TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከፊል የፀሀይ ግርዶሽ (ፓርሻል ሶላር ኢክሊፕስ)...

"ከፊል የፀሀይ ግርዶሹን ለመመልከት ወደ ፀሀይ ያለ መከላከያ ፊልተር እንዳትመለከቱ!!" - የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ

Photo Credit: Enbakom Birhanu.
#DebreBirhan 12:50 LT
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DebreBirhan የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ውሳኔዎች ተላለፈ።

ትላንት የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከፓሊስ እና ከቀበሌ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዩ ዉይይት በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚሁ መሰረት ከዛሬ ጥቅምት 10 ጀምሮ በከተማው ውስጥ ለጥበቃ ስራ ከተሰማሩና ከጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጪ ይሉ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት - ምሽት 2:30 ድረስ ብቻ የእግረኞች እንቅስቃሴ ደግሞ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽት 4:00 ድረስ ብቻ እንዲሆን የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል።

በተጨማሪ፦
- የአንኮበርና ጅሩ መስመርን ጨምሮ በ4ቱም ኬላዎች የተጠናከረ ፍተሻ እንዲካሄድ
- የ24 ሰዓት ፓትሮል/ጥበቃ እንዲደረግ
- በርካታ ህዝብን የሚያከብሩና የህዝቡን ህልውና አደጋ ላይ የማይጥሉ ወጣቶችን መመልመል ማደራጀትና ማሰልጠን
- የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት ከጸጥታ ኃይለሉ ጋር በማቀናጀት ስምሪት እንዲሰጥ፣
- ተመላሽ ሰራዊት አባላትን አደራጅቶ ወደ ስራ እንዲገቡ
- አከራይ ተከራይን መለየት 50ለ5 የብሎክ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል
- የፓለቲካ አመራሩና የቀበሌ አመራሩ ህብረተሰቡን የማነቃቃት ስራ እንዲሰሩ
- በየቀበሌው የስጋት ቦታዎች ተለይተው ልዪ ጥበቃ እንዲደረግ
- ለጸጥታ ሃይሉ አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲሟሉ
- የህብረተሰቡን ስነ ልቦና በመገንባት ማረጋጋትና ማነቃቃት እንዲቻች
- ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በየቀበሌው የተጠለሉ ወይም የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ማንነት መለየት
- ህገወጥ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦችን በ1 ሳምንት ውስጥ ወደህጋዊ መስመር ማስገባት
- የመረጃ ስርዐቱ ከወትሮው በተለየ የተጠናከረ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል።

ያንብቡ : telegra.ph/DB-10-20

@tikvahethiopia
#DebreBirhan : በደብረ ብርሃን ከተማ የባጃጅና ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡ ተገለፀ።

በከተማ አስተዳደሩ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቋረጥ የተደረገበት ምክንያት በከተማው ያለውን የሰዎች እንቅስቃሴ መቆጣጠር እንዲቻል መሆኑ ተጠቁሟል።

የከተማው ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በየአካባቢው ሰርጎ ገቦችን በመከታተልና የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ሃገራዊ ኃላፊነታቸውን እዲወጡ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል::

@tikvahethiopia
#DebreBirhan

በደብረ ብርሃን ከተማ #ከነገ ጀምሮ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች እና የደብረ ብርሃን ከተማ መታወቂያ ካላቸው ግለሰቦች ውጪ በከተማው ውስጥ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ፥ " በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ሰርጎ ገቦች ገብተው አካባቢን የማጥናትና መረጃ የመስጠት ስራ እየሰሩ እንደሆነ ስለተደረሰበት ሰርጎ ገቦችን መለየትና አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ነጻ ለማድረግ ነው " ብሏል።

በዚህም ለከተማውና ለነዋሪዎች ደህንነት ሲባል በከተማው በየትኛውም አካባቢ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና መታወቂያ ካላቸው ሰዎች ውጪ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ የማይቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ የተጠለሉ ወገኖችም በተዘጋጀላቸው መጠለያ እንዲገቡ ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#DebreBirhan

በደብረብርሃን ተፈናቅለው የሚገኙ ከ12,000 በላይ ሰዎች የመጠለያ፣ የማዕድ ቤት እቃዎች፣ ምንጣፎች፣ የሶላር መብራቶች እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲደርሳቸው ማድረጉን ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) አሳውቋል።

በተጨማሪም የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ከ6,000 በላይ የተፈናቀሉ ሰዎችን መርዳት እንዲችል የመጠለያ እና የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ የደብረብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል ለቆሰሉ እና ለተፈናቀሉ ሰዎች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማጠናከር እንዲያግዝ የተለያዩ የድንገተኛ ህክምና መድሃኒቶችን እና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

@tikvahethiopia