በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በዘጠኝ ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከግንቦት 2016 ዓ/ም ጀምሮ ያልተከፈላቸው የተጠራቀመ የትርፍ ሰዓት ስራ (ዲዩቲ) ክፍያቸው ሳይከፈላቸው እንደቆየ ተናግረዋል።
ክፍያቸው እንዲፈጸምላቸው ተደጋጋሚ የሆነ ጥያቄ ለወረዳው እና ለጤና ጽ/ቤቱ ሲጠይቁ የቆዩ ሲሆን የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ከ6 ወር ክፍያው ውስጥ የ2 ወሩን እንደከፈላቸው ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያቀረቡ የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎች የቀረውን የ4 ወር ክፍያ ለመፈጸም ግን ከወረዳው " በጀት የለንም " የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
ያነጋገርናቸው የጤና ባለሞያዎች " ወረዳው በክልሉ ካሉ የሰላም ወረዳ (ቀጠና) አንዱ ነው የመንግስት ስራ በሁሉም ሴክተር እየተሰራ ነው ያለው የግብር እና የታክስ መሰብሰብ ስራም በአግባቡ እየተሰራ ነው የበጀት እጥረት አጋጠመን የሚባለው በጭራሽ ከእውነት የራቀ ነው " ብለዋል።
" በዞኑ የሚገኙ አጎራባች ወረዳዎችን፣ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር፣ ባቲ ወረዳ፣ አርጎባ ልዩ ወረዳ እና ሌሎችም ወረዳዎች ለባለሙያዎቻቸው የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከፍለዋል የእኛ በምን ተለይቶ ዘገየ " የሚል ጥያቄን አንስተዋል።
በወረዳው ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች አንዱ ከሆነው " ደጋን " ጤና ጣቢያ ሁለት የጤና ባለሞያዎች ማክሰኞ 03/03/17 ዓም በጸጥታ አካላት ተወስደዋል።
የጤና ባለሞያዎች ለእስር የተዳረጉት ካልተከፈላቸው ክፍያ ጋር በተገናኘ የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዲከፈላቸው የሚጠይቅ ጽሁፍ " በሶሻል ሚዲያ አጋርታቹሃል " በሚል ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።
ባለሞያዎቹ ከ4 ቀናት እስር በኋላ ትላንት ምሽት ተፈተዋል።
የቃሉ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን አህመድ ለጤና ባለሞያዎቹ ክፍያው በእርግጥም አለመፈጸሙን አረጋግጠው ያልተከፈላቸው ግን በበጀት እጥረት ምክንያት አለመሆኑን ተናግረዋል።
" ክፍያው የዘገየው በየጤና ጣቢያዎቹ የሚሰጠው አገልግሎት እና የሥራ ጫና የሚለያይ በመሆኑ የሚያድረው የጤና ባለሞያ ቁጥርም ይለያያል በዛ ምክንያት ደረጃ ይውጣለትና በሚሰጡት አገልግሎት እና ባለባቸው የስራ ጫና ልክ ይከፈላቸው ተብሎ ይህንን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳው በሚገኙ በዘጠኙም ጤና ጣቢያዎች እያጣራ ነው ሪፖርቱን እንዳቀረበ ይከፈላቸዋል " ብለዋል።
በሌሎች ትይዩ ወረዳዎች ላይ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ችግር የለም ይህ በቃሉ ወረዳ ለምን ተፈጠረ ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ " የእኛ ወረዳ ከሌሎች የጎንዮሽ ወረዳዎች ጋር ለማነጻጸሪያ ቢቀርብ የተሻለ ከፋይ ነው " ብለዋል።
ታሰሩ ስለተባሉት ባለሞያዎች መረጃው እንደሌላቸው ተናግረው በሌላ ጉዳይ ተጠርጥረው ካልታሰሩ በቀር በክፍያው ጉዳይ አይታሰሩም ብለዋል።
" ከተያዙም ሌላ የጸጥታ ስራ ስላለ በዛ ምክንያት ተጠርጥረው ነው የሚሆነው በተባለው ምክንያት ከሆነ ግን አጣርቼ ልጆቹን ትሪት አደርጋለው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የጤናባለሞያዎችድምጽ
🔴 " ከደመወዝ ጋር ይከፈለናል ብለን በተስፋ ስንጠብቅ አሁንም ሳይከፈለን ቀርቷል " -ቅሬታ አቅራቢ የጤና ባለሞያዎች
🔵 " ምን ያህል ይታገሱ የሚለውን አላውቅም " -የወረዳው አስተዳዳሪ
በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በ9 ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከግንቦት 2016 ዓ/ም ጀምሮ የተጠራቀመ የትርፍ ሰዓት ስራ (ዲዩቲ) ክፍያቸው እንዳልተከፈላቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ባለሞያዎቹ ያልተከፈላቸው የ2016 ዓ/ም የግንቦት እና የሰኔ ወር እንዲሁም በ2017 ዓ/ም የ3 ወር በጠቅላላው የ5 ወር የዱዩቲ (የትርፍ ሰዓት) የሰሩበት ክፍያ ነው።
መረጃውን ባጋራንበት ወቅት ባለሞያዎቹ ያልተከፈላቸው የ4 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቃሉ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ሙህዲን አህመድን በጉዳዩ ላይ አነጋግሮ ነበር።
አስተዳዳሪው " ክፍያው የዘገየው በየጤና ጣቢያዎቹ የሚሰጠው አገልግሎት እና የሥራ ጫና የሚለያይ በመሆኑ የሚያድረው የጤና ባለሞያ ቁጥርም ይለያያል በዛ ምክንያት ደረጃ ይውጣለትና በሚሰጡት አገልግሎት እና ባለባቸው የስራ ጫና ልክ ይከፈላቸው ተብሎ ይህንን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳው በሚገኙ በዘጠኙም ጤና ጣቢያዎች እያጣራ ነው ሪፖርቱን እንዳቀረበ ይከፈላቸዋል " ማለታቸው ይታወሳል።
አስተዳዳሪው ይህንን ምላሽ ይስጡ እንጂ የባለሞያዎቹ የትርፍ ሰአት ክፍያ ሳይከፈል 5 ወር ማለፉን የጤና ባለሞያዎች በድጋሚ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ባለሞያዎቹ " የሰራንበትን ክፍያ እንዲከፈለን ደጋግመን ብንጠይቅም የሚሰማ አመራር በማጣታችን አሁንም ለችግር ተጋልጠናል " ብለዋል።
" በህዳር ወር መጨረሻ ከደመወዝ ጋር ይከፈለናል ብለን በተስፋ ስንጠብቅ አሁንም ሳይከፈለን ቀርቷል ለምን ? ብለን ስንጠይቅ እንደገና በወረዳው ጤና ጥበቃ ኦፊሰሮች ኮሚቴ ተዋቅሮ 9ኙም ጤና ጣቢያዎች ቼክ ይደረጉ ተብሎ ከወረዳ አስተዳደር አቅጣጫ ተቀምጧል በዚህ ወር የሰራችሁበት አይከፈላቹም " የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወረዳውን አስተዳዳሪ የጤና ባለሞያዎቹ ምን ያህል ጊዜ ይታገሱ ሲል በድጋሚ ጠይቋል " ምን ያህል ይታገሱ የሚለውን አላውቅም በቴክኒክ ኮሚቴው ተጨማሪ ጥናት እየተደረገ ነው እሱ እንዳለቀ ይከፈላቸዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ወረዳው ኮሚቴዎችን አዋቅሮ በዘጠኙም ጤና ጣቢያ ጀምሮት የነበረውን የማጣራት ስራ ካጠናቀቀ በኋላ በድጋሚ ጤና ጣቢያዎቹ በራሳቸው የማጣራት ስራ ጀምረዋል ይህ ለምን ሆነ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " ተቋማቱ (ጤና ጣቢያዎቹ) እኛም ቼክ እናድርግ አሉ እኛ ከሰራነው ጋር ያለውን mismatch (ልዩነት) እንየው ከቴክኒኩ ውጤት ጋር ይገጥማል ወይስ ልዩነት አለው የሚለውን ለማየት ፈልገው ስለሆነ እሱ እንዳለቀ ይከፈላል " ሲሉ መልሰዋል።
ሃላፊው በወረዳው ደረጃ የሰሩት የጥናት ውጤት ምን እንደሆነ ከመናገር የተቆጠቡ ሲሆን ተጨማሪ ምላሽ ለመስጠትም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ጋሻው ምን ምላሽ ሰጡ ?
ሃላፊው " የጤና ጣቢያዎቹ አሰራራቸውን ማየት ስላለብን በድጋሚ ጀምረናል የሚሰጡት አገልግሎት እና የባለሞያው ቁጥር ትንሽ ይጣረሳል " ብለዋል።
ጥናቱም በዚህ ሳምንት እንደሚያልቅ እና በውጤቱም መሰረት እንደሚከፈላቸው ተናግረዋል።
" ነገሩን ማስተካከል ስለሚቻል በዚህ ሳምንት ጨርሰን ያለውን ነገር ችግሮቹን ለይተን የሚከፈለው ካለ ይከፈላል ያልሰራበትንም የወሰደ ካለ በምርመራው መሰረት ያሰራውም አካል የወሰደውም አካል ተጠያቂ ይሆናል " ነው ያሉት።
" ጥናት ማድረግ የተለየ ነገር አይደለም አሰራርን መፈተሽ ያለ ነው ለሰራተኛውም ይጠቅማል የሚሰራውን እና የማይሰራውን ለመለየትም ያግዛል " ሲሉ አክለዋል።
ጥናቱን ከጨረሳችሁ በኋላ የቀረውን ክፍያ በሙሉ ትከፍላላቹ ወይስ እየቀነሳቹ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ " እሱን ከጥናቱ በኋላ ነው የምናየው ግን የሰሩበት ይከፈላል " ብለዋል።
በውጤቱ መሰረትም በጣም ኬዝ ሎድ ኖሮባቸው ዝቅተኛ የሚከፈለው ካለ ክፍያውን ሊሻሻል እንደሚችል እና ምንም ሳይሰራ እንደ መርሐ ግብር የሚከፈለው ካለም ክፍያውን ሊያጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

🔴 " እስከሚከፈለን ድረስ ወደ ሥራ ላለመመለስ ተስማምተናል ለሁሉም ባለሞያ እስከሚከፈል ድረስ አንሰራም " - የጤና ባለሞያዎች
🔵 " ዝም ያለ አካል የለም ዘግቶ መሄዳቸው ትክክል አይደለም " - የጤና ቢሮ ሃላፊ
በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በዘጠኝ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የትርፍ ሰዓት ስራ(ዲዩቲ) ክፍያ ስላልተከፈላቸው 05/05/17 ዓ/ም ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል።
ባለሞያዎቹ ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በተለያዩ ጊዜያት ያልተከፈላቸው የ1 አመት ከ 5 ወር በላይ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ መኖሩን ተናግረዋል።
እስከ ክልሉ የበላይ አካላት ድረስ ሄደን ጠይቀናል በተደጋጋሚ የሚሰጠን ምላሽ ግን " ታገሱ " የሚል ነው በዚህ ምክንያት ተነጋግረን ስራ ለማቆም ተገደናል ነው ያሉት።
" አብዛኛው ባለሞያ ከወረዳው ሸሽቶ ወደተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ ተደብቆ ነው ያለው አመራሮችም በአንቡላንስ ቤት ለቤት በመሄድ የህክምና ባለሞያዎችን እያፈለጉ እያስፈራሩ ነው " ብለዋል።
ባለሞያዎቹ " በተለያዩ ጊዜያት ከወረዳ እና ከዞን አመራሮች ጋር በርካታ ውይይቶችን አድርገናል ነገር ግን ' ግብር እስከሚሰበሰብ ጠብቁ፣ ገንዘብ የለም ታገሱ ' ከማለት የዘለለ እስካሁን ምንም ምልሻ ባለመግኘታችን እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ተገደናል ነው " ያሉት።
" እስከሚከፈል ድረስ ወደ ሥራ ላለመመለስ ተስማምተናል ለሁሉም ባለሞያ እስከሚከፈል ድረስ አንሰራም የተጠራቀመ ክፍያው እስከ 100 ሺ የደረሰለት ባለሞያም አለ " ብለዋል።
" በዚህ ደመወዝ ፣በዚህ ኑሮ ውድነት መኖር አልቻልንም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ነው የደረስነው ልጆች ያላቸው ልጆቻቸውን ማሳደግ አልቻሉም መስራትም መኖርም አልቻልንም ይሄንን እርምጃ ስንወስድም ወደ ፖለቲካ ተቀይሮ ' ትታሰራላቹ ' ወደ ሚል ማስፈራሪያ ተሸጋግረዋል " ሲሉ አክለዋል።
ባለሞያዎቹ በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ጤና ጣቢያዎች አድማው ቢቀጥልም ለወሊድ ለሚመጡ እናቶች ብቻ አንዳንድ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ነገር ግን በሁሉም ጤና ጣቢያዎች መደበኛ ስራዎች ማቆማቸውን ተናግረዋል።
የአዳባ ወረዳ የጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሽመልስ ፈይሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የባለሞያዎቹ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ አለመከፈሉን አረጋግጠዋል።
ሃላፊው በዝርዝር ምን አሉ ?
" በየደረጃ ያሉ ቢሮዎችን እየጠየቁ መምጣት ይችሉ ነበር እኔ የቢሮ ሃላፊ ነኝ ወደ እኔ የመጣ የለም ስራቸውን ነው ዝም ብለው ያቆሙት።
የኑሮ ውድነት በሃገሪቱ እና በአለም ያለ ሁኔታ ነው የትርፍ ሰዓት ስራ ባይሰሩም በመደበኛ ስራቸው መገኘት ነበረባቸው የሙያ ስነምግባሩ ይህንን አይፈቅድም።
የገቢ ማነስ ይኖራል፣ የጸጥታ ችግርም ሊኖር ይችላል በእነዚህ ምክንያቶች ነው እንጂ ዝም ያለ አካል የለም ዘግቶ መሄዳቸው ትክክል አይደለም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለሞያዎቹ የጠየቁት ከአመት በላይ ሳይከፈላቸው ስለቀረ ክፍያ ነው ችግሩ በምን ያህል ጊዜ ይፈታል ብለን እንጠብቅ ሲል ጠይቀናቸዋል ? በምላሻቸው ፦
" ከእዚህ በፊት ጥያቄውን ለበላይ አካል አቅርበው ጉዳዩ ወደ ወረዳ እንዲመለስ ተደርጎ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈታል ተብሎ ነበር ለዚህ እንቅስቃሴ እያደረግን ባለበት ሰዓት ነው ይሄ የተፈጠረው ገቢ ላይ የተመሰረት አከፋፈል ነው የሚኖረው ከስር ከስር እየተከፈለ በጊዜ ሂደት ችግራቸው ይፈታል " ብለዋል።
የቦርድ አባላት በየጤና ጣቢያው በመሄድ ሰራተኛው መጥቶ የራሱን ቅሬታ እንዲያቀርብ ጠይቀው እስካሁን መጥቶ ያቀረበ አካል የለም እኛም መፍትሄ ለመስጠት ተቸግረናል ብለዋል።
ሃላፊው ባለው ሰራተኛ ስራው እንዲቀጥል ለማድረግ እየጣርን ነው ያሉ ሲሆን " የሰራተኛው ችግር ምን እንደሆነ በቢሮ ደረጃ አናውቅም መጥቶ ያቀረበልን አካልም የለም " ነው ያሉት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወረዳው የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ከክፍያ ጋር ተያይዞ የሚያነሱትን ጥያቄ ለመቅረፍ ወረዳው ምን ያህል ብር ይፈልጋል ሲል ጠይቋል።
ሃላፊው " የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን በየጊዜው ስለሚጨምር ይሄን ያህል ነው ማለት ያስቸግራል ነገር ግን በ 2016 ዓም ብቻ ያልተከፈላቸውን ክፍያ ለመፈጸም እስከ 5 ሚሊየን ብር ያስፈልጋል " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM