TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጋምቤላ ነዋሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ‼️

በጋምቤላ ከተማ #ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ሲያዘዋውር ደርሸበታለሁ ያለውን አንድ #ተጠርጣሪ ግለሰብ #በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

በከተማውና አካባቢው የሀሰተኛ የብር ኖት ዝውውር #እየተበራከተ በመምጣቱ ህብረተሰቡ #ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋምቤላ ከተማ ኦፔኖ ቅርንጫፍ አሳስቧል።

በጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የፎረንሲክ ምርመራ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር #ቱት_ኑዑት ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው የልብስ ግብይት ያካሄደባቸው ባለሱቆች የሰጣቸው የብር ኖት ሀሰተኛ መሆኑን ከተረዱ በኋላ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ነው።

ፖሊስ ባካሄደው የማጣራት ስራ ግለሰቡ ለባሱቆች ከሰጣቸው 20 ሺህ ሀሰተኛ ባለ መቶ የብር ኖት በተጨማሪ አንድ ካርቶን ሀሰተኛ የብር ኖት ወደ ወረዳዎች እንደተሰራጨ መረጃ ማግኘቱን ተናግረዋል።

በወረዳዎች የተሰራጨውን ሀሰተኛ የብር ኖት ለመያዝም ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

”በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር በዋለው ግልሰብ ላይ  የምርመራና የማጣራት ስራ እየተከናወን እንደሚገኝ ጠቁመው ሂደቱ እንደተጠናቀቀም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የሚላክ ይሆናል “ብለዋል።

በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ የጋምቤላ ከተማ ኦፔኖ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ግሩም አበራ በበኩላቸው  በጋምቤላ ከተማና አካባቢው በርካታ ሀሰተኛ የብር ኖት ስርጭት  እንዳለ ምልክቶች ስለሚያሳይ ህብረተሰቡ  በግብይት ወቅት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በቅርቡ በአንድ ደንበኛ ወደ ባንኩ ሊገባ ከመጣ 90 ሺህ ባለ መቶ የብር ኖት ውስጥ 20 ሺህው  ሀሰተኛ የብር ኖት ሆኖ መገኘቱንና ጉዳዩንም ለፖሊስ በማሳወቅ እንዲያዝ መደረጉን ገልጸዋል።

ከአሁን በፊት ይገኝ የነበረው የሀሰተኛ የብር ኖት አንድና ሁለት ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ስራ አስኪያጁ በተወሰነ ብር መካከል ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሀሰተኛ የብር ኖት መገኘቱ በርካታ ስራጭት መኖሩን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ግብይት በሚያደርግበት ወቅት በተለይም በብር ኖቶች ላይ ያለውን የዘንግ ምልክቱን በማየት መጠቀም እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፖላንድ

በህገ ወጥ መንገድ ስራ እናስቀጥራችኋለን በሚሉ ደላሎች ተታለው ወደ ፖላንድ ያቀኑ ኢዮጵያውያን ለከፋ ችግር መዳረጋቸው ተገለፀ።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ህጋዊ ባልሆነና ትክክለኛ መረጃ ሳይዙ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለስራ ፍለጋ ጉዞ የሚያደርጉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር #እየተበራከተ መምጣቱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

የእነዚህ ዜጎች የጉዞ መነሻ ምክንያትም ነፃ የትምህርት እድል ለማግኘት አሊያም ዳጎስ ያለ ክፍያ የሚያስገኝ የስራ ዕድል ታገኛላቹህ በሚሉ ህገ ወጥ ድላሎች እና ድርጅቶች በመታለል ነው።

በአሁኑ ወቅት በብዛት በዚህ የህግ ወጥ ደላሎች ወጥመድ ገብተው ከሚጓዙት መካከል ወደ ቻይና የሚጓዙ ኢትዮጵያን ተጠቃሽ ሲሆኑ፥ ከቅርብ ወራት ወዲህ ደግሞ ወደ ፖላንድ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እያሻቀበ ነው።

ፖላንድ የሚገኘው የኢትዮዽያ እና ፖላንድ ማህበር ሰላም ሊቀመንበር መርሻ ወልዱ ለfbc እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያዊያኑ ፖላንድ ውስጥ ትልቅ ክፍያ የሚያስገኝ ስራ ትቀጠራላቹ በሚል እየተታለሉ ለከባድ ችግር እየተዳረጉ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ዜጎቻችን ዋርሶ ውስጥ የተሻለ ስራ ታገኛላቹ ተብለው መጥተው ያሰቡት ሳይሆን ቀርቶ ለእንግልት እየተዳረጉ ነው ያሉት ሃላፊው፥ ይህም እንደ ማህበረሰብ ሆነ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የሚያስጨንቅ እና የሚያሳስብ ጉዳይ ነው ነው ይላሉ።

አቶ መርሻ ወደ ፖላንድ ጉዞ ማድረግ የሚፈልጉ ዜጎች በአሁኑ ወቅት ፖላንድ በስደተኞች እና ፍልሰተኞች እንዲሁም በህገ ወጥ ኗሪዎች ላይ ጠንካራ ህግ የምትከተል መሆኗን ማወቅ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።

የዋርሶ ቀኝ አክራሪ ፖለቲከኞች አባል የሆኑበትን የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች ጉዳይ ፖሊሲ ሳይቀር እየተቃወሙ ስደተኞችን በኮታ የመቀበልን ጥያቄ ውድቅ እያደረጉ ናቸው ብለዋል።

አቶ መርሻ ፖላንድ አሁን ላይ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሀገሯ ከማስትናገድ ይልቅ ወደ መጡበት ሀገር በመመለስ በሀገራቸው መንግስት ጋር የማቋቋም ስራ ነው እየሰራች ያለቸው ብለዋል።

በድርጅቶች እና በግለሰቦች ቅስቅሳ እየተገፋፉ ከ8 ሺህ ዶላር እስክ 300 ሺ ብር የሚከፍሉ ወገኖቻቸን አካሄዳቸውን ቆም ብለው ሊያጤኑት ይገባልም ነው ያሉት።

ከተሰጡት ሃላፊነቶች መካከል አንዱ የዜጋ ዲፕሎማሲን ማካሄድ የሆነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፥ ይህን ጉዳይ እንዴት ያየዋል በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት በአሁኑ ወቅት በውጭ ሀገራት ለሚገኙ ዜጎች ደህንነት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናገረዋል።

ቃል አቀባይ ነብያት መንግስት ይህን መሰል ድርጊት ለመከላከል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከኤምባሲዎች ጋር እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን፥ ዜጎች በራሳቸው ሊወስዱት የሚገባ ሃላፊነት እንዳለም አንስተዋል።

የስራ እድል ተገኝቷልና ነጻ የትምህርት እድል አግኝታቹሃል ሲባሉ እንቅስቃሴ ውስጥ ከመግባት አስቅድመው ስለ መረጃው ትክክለኛነት ከሚመለከታቸው ተቋማት ማረጋገጫ ማግኘት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ቃል አቀባዩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ሀገራት ችግር እያጋጠማቸው ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ከመመለስ ባለፈ፥ ለዚህ ችግር የዳረጋቸውን መነሻ ክፍተት ለመድፈን ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia