዮች መነሳታቸውን ከሚገልፅ መረጃ ውጭ ዝርዝር ነገር አልተገለፀም።

ኮሚሽነሩ ከውይይቱ ቀደም ብሎ የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል መጎብኘታቸውን የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት አሜሪካን ስጋት እንዳጫረባት ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እና በመጨረሻም ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ብሊንከን ፤ ላለፉት 5 ወራት የነበረው የተኩስ አቁም የበርካቶችን ሕይወት መታደጉንና…
#EU

" ወቅቱ ለሰላም ውይይት የሚደረግበት ጊዜ ነው " - የአውሮፓ ኅብረት

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና የአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦሬል በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ማግርሸቱን የሚገልፁ ሪፖርቶች የሰላም ተስፋ ላይ ጥላ ያጠላል ብለዋል።

ሁሉም ወገኖች ሁኔታው ይበልጥ ከመባባሱ በፊት እና ወደ ለየለት ጦርነት ሳይገባ ግጭቱን እንዲያረግቡ ጠይቀዋል።

" ወቅቱ ለሰላም ውይይት የሚደረግበት ጊዜ ነው "  ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EU

" የትግራይ ባለስልጣናት የተዘረፈውን ነዳጅ በአስቸኳይ ይመልሱ " ሲሉ የአውሮፓ ኅብረት የቀውስ ጉዳዮች ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺክ ጠይቀዋል።

ሌናርቺክ ፤ ያለ ነዳጅ በትግራይ ውስጥ ምግብ የማድረስ ስራ ሊሰራ አይችልም ብለዋል።

የሚሊዮች ህይወት በዚህ ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA " አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል። ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው። ብሊንከን ፤…
#UN #EU

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በአስቸኳይ ለማቆም እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን ማሳወቁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል።

በተጨማሪ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለሚደረገው የሰላም ሂደት ፍቃደኛ መሆኑን አበረታተዋል።

ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት ይህንን እድል ለሰላም እንዲጠቀሙበት እና ግጭት እንዲቆም እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንዲሁም ለውይይት አማራጭ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁለቱም በቅን ልቦና ሳይዘገዩ እንዲሁም ለውይይቱ መካሄድ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አበረታተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ዋና ፀሀፊው በመጨረሻም አዲሱ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያውያን የደስታ እና የሰላም እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የአውሮፓ ህብረት የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአስቸኳይ ግጭት ለማቆም እና በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን መግለፁን ተከትሎ " አሁን ፤ ይህንን እድል ሁሉም ሊጠቀምበት ይገባል " ብሏል።

የአውሮፓ ህብረት፤ የአፍሪካ ህብረትን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #EU #UNICEF

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ።

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የተቋረጡ የጤና አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀምሩ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት (EU) የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ያደረገው የማስጀመር እና የአቅም ግንባታ ስራ እንዲሰራ ለማስቻል ለተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የተደረገው ድጋፍ የህፃናትና ሴቶች ኑሮ ለማሻሻልና በግጭቱ ሳቢያ ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ እንዲሁም የጤና አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ለማድረግ ነው።

@tikvahethiopia
#EU #Visa

የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ጣለ።

የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት በኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ ፦

- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ፤

- አባል ሀገራት ከአሁን በኋላ ከ2 ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉ ፤

- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛ የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ ተነግሯል።

በተጨማሪ መደበኛ ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ተቀይሯል።

ይህ ውሳኔ የተወሰነው የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚቆዩትን ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ ነው ተብሏል።

ገደቡ እንከመቼ እንደሚቆይ የተባለ ነገር የለም።

https://www.consilium.europa.eu/en/press/press-releases/2024/04/29/ethiopia-council-restricts-visa-provision/

@TikvahethMagazine @tikvahethiopia