TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመከላከያ ሰራዊት ቀን🔝

7ኛው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል #አሶሳ ከተማ እና በአማራ ክልል #ባህርዳር ከተማ በፓናል ውይይት በመከበር ላይ ነው።

“ህገ መንግስታዊ ስረአታችንና ህዝባዊ ባህሪያችንን ጠብቀን የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን'' በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

የምእራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ አስተዳደር ብርጋዴል ጄነራል እንዳልካቸው ወ/ኪዳን በውይይቱ ላይ እንዳሉት በህገ መንግስታዊ መርሆዎች የተቋቋመው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚሰጠውን ተልእኮዎችን በላቀ ድል እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ታሪካዊ አመሰራረት ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። በፓናል ውይይቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት የህዝብ ወኪሎ፣ የምእራብ ዕዝ እና የ22ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የሰራዊት አባላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ሪፖርተራችን ያለለት ወንድዬ ከአሶሳ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና በባሕር ዳር ከተማ ሙሉዓለም የባሕል ማዕከል 7ኛው የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን እየተከበረ ነው፡፡

በበዓሉ ላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ መንግሥት ሰላምና ደኅንነት አባላትና አመራሮች፣ የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ከፍሎች እየታደሙ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክረተሪያት ኃላፊ አቶ #ንጉሡ_ጥላሁን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናትም በበዓሉ አከባበር እየተሳተፉ መሆኑን አብማድ ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia