TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የየካቲት 11 የማጠቃለያ ፕሮግራም...

45ኛው ዓመት የየካቲት 11 በዓል ማጠቃለያ ኘሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ ሚለንየም አደራሽ ከ30 ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች፣የብሄር ብሄረሰብ ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በመከበር ላይ ይገኛል።

#TigraiTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ከነገ መጋቢት 19/2012 ዓ/ም ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ ከከተማ ወደ ከተማ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። ከገጠር ወደ ገጠር፣ እንዲሁም ከገጠር ወደ ከተማ ወይም ከከተማ ወደ ገጠር መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። ከነገ ጀምሮ ባለንበት ቦታ ነው የምንቀመጠው።

#DrDebretsionGebremichael #TigraiTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ወደ ትግራይ የሚያስገቡ ዋና መንገዶች አይዘጉም። ነገር ግን ክትትል እና ቁጥጥር ይደረግባቸዋል። አንድ ሰው መቐለ ገብቶ ወደ አዲግራት ወደ አድዋ ወይም ወደ ሽሬ መሄድ የሚባል ጉዳይ አይኖርም። በአንድ መስመር ሰው ከገባ እዛው ቦታ ብቻ ነው መቀመጥ ያለበት። መንቀሳቀስ አይፈቀድም። ይህንን አዎቆ ነው ወደ ትግራይ መግባት የሚቻለው።

#DrDebretsionGebremichael #TigraiTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የተናገሩት፦

...እያየን ያለነው የህዝቡን ጥያቄ የምንመልስበትን የስራ ሂደት ነው። ከኮሮና ቫይረስ ጋር ትግል ላይ ነን፤ የትግራይ ክልል ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው እየሰራን ያለነው።

በክልሉ የወጣው አዋጅም የዚህ አንድ አካል ነው። እስካሁን ድረስ የደም ናሙና ወደአዲስ አበባ እየተላከ ነበር ውጤት የምንጠብቀው የትግራይ ምርምር ማዕከል ከዚህ ቀደም የተለያዩ መሳሪያዎች ነበሩት የጎደለውን ለሟሟላት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

አሁን የኮሮና ቫይረስን የመመርመር ሂደት ላይ ነን። ከአሁን በኃላ ወደ አዲስ አበባ የሚላክ የደም ናሙና አይኖርም።

ማዕከሉ ከአዲስ አበባ የተላከ ፈተና በአግባቡ በማለፍ #ብቃት እንዳለው ተረጋግጧል። አሁን ባሉት መሳሪያዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይጀመራል። በቀጣይ ግብዓቶችን በመጨመር አቅምን ማሳደግ ያስፈልጋል።

#TigraITV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TigraiTV

የትግራይ ቴሌቪዥን በጊዜያዊ የትግራይ ክልል አስተዳደር እየተመራ በቅርብ ቀን መደበኛ ስርጭቱን እንደሚጀምር ዛሬ አሳውቋል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ወደአየር መመለሱንም ለመመልከት ችለናል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
" ለ1,523 ቀናት ያህል በፕላስቲክ ቤት መኖር ይብቃን " - ተፈናቃይ ወገኖች

ዛሬ ጥዋት በመቐለ ሰላማዊ ስልፍ ተካሂዷል።

ሰላማዊ ሰልፉ " በቃን ወደ ቄያችን መልሱን " ባሉ የተፈናቃይ መጠለያዎች ውስጥ በሚገኙ ወገኖች አማካኝነት ነው የተደረገው።

የመቐለ ሮማናት አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ፓሊስ ከተሸከርካሪ እና ከእግረኞች እንቅስቃሴ ነፃ  እንዲሆኑ ተደርገው ነበር።

በመቐለ እና ከመቐለ ውጪ ባሉት የተፈናቃይ መጠለያዎች የሚገኙ ወገኖች " ይበቃል !! " በሚል በሦስት አቅጣጫ ወደ ሮማናት አደባባይ ተሰባስበው ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ሰልፈኞች በሮማናት አደባባይ እንደደረሱ ፦

- ለ1523 ቀናት በፕላስቲክ ቤት መኖር ይብቃን !
- የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉነት ይተግበር !
- ወደ ቤታችን መልሱን !
- ጦርነት እንጠየፋለን ፤ ሰላም እንሻለን !
- ዓለም ድምፃችንን ስሚ !
- በመቀጠል ያለው የተፈናቃዮች ሞት ይብቃ !
- ህገ- መንግስት ይከበር !  ... የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።

ተፈናቃዮቹ በተወካያቸው በኩል ባሰሙት መግለጫ ፥ በመላ ትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች በረሃብ እና መድሃኒት እጦት እየሞቱ መሆናቸው ጠቅሰዋል።

ለማሳያ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ወዲህ  ብቻ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የተፈናቃይ ማቆያ ጣብያዎች ይኖሩ የነበሩ ከ812 በላይ ወገኖች ህይወታቸው ማጣታቸው ገልፀዋል።

መሰል ሰለማዊ ሰልፍ የዛሬን ጨምሮ ለ3 ቀናት እንደሚኖር ተነግሯል። የዛሬው የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ሰላማዊ ነበር።

የተፈናቃይ ስልፈኞቹን ጥያቄ እና የሚመለከተው የመንግስት አካል ምላሽ ካለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ተከታትሎ ያቀርባል።

#TigraiTV #TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia