TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

“ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” - የሟች ቤተሰብ

“ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ

ወጣት ሶፎኒያስ አስራት የሚባል ሹሬር ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ ሰዎችን አሳፍሮ እንደወጣ አለሙለሱን፣ በመጨረሻም ሹፌሩን ገድለው ፣ ተሽከርካሪውን ይዘው እንደተሰወሩ፣ ገዳዮቹ አስካሁን #እንዳልተያዙ፣ በዚህም መሉ ቤተሰቡ መራራ ሀዘን ውስጥ መሆናቸውን የሟች ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሟች ቤተሰብ በሰጡት ቃል፣ “ ከላፍቶ ነበር መነሻውን ያደረገው (ልዩ ስሙ መስቀልኛ የሚባለው አካባቢ ናሆም ሆቴል የሚባል አለ)። ከዚያ ነበር ሦስቱንም ተሳፋሪዎች ማክሰኞ ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ያሳፈራቸው። መዳረሻቸውን ‘ቦሌ ሚካኤል’ ብለው ነበር መሳፈር የፈለጉት ” ብለዋል።

“ ትንሽ ወረድ እንዳለ/እንደተጓዘ ከእኔ ጋር ተገናኝተናል። አብረን የምንሰራበት ቦታ ነው። ሦስት ሰዎች እንዳሳፈረ አይቻለሁ” ያሉት የሟች ቤተሰብና የዓይን እማኝ፣ “ሶፊ ወዴት ነህ ስለው ‘መጣሁ። ቦሌ ሚካኤል አድሻቸው ልምጣ’ አለኝ። በቃ ደርሰህ ና ስራ የለም እንገናኛለን ተባባልን። በዛው እንደወጣ አልተመለሰም ” ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

አክለውም፣ ጠዋት ላይ ላፍቶ ፓሊስ ጣቢያ ሲያመለክቱ የቃሊቲ ፓሊስ ጣቢያ እንዲጠይቁ እንደነገሯቸው፣ ቃሊቲ ፓሊስ ጣቢያ ሲጠይቁ ፓሊስ ስለተፈላጊው ሰው ሙሉ መለያ መረጃ ከጠየቃቸው በኋላ “ እንግዲህ ጠንከር በሉ። ኤቲኤሙን አግኝተናል። አሁን ያለው ጳውሎስ ሆስፒታል ነው። አዲስ አበባ ፓሊስ ሂዳችሁ ቃል ሰጥታችሁ ትወስዳላችሁ ” ብለው #መገደሉን እንዳረዷቸውም ተናግረዋል።

“ ማሰልጠኛ ተሻግሮ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ዳር ላይ ነው ሞቶ የተገኘው። ፓሊሶች አስከሬኑን ያነሱት ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ነው። ከጥበቃ ሥራ የሚመለሱ አንድ አባት ናቸው በወደቀበት አግኝተውት ጥቆማ አድርገው ፓሊስ የሄደው ” ነው ያሉት።

“ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” ያሉት የሟች ቤተሰብ፣ ማንም ጋ ፀብ እንዳልነበር ገልጸው፣ ሙሉ ቤተሰቡ ሀዘን ላይ እንደሆነ፣ ቢያንስ ገዳዮቹ እንዲያዙ ፓሊስ ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ስለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ ስለሟች ሁኔታ ጠይቀው ጉዳዩን እንዲያጣሩ ፋታ እንዲሰጣቸው ከጠየቁ በኋላ በሰጡት ቃል ፣ “ አረጋግጫለሁ። ፓሊስ ሥራ ላይ ነው ያለው። የተለያዩ ዝርዝር መረጃዎችን ለመግለጽ የሚያስፈልግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ” ብለዋል።

“ መረጃ እየተሰበሰበ ነው ያለው ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ “ አንተ ማክሰኞ ሌሊት 8 ሰዓት አልከኝ እንጂ፣ ስጠይቅ ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ 8 ሰዓት ላይ ነው ወንጀሉ የተፈጸመው የሚል መረጃ ነው ያለው። ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ” የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ወንጀሉ የተፈጸመው ማክሰኞ ሌሊት 8 ነው ያሉት የሟች ቤተሰብ በስህተት እንዳይሆን በሚል በድጋሚ የጠየቀ ሲሆን፣ ማክሰኞ ለረቡዕ ሌሊት 8 ሰዓት እንደሆነ፣ ረቡዕ ማታ ጣቢያ አስክሬን እንዳገኙ አስረድተዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia