" አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በአስተማማኝ ሰላም ላይ ይገኛል " - ዶ/ር ቀነዓ ያደታ
ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉ የአፍሪካ የኤዢያና ፓስፊክ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ተደረገ።
በመድረኩ ላይ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ፤ የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል የከተማው የፀጥታ ሀይል ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ከሪፐብሊካን ጥበቃ ሃይል ፣ከኦሮሚያ ፖሊስ እና ከሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።
ከ27 ሺህ በላይ ወጣቶች እንዲሁም ህዝባዊ ሰራዊት የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታን የሚያስከብሩ አደረጃጀቶች እስከ ታችኛው የብሎክ መዋቅር ድረስ በመደራጀት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልፀው በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በአስተማማኝ ሰላም ላይ መሆኗን አስረድተዋል።
በምዕራባዊያን ሚዲያዎች የሚነዙትን የፕሮፖጋንዳ እና የሽብር ወሬ መሬት ላይ ካለዉ የከተማዋ የተረጋጋ ሰላም ጋር ፍፁም የሚጋጭ በመሆኑ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባው ዶ/ር ቀነዓ ያደታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መረጃውን ያገኘ ነው ከAAPS ነው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ዛሬ እና ነገ ይመሰረታል። 5 ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ ሆነው የሚያቋቁሙት የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዛሬና ነገ በሚካሄዱ መርሀ ግብሮች 11ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ይመሰረታል፡፡ ለክልሉ ምስረታ ከአምስቱ ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የተውጣጡ የሥራ ሃላፊዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ ከትላንት ምሽት ጀምራ የክልል እና የፌደራል እንግዶች ለክልሉ…
#Update
ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በሀገራችን 11ኛው የክልል መንግሥት በይፋ ይመሰረታል።
11ኛው የክልል መንግሥት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በቦንጋ ከተማ ይመሰረታል።
በቦንጋ እየተካሄደ በሚገኘው የክልል ምስረታ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንግዶችና ከ6ቱም መዋቅሮች የተገኙ የህዝብ ተወካዮች፣ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የሃይማኖት አባቶችና ምሁራን እንዲሁም ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
#SRTA

" እስካሁን ወደላሊበላና ኮምቦልቻ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የጠየቀ አንድም የዓለም አቀፍ ተቋም የለም "– አቶ ምትኩ ካሳ
የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ላሊበላ እና ኮምቦልቻ አየር ማረፊያዎች የሰብዓዊ ድጋፍ በረራ ፍቃድ ቢሰጥም እስካሁን ድረስ ድጋፍ ለማድረስ የጠየቀ አንድም የዓለም አቀፍ ተቋም እንደሌለ የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ አሳወቁ።
ኮሚሽነሩ ይህ ያሳወቁት ለኢፕድ በሰጡት ቃል ነው።
" በአካባቢዎቹ ለአምስት ወራት ያህል ድጋፍ ያላገኙና እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች አሉ" ያሉት አቶ ምትኩ ካሳ፥ " መንግሥት ሁኔታዎችን ሲያመቻች ገብተው ሰብዓዊ ድጋፍ የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደተግባራዊ እርምጃ አልገቡም" ብለዋል።
በሰሜን እና ደ/ወሎ አካባቢዎች ከተፈናቀሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ባለፉት ወራት እርዳታ ሳይቀርብላቸው የቆዩ ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንደሚገኙ ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች ወደአካባቢዎቹ እርዳታ ጭነው ቢሄዱና ሰብአዊ ድጋፍ ቢያቀርቡ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን መታደግ የሚቻልበት አማራጭ መኖሩንም አሳውቀዋል።
የዓለም አቀፍ ተቋማት ጦርነት እየተካሄደባቸው በማይገኙ ቦታዎች ላይ ገብተው ድጋፍ የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው ያሉት አቶ ምትኩ የሚሠሩት ሥራ የሰብዓዊነት ዓላማ እስካለው ድረስ የእራሳቸውን መለያ እና አርማ አድርገው ድጋፍ ለማድረግ ወደየስፍራዎቹ መግባት ይችላሉ ሲሉ ገልፀዋል።
አማራና አፋር ክልሎች ያለው የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች ድጋፍ የሚጠበቀውን ያህል እንዳልሆነ የገለፁት አቶ ምትኩ፥ "ችግሩን ለመፍታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት ከየተቋማቱ ጋር ተደጋጋሚ ውይይት አድርገናል። በዚህ መነሻነት ለውጦች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል" ብለዋል።

#Update ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በሀገራችን 11ኛው የክልል መንግሥት በይፋ ይመሰረታል። 11ኛው የክልል መንግሥት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በቦንጋ ከተማ ይመሰረታል። በቦንጋ እየተካሄደ በሚገኘው የክልል ምስረታ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንግዶችና ከ6ቱም መዋቅሮች የተገኙ የህዝብ ተወካዮች፣ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የሃይማኖት አባቶችና ምሁራን እንዲሁም ነዋሪዎች ተገኝተዋል።…
#Update
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመስርቷል።
11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ህገ መንግስትም በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
የምክር ቤቱ አባላትም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።
ምንጭ፦ የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው
@tikvahethiopia
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመስርቷል።
11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ህገ መንግስትም በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
የምክር ቤቱ አባላትም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።
ምንጭ፦ የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመስርቷል። 11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ህገ መንግስትም በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። የምክር ቤቱ አባላትም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል። ምንጭ፦ የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው @tikvahethiopia
#Update
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስራ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
የዞን መዋቅሮች ደግሞ የራሳቸውን ቋንቋ እንደሚገለገሉ ተገልጿል።
የስልጣን እርከን ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ፣ አፈጉባኤየክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳትና የብሄረሰብ ምክር ቤት አፈጉባኤ በአንድ ጊዜ ከተመሳሳይ ብሄር እንዳይሆኑ ተቀምጧል።
የስልጣን ገደብም የተቀመጠ ሲሆን÷ በተለያየ ምክነያት ከጊዜያቸው ቀድሞ ሊለቁ መቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ረጅም ጊዜ ቢቆዩ ከ10 ዓመት እንዳይበልጥ ተመላክቷል።
የብዝሓ ማዕከል ወይንም ዋና ከተማ እንዲኖርም ተደንግጓል፣ የትኞቹ ከተሞች እንደሚሆኑ በዝርዝር ህግ በም/ ቤት እንዲወሰንም በህገ መንግስቱ መጠቀሱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopoa

#Update የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስራ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ፀድቋል። የዞን መዋቅሮች ደግሞ የራሳቸውን ቋንቋ እንደሚገለገሉ ተገልጿል። የስልጣን እርከን ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ፣ አፈጉባኤየክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳትና የብሄረሰብ ምክር ቤት አፈጉባኤ በአንድ ጊዜ ከተመሳሳይ ብሄር እንዳይሆኑ ተቀምጧል። የስልጣን…
#Update
አቶ ወንድሙ ኩርታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና አፈጉባኤ ፤ ወይዘሮ ገነት መንገሻ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።
ሁለቱም አፈ ጉባኤዎች ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
@tikvahethiopia
አቶ ወንድሙ ኩርታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና አፈጉባኤ ፤ ወይዘሮ ገነት መንገሻ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።
ሁለቱም አፈ ጉባኤዎች ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ወንድሙ ኩርታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና አፈጉባኤ ፤ ወይዘሮ ገነት መንገሻ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል። ሁለቱም አፈ ጉባኤዎች ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። @tikvahethiopia
#Update
ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ም/ርዕስ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ።
ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ በክልልና በሀገር ደረጃ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች የሰሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የውሃና መስኖ ሚንስቴር ዴኤታ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።
ም/ርዕስ መስተዳደሩ በጉባኤው አባላት ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

#WFP #USAID
USAID በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አቁሞ ከአገሪቱ ሊወጣ ነው የተባለ ሐሰት ነው ሲል አስታወቀ።
ድርጅቱ ይህን ያሳወቀው ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ነው።
USAID እየተካሄደ ባለው ጦርነት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ማቅረብ መቀጠሉን አስታውቋል።
የተቋሙ ቃል አቀባይ ሬቤካ ክሊፍ ፥ " የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሠራተኞቻችን ከአገሪቱ ቢወጡም፤ በሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ከሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን " ብለዋል።
በሌላ በኩል ፦የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በሚገኘው ኮምቦልቻ ውስጥ ያሉት የሰብዓዊ እርዳታ ማከማቻ መጋዘኖቹ መዘረፋቸውን ዛሬ ገልጿል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ቶምሰን ፊሪ ፥ ባለፈው ሳምንት የዓለም ምግብ ድርጅት በአማራ ክልል ኮምቦልቻ የሰብዓዊ እርዳቃ እንዲያቀርብ ፍቃድ አግኝቷል ብለዋል።
ድርጅቱ ባደረገው ቅድመ ግምገማ መሠረት በርካታ ንብረቶቹ መውደማቸውን እና መጋዘኖች ውስጥ የነበረ እህልም መዘረፉን አሳይቷል ሲሉ ገልፀዋል።

#Update የአብኑ አመራር ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር አብረው እንደሚዘምቱ አሳወቁ። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መከላከያን በግንባር ሆነው ለመምራት ከነገ ጀምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እንደሚዘምቱ ካሳወቁ በኃላ የአብን አመራር እና የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚዘምቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል። አቶ ክርስቲያን…
#ETHIOPIA
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ፤ በግንባር መሰለፍን ጨምሮ ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አሉ።
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ይህ ያሉት ለኢዜአ በሰጡት ቃል ነው።
" በኢትዮጵያ የተደቀነው አደጋ አፍሪካን የማንበርከክ ዓላማ ጭምር ያነገበ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ሙከራ ነው " ያሉት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ፥ " " ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት ናት ፤ ኢትዮጵያን በማንበርከክ የጥቁር ሕዝቦችን አኩሪ ታሪክ ለመቀማት የተቀናጀ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ እየተከናወነ ይገኛል" ብለዋል።
ከዚህ አኳያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ክብር ወደ ግንባር መዝመታቸው አገሩን ከሚወድ መሪ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእርሳቸውን ፈለግ እንዲከተል ጥሪ አቅርበዋል።
መላ አፍሪካዊያን ትግሉ የሁሉም ጥቁር ሕዝቦች መሆኑን በመገንዘብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል።
አትሌት ኃይሌ ፦ "ኢትዮጵያን ብለን ተሸንፈን አናውቅም፤ ኢትዮጵያ ሁሌም አሸናፊ ናት" ሲሉ ነው የተናገሩት።
በአንድ ወቅት የጎበኟት የቱሪስት መናኸሪያ የነበረችውን የሶሪያዋ አሌፖ ከተማ በምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት ምክንያት ወደ ፍርስራሽነት መቀየሯን ጠቅሰዋል።
"በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን በአገራችን ላይ ይህን መፍቀድ የለብንም" ያሉት አትሌት ኃይሌ ፤ " ከዚህ አንጻር ከደጀንነት ባሻገር በግንባር በመሰለፍ ጭምር አገሬ በምትፈልገኝ ቦታ ለማገልግል ዝግጁ ነኝ " ብለዋል ለኢዜእ በሰጡት ቃላቸው።

#StateofEmergencySomalia
ሶማሊያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች። ሀገሪቱ በከፍተኛ ድርቅ መጠቃቷን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀችው።
እየተባባሰ በመጣው ወቅታዊ የድርቅ ሁኔታ ላይ የሃገሪቱን ካቢኔ ለአስቸኳይ ስብሰባ የጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሮብል አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አውጀዋል፡፡
“ሃገራችን በድንገተኛ ሰብዓዊ አደጋ ላይ ትገኛለች” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያጋጠመውን አስከፊ ድርቅ ሰላባዎች እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ባለችው ጎረቤት አገር ሶማሊያ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ለከፋ ድርቅ ተጋልጠዋል፡፡
በርካቶች ለችግር መዳረጋቸውን የተመድ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማስተባበሪያ አስታውቋል፡፡
በሶማሊያ ባለፉት ሶስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ያልዘነበ ሲሆን በተለይም ጁባ እና ሸበሌ ወንዞች የውሃ መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ የድርቁን ደረጃ እንዳባባሰው ድርጅቱ አክሏል፡፡
የድርቅ መጠኑ በተለይም ከቀጣዩ ታህሳስ ወር ጀምሮ እስከ መጋቢት ድረስ እንደሚባባስ የገለጸው ድርጅቱ ተጎጂዎችን ለመርዳት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡
Credit : Al AIN News