TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለመላው ኢትዮጵያዊያን‼️

"በመላው አገሪቱ በመደበኛነት #በድርቅ_አደጋ የሚረዱ ከሰባት #ሚሊዮን በላይ ዜጎች አሉ ለጋሽ አካላት የተለመደ #ትብብራቸው እንዲያደርጉ ተጠይቋል።"
.
.
አንዳንዶቻችን ይሄን ረስተነው ይሆን በትንንሽ ጉዳዮች ተለያይተን እየተባላን የምንውለው?? ዛሬም በብሄር ተከፋፋለን የምንበሻሸቀው?? በጥላቻ ተሞልተን ስንሰዳደብ የምንውለው?? ዛሬም ሀገራችን #ለጋሾች እጃቸውን እንዲዘረጉላት #እየተማፀነች ነው። ዛሬም በሀገራችን በድርቅ አደጋ የሚረዱ በሚሊዮኖች ናቸው። ወገኖቼ ይህን ታሪካችንን እስከወዲያኛው ልንቀይር ይገባናል። ይህን መጥፎ ስም የምንቀይረው #በፌስቡክ ብሽሽቅ እና ስድብ፤ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሚሰጡን አጀንዳዎች እየተባላን አይደለም‼️ ተባብረን ሰርተን ከዚህ የደህነት እና የችግር ስም መውጣት አለብን‼️

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀሰተኛ ወሬዎች ተጠንቀቁ‼️

በአሐዱ ሬዲዮ ከአቶ #ጃዋር_መሃመድ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ተብሎ #በፌስቡክ የተሰራጨው መረጃ #የተሳሳተ መሆኑን አሐዱ ራድዮ በዛሬው ዕለት ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢራቅ‼️

በኢራቅ የካቢኔ አባላት #በፌስቡክ ማስታወቂያ ተመረጡ፡፡ የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር #አደል_አብዱል_ማህዲ በበይነ መረብ ከተወዳደሩ 15 ሺ ሰዎች መካከል የካቢኔያቸው አባል የሚሆኑ 5 ሰዎችን መርጠዋል። ይህ በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት ውስጥ ያልተለመደ የቅጥር መንገድ መጀመሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ማህዲ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተዋወቀ ሲሆን ከሚያስፈልጉት 14 የካቢኔ አባላት መካከል 5ቱ በዚህ መንገድ ተመርጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እርስ በእርስ ተጋጭተው የ3 ተማሪ ህይወት ጠፋ እየተባለ #በፌስቡክ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው። ግቢውም ሆነ ከተማው ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

#ሼር ወላጆቻች ጋር እንዲደርስ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Amhara

የአማራ ክልል ህዝብ ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው የመንግስት አካል እንዲወስድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር አሳሰቡ።

አቶ አገኘው ይህን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት ዛሬ ለአማራ ክልል ህዝብ የክተት አዋጅ ባወጁበት ወቅት ነው።

ኅብረተሰቡ መረጃ እንደሚያስፈልገው እናውቃለን ያሉት አቶ አገኘሁ ፥ ነገር ግን ሁሉም የጦርነት መረጃ አይሰጥም ብለዋል። "በዚህ በኩል እያጠቃን ነው፤ በዚህ በኩን እየተጠቃን ነው ፤ በዚህ በኩል እንዲህ አይነት ወታደራዊ መሬት ይዘናል ተብሎ መረጃ አይሰጥም" ሲሉ አስገንዝበዋል።

አንዳንዱ #በፌስቡክ ጦርነት ሊመራ ይፈልጋል ይህ ተገቢ አይደለም መታረም አለበት ብለዋል።

አስፈላጊው መረጃ በፌዴራል እና በክልል መንግሥታት የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ይሰጣል ያሉ ሲሆን ህዝቡ መረጃዎችን ከትክክለኛው አካል መውሰድ እንደሚገባው አሳስበዋል።

ትግራይ ክልልን በሚያዋስኑት የአማራ ክልል እና በአፋር ክልል አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች መቀጠላቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች ቢኖሩም መሬት ላይ ስላለው ሁኔታ ለማወቅ ፍፁም አዳጋች ሆኗል።

ትክክለኛ መረጃ ባለመኖሩም ህዝቡ ለፕሮፖጋንዳ እና ለሀሰተኛ መረጃዎች ፣ እንዲሁም ለአክቲቪስቶች ያልተጨበጠ ወሬ እንዲጋለጥ ማድረጉን በርካቶች እያነሱ ነው።

@tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት መለዋወጫ !

ከዚህ ቀደም ተከፍተው አገልግሎት ላይ የነበሩት የመልዕክት መቀበያዎች በተደጋጋሚ በቴሌግራም ቴክኒንክ ችግር አገልግሎታቸው እየተደነቃቀፈ ነው።

በዚህም ምክንያት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚመጡትን መልዕክቶች ለማግኘት ችግር ሆኗል ፤ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ችግሩን ለመቅረፍ እና በየትኛውም መልኩ ነፃነቱ የተጠበቀ ለቲክቫህ አባላት ብቻ የሚያገለግል የሀሳብ መለዋወጫ በቅርቡ ይፋ የምናደርግ ሲሆን እስከዛው ድረስ ግን በዚህ አዲስ መልዕክት መቀበያ ላይ ብቻ መልዕክት ማጋራት ይቻላል  👉@tikvah_eth_BOT

በተጨማሪ @tikvah_Ethiopia_Fam ወይም ደግሞ 0703313630 መደወል ይቻላል።

በቲክቫህ ቤተሰብ ውስጥ ማስተላለፍ የሚቻሉ መልዕክቶች ምን አይነት ናቸው ?

- የፀጥታ ችግሮች፣ የደህንነት ስጋቶች፣ የወንጀል ድርጊቶች በመንግስት አካላት / ተቋማት የሚፈፀሙ ማንኛውም አይነት አስተዳዳራዊ በደሎች፤
- የየመንገድ ፣ የውሃ፣ እንዲሁም የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚና የሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎች፤
- በግልም ሆነ በጋር የማያጋጥሙ ችግሮች፣ ሊበረታቱ የሚግባቸው ተግባራት፣
- ለሀገር እና ለትውልድ ጠቃሚ ናቸው የሚባሉ ሃሳቦችን፣
- የእርስ በእርስ እገዛዎች ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች፣
- ጥቆማዎችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ይሄ ነገር ለቤተሰቡ ቢጋራ መልካም ነው የምትሉትን (ዜና ፣ መረጃ) ሁሉ ማቅረብ ትችላላችሁ።

ምን መላክ አይቻልም ?

ስድብ፣ የጥላቻ ንግግር ፣ የማንኛውም የግለሰብ ማንነትን በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካ ፣ ህዝብን በጅምላ የሚፈርጅ፣ ፣ ህዝብ ላይ ጥላቻን የሚያሰርፅ፣ ሀገር ሊያስጣ የእርስ በእርስ ግጭት የሚያባብስ፣ ሀሰተኛ መረጃ ፅሁፍ / መልዕክት መላክ በፍፁም አይቻልም። በየትኛውም አካል ላይ ትችትም ይሁን ቅሬታ ለመግለፅ የሚፈልግ የቤተሰቡ አባል የሚጠቀማቸውን ቃላት የመምረጥ ግዴታ አለበት።

ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም መልዕክት ስትልኩ የራሳችሁ የግላችሁ መልዕክት መሆኑን በማስረጃ አስደግፋችሁ ላኩልን። እናተ ያላረጋገጣችሁትንና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስላያችሁት የራሳችሁ በማስመሰል ማንኛውም መልዕልት መላክ ፍፁም አይቻልም።

ማስታወሻ ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት #በፌስቡክ#ዩትዩብ#ቲክቶክ ላይ ምንም አይነት የመሰባሰቢያ መድረክ (ገፅ) የላቸውም።

ትዊተር ፦ https://twitter.com/tikvahethiopia?t=jZrpieALuIGzw6OM-HWgEw&s=09

ሀሳባችን ስንገልፅ ቃላትን እንምረጥ !!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ!!
#TikvahFamily

@tikvah_eth_BOT
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ታዬ ከሰሞኑን ምን ሲሉ ነበር ? ዛሬ ታህሳስ 1/2016 ዓ/ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፊርማ ባረፈበት ደብዳቤ ከሰላም ሚኒስትር ዴኤታነት መነሳታቸው የተገለፀላቸው አቶ ታዬ ደንደአ ከሰሞኑን አነጋጋሪ ቃለ ምልልሶችን ሲሰጡ ነበር። ለአብነት ፦ ▪️የቲክቫህ - ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባልን ጨምሮ ፤ ለተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች በአዳማ በነበረ አንድ ፕሮግራም በሰጡት ቃለ ምልልስ ተከታዮቹን…
አቶ ታዬ #በሕግ የሚያስጠይቃቸው ጉዳይ ይኖር ይሆን ?

" በሕግ መጠየቅ ምን ችግር አለው፤ ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ " - አቶ ታዬ ደንደአ

አቶ ታዬ ደንደአ ከሰላም ሚኒስትር ዴኤታነት መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ከደረሳቸው እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ጠንካራ ትችት ከሰነዘሩ በኃላ ማምሻውን ለ " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

አቶ ታዬ ደንደአ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሥልጣን የተሰናበቱት በአገሪቱ ያለው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ በማቅረባቸው እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል።

" ስለእርቅ ስለተናገርኩ ጦርነት ይቁም ስላልኩ እንጂ ሌላ ምክንያት የለም " ያሉት አቶ ታዬ፣ " በጦርነቱ ጊዜ ጦርነቱን ስደግፍ፣ ሲያበረታቱኝ ነበር። ሕዝቡ ይታረቅ ስንል ነው ያመማቸው። ጠርተው አላናገሩኝም። በአካል አልተገናኘንም " ሲሉ ተናግረዋል።

ስንብታቸውን በተመለከተ #በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩትን ጠንካራ ቃላትን የተጠቀሙት ትችትን በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ታዬ ደንደአ ፤ " ይሄ እውነት ነው። ለሰው አያዝኑም። የሰው ልጅ ሞቶ አውሬ እየበላው ስለ ፓርክ ያወራሉ። ሰው የሚበላው አጥቶ እየሞተ በብዙ ገንዘብ ቤተ መንግሥት ያስገነባሉ " በማለት ወቅሰዋል።

በማህበራዊ ገፃቸው በፃፉት ትችት በሕግ ሊያስጠይቃቸው የሚችል ነገር ይኖር እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ታዬ ለዚህ ዝግጁ መሆናቸውን ፤ ነገር ግን ይህ የሚሆንበት ዕድል እንደሌለ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።

" በሕግ መጠየቅ ምን ችግር አለው ታዲያ። ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ። " ብለዋል።

የመንግሥትና የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆነው በጠንካራ ትችታቸው የሚታወቁት አቶ ታዬ ሰሞኑን በተከታታይ የሰነዘሯቸው አስተያያቶች ለስንብታቸው ምክንያት ይሆናል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል።

አቶ ታዬ ፤ " ከዚህ ጋር የሚገናኝ አይመስለኝም። ከፓርቲያችን መርሆች ውስጥ ነጻነት አንዱ ነው። ከዚህ መርህ በተቃራኒ መቆም ተገቢ አይደለም። እኔ ስናገር የነበረው ይህንን መርህ መሠረት በማድረግ ነው " ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሆነ ሰላም ሚኒስቴር እስካሁን ስለጉዳዩ ያሉት ነገር የለም። ነገር ግን አቶ ታዬ ከስልጣን መሰናበታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
" ነገሩ ሁሉ በጥድፊያ ነበር የሆነው #በፌስቡክ የተለቀቀውን ፎቶ እንኳን መነሳቴን አላውቅም " -  ወ/ሮ አማረች ያዕቆብ

ከወር በፊት በመንግሥት የኮሚኒኬሽን ገጾች ፣  በመንግሥት ሚዲያዎች እና ከነዚህ በወሰዱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች አንዲት ሰራተኛ " መድሃኒት ሰርቃ ልትወጣ ስልት እጅ ከፍንጅ ተይዛ በቁጥጥር ስር ዋለች " የሚል ዜና መሰራጨቱ ይታወሳል።

ይህች ግለሰብ ወ/ሮ አማረች ያዕቆብ ትባላለች።

በወላይታ ዞን ፣ አባላ አባያ ወረዳ ከምትሰራበት የህክምና ተቋም ተረኛ ሆና ለሊት አድራ ልትወጣ እየተዘጋጀች በነበረበት ወቅት መድሀኒት ጠፋ ተብሎ ሲፈለግ ቆይቶ በመጨረሻ እርሷ ትያዛለች።

" መድሃኒቱ ግን የእርሷ ባልሆነ ጋወን ውስጥ መገኘቱን " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጻለች።

ወ/ሮ አማረች ፥ " መድሀኒት ስትሰርቅ እጅ ከፍንጅ ተያዘች " ተብላ በጥድፊያ ለእስር እና ለእንግልት መዳረጓን አስረድታለች።

ይህ ሳያንስ የመንግስት ኮሚኒኬሽኖች ገጾችና የመንግስት ሚዲያዎች ዜናውን በማህበራዊ ገጾቻቸዉ ማራገባቸዉ ለከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት እንደዳረጋት ተናግራለች።

በመጨረሻ በእስር ቤት ውስጥ እያለች የደረሱላት የጠበቆች ቡድን እውነቱን አውጥተው ነጻ እንዳደረጓት ገልጻለች።

" እነሱ ባይደርሱልኝ ኖሮ ባልሰራሁት ወንጀል ወደ ወህኒ ልወርድ ነበር " ያለችው ወ/ሮ አማረች " ጉዳዩን አሁን ላይ ሳስበው ህልም መስሎ ነው የሚታየኝ " ብላለች።

በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን የሰጡት የጠበቆች ቡድን አባሉ ጠበቃና የህግ አማካሪዉ አቶ መብራቱ ኮርኪሳ ፥ " በደንበኛችን ላይ የቀረበዉ የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ #ነጻ_ተብላ_የመገመት መብቷን ከመጣስ ባለፈ ሁኔታዉን ለማጣራት ስንሞክርም ብዙ የሚያጠራጥሩ መረጃዎች ልናገኝ ችለናል " ብለዋል።

በዚህም በወላይታ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተበዳዩዋን የዋስ መብት ከመጠየቅ አንስቶ " በነጻ በእስር እስክትወጣ ድረስ ታግለናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላዉ የጠበቆች ቡድን አባሉ የህግ ጠበቃ እና መምህሩ አቶ አበባየሁ ጌታ ፤ " ክሱን ያቀረበባት አቃቤ ህግ ያቀረባቸዉ ምስክሮች በሰጡት ቃል ወንጀሉን እንዳልፈጸመች ማረጋገጡን ተከትሎ ፍ/ቤቱ በነጻ አሰናብቷታል " ብለዋል።

አሁን ላይ ነጻ ብትወጣም የደረሰባት የስም ማጥፋት ከፍተኛ የስነልቦና ጫና እንዳሳደረባት ጠቁመዋል።

ከዚህ በኋላ የሚቀረዉ በሚዲያ የጠፋዉን ስሟን የመመለስና ለደረሰባት ጉዳት ካሳ የመጠየቅ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ይህም በግለሰቧ ፍላጎት የሚመሰረት ነው ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia