TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ " በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየሰራው ነው " ሲል ገልጿል። ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ…
#Update

" ግለሰቦቹ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ባዘጋጁት ተሽከርካሪ እቃዎችን ጭነው ሄደዋል " - ቢሮው

ሰኞ ዕለት በመርካቶ ያሉ ነጋዴዎች " ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው የመጣነው " ያሉ ሰዎች ያለ ደረሰኝ ለምን ሸጣችሁ በሚል እቃችንን ወርሰውብናል ብለዋል።

በዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በእለቱ በመርካቶ ያሉ በርከት ያሉ ሱቆች ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ፥ የተባለው ችግር በመርካቶ እንደተፈጠረ አምኖ ነገር ግን የነጋዴዎችን እቃ ወርሰዋል የተባሉት ግለሰቦች ከገቢዎች ቢሮም ይሁን ከየትኛውም የመንግስት አካል ያልተወከሉ ህገ ወጦች ናቸው ሲል ማመልከቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

የታክስ ኢንቴሌጀንስና ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ነጋሽ " እኛ ምንም አይነት ንብረት የመውረስ መብት የለንም መወረስ ካለበትም ይህንን የሚሰራው የጉምሩክ ኮሚሽን ነው " ብለዋል፡፡

" ግለሰቦቹ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ባዘጋጁት ተሽከርካሪ እቃዎችን ጭነው ሄደዋል፤ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ደግሞ ገንዘብ ተቀብለው ተሰውረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ነጋዴዎቹ ለፀጥታ አካላት መረጃዎችን በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " መንግስት ከመርካቶ ገበያ የነጋዴዎችን እቃ መውረስ ጀመረ " ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ግን ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ውዥምብሩ የተፈጠረው በዚህ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ከዚህ ቀደም ይሰራ እንደነበረው ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይፈፀም ለማድረግ ያለመ የቁጥጥር ስራ እነደሆነ ኃላፊው ጠቁመዋል።

ከህዳር 1 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዘመቻ መልክ ነው እየተሰራ ያለው።

ከዚህም በተጨማሪ ቢሮው በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመርካቶን የንግድ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠሩ ባለሙያዎች " ያለ እጅ መንሻ " የማይሰሩ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሎ ሁሉንም የመርካቶ ተቆጣጣሪዎችን በማንሳት በአዲስ መተካቱንም ተናግሯል።

ያለ ደረሰኝ ሲገበያይ የተገኘን ማንኛውም ሰው 100 ሺህ ብር እንደሚቀጣም አሳውቋል።

ቢሮው መርካቶን ጨምሮ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ያሉ አምራቾች፣ አስመጪዎችና ቸርቻሪዎች የትኛውንም ግብይት በደረሰኝ እንዲፈፅሙ ይገደዳሉ ማለቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ገልጿል።

ነጋዴዎች ምን ይላሉ ?

በመርካቶ ያለው ችግር ውስብስብ ያለና ከላይ ጀምሮ መጥራት ያለበት ነው።

በተለይ ደግሞ የገቢዎች ተቆጣጣሪ የሚባሉት ያለ ገንዘብ ያለ ሙስና አይሰሩም።

ሆን ብለውም የማስጨነቅ ስራ በመስራት ከነጋዴው ገንዘብ የመቀበልን ተግባራ ስራቸው ያደረጉ እንዳሉ ይገልጻሉ።

ያለ ደረሰኝ ግብይት ተደረገ ተብሎም የገንዘብ ድርድር የሚያደርጉ ተቆጣጣሪዎችም አሉ።

ደረሰኝን በተመለከተ ቸርቻሪው ላይ ጣትን ከመቀሰር ከላይ ጀምሮ ያለውን ነገር ማጥራት እንደሚገባ ነጋዴዎች ጠቁመዋል።

#AddisAbaba #Merkato

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ግለሰቦቹ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ባዘጋጁት ተሽከርካሪ እቃዎችን ጭነው ሄደዋል " - ቢሮው ሰኞ ዕለት በመርካቶ ያሉ ነጋዴዎች " ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው የመጣነው " ያሉ ሰዎች ያለ ደረሰኝ ለምን ሸጣችሁ በሚል እቃችንን ወርሰውብናል ብለዋል። በዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በእለቱ በመርካቶ ያሉ በርከት ያሉ ሱቆች ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ፥ የተባለው ችግር…
" የቢሮ ሰራተኛ መሆናቸውን መታወቂያና መለያ ባጅ ጠይቋቸው  " - ገቢዎች ቢሮ

ዛሬ የገቢዎች ቢሮ መርካቶ ሸራ ተራ አካባቢ " በገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ " ስም ሲያጭበረብር ነበረ የተባለ ግለሰብ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

ቢሮው ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጋር አካሄድኩት ባለው ክትትል ነው ግለሰቡ የተያዘው።

በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ ግለሰብ በመርካቶ ገበያ በአንድ ግለሰብ ሱቅ ውስጥ በመግባት የዕቃዎች ደረሰኝ ሲጠይቅና ሲያጭበረብር በደረሰ ጥቆማ መሠረት ለማምለጥ ሲሞክር በፖሊስ መያዙን ቢሮው አስረድቷል።

ቢሮው " የንግዱ ማህበረሰብ ማንኛውም በግል ወይም በቡድን የሚንቀሳቀሱ አጭበርባሪዎች ወደ ንግድ ስፍራቸው ሲመጡ የቢሮ ሰራተኛ መሆናቸውን መታወቂያና መለያ ባጅ በመጠየቅ ሊያረጋግጥ ይገባል " ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ አጠራጣሪ ድርጊቶች ሲያጋጥሙት በነፃ የስልክ መስመር  7075 በመጠቀም እንዲጠቁም ጥሪ አቅርቧል።

በተለይ መርካቶ ገበያ የሚሰሩ ዜጎች " ከገቢዎች ነው የመጣነው " በሚሉ አካላት በሆነው ባልሆነው ገንዘብ እንደሚጠየቁ ፤ " ያለ ደረሰኝ ስትሸጡ ነበር " በማለትም የገንዘብ ድርድር አድርገው ከነጋዴዎች ገንዘብ የሚቀበሉ ሰራተኞች እንዳሉ ይናገራሉ።

በአንዳንድ ሰራተኞች ምክንያት ስራ መስራት እንዳልተቻለና ከነጋዴው ገንዘብ የሚቀበሉትም የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር መሆኑንም አስረድተዋል።

በዚህም በቸርቻሪው ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚደርስ በማመልከት ቢሮው መጀመሪያ የራሱን ሰራተኞች እንዲጠራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠቱት ቃል ጠይቀዋል።

#AddisAbaba #Merkato

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

" በቦታው ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ምክረ ሃሳብ ቀርቧል። ያቀረብነው ምክረ ሃሳብ ቦታው እንደ አዲስ በመልሶ ማልማት እንዲለማ ነው " - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በትላንትናው ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ የእሳት አደጋ ያጋጠመው በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ገበያ የሚገኝ አካባቢ፤ " በመልሶ ማልማት እንዲለማ " ምክረ ሃሳብ ቀረበ።

ምክረ ሃሳቡን ያቀረበው የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።

ትላንት እሁድ ህዳር 8/2017 እኩለ ቀን ገደማ የእሳት አደጋ የደረሰበት የመርካቶ ገበያ ስፍራ፤ በተለምዶ " ድንች ተራ " የሚል ስያሜ ያለው ነው።

ስፍራው ከሁለት ሳምንት በፊት በተመሳሳይ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ከነበረው " ነባር የገበያ ማዕከል " በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።

የእሁዱ ቃጠሎ የደረሰበት ስፍራ፤ " በነባር የገበያ ማዕከል " ላይ የሚነግዱ ነጋዴዎች ንብረቶቻቸውን የሚያስቀምጡበት መጋዘን እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች " ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጽ ተናግረዋል። 

የእሳት አደጋው " ጌሾ ግቢ " ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከሚገኘው መጋዘን በተጨማሪ በአቅራቢያው የሚገኙ መደብሮች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ውድመት አድርሷል። 

ትላንት በአደጋው ወቅት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ነጋዴዎች የእሳት ቃጠሎው ወደ ሌሎች የገበያ ማዕከሎች እና መደብሮች እንዳይዛመት በስጋት ሲያስተውሉ ነበር።

የተወሰኑ የአካባቢው ወጣቶች እና ከእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ጋር በመሆን ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማድረግ ርብርብ ሲያደርጉ ነበር።

በአንድ ሰዓት ተኩል ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋለውን የእሳት አደጋ ለመከላከል፤ ሰባት የውሃ ቦቴዎች እና 18 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጽ ገልጸዋል።

ከእነዚህ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ የኮሚሽኑ እና የቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንሶች፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ወደ ህክምና ተቋማት በመውሰድ ተሳትፈዋል። 

በትላንቱ የእሳት አደጋ ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እና ሁለት የኮሚሽኑ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በዚሁ አካባቢ በደረሰው ተመሳሳይ አደጋ፤ ዘጠኝ ሰዎች መጎዳታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁ አይዘነጋም።

የትላንቱ አደጋ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች አካባቢውን በገመድ በማጠር ጥበቃ ሲያደርጉ ነበር።

ክልከላውን አልፈው ለመግባት ሲሞክሩ የነበሩ ነዋሪዎች እና ነጋዴዎችን፤ የፖሊስ አባላቱ ወደ ቦታው እንዳይጠጉ በኃይል ሲከላከሉም ነበር።

ፖሊሶች እና የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ከመድረሳቸው በፊት ግን የተወሰኑ ነጋዴዎች ንብረቶቻቸውን ከቃጠሎ ማትረፍ ችለዋል።

በዚህም ምክንያት በአደጋው " የከፋ ጉዳት " አለመድረሱን አቶ ንጋቱ አስረድተዋል።

ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላም፤ ነጋዴዎች ንብረታቸውንን ከአካባቢው ለማራቅ ሲጥሩ ታይተዋል። 

ነጋዴዎች፤ አካባቢው በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመው በመሆኑ ምክንያት " መንግስት ከስፍራው ያነሳናል " የሚል ከፍተኛ ስጋት አላቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አካባቢውን " ለአደጋ ተጋላጭ " በሚል አስቀድሞ መለየቱን የገለጹት አቶ ንጋቱ፤ በቦታው ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን አስረድተዋል። 

" ያቀረብነው ምክረ ሃሳብ ቦታው እንደ አዲስ በመልሶ ማልማት ወይም የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ቧሟላ፣ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ መገንባት ይኖርበታል ነው። ምክረ ሃሳቡን ተቀብሎ በመልሶ ማልማት ለመስራት የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉ መረጃው አለን። በሂደት ላይ ነው ያለው። ታምኖበታል። ምን አልባትም በዚህ አመት ሊጀመር ይችላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።

#AddisAbaba #Merkato #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
#Update

ከሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎችን በጊዜያዊነት መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አካባቢው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መልሶ እንደሚገነባ ጠቁመዋል።

" እስከዛው ሱቅ ለተቃጠለባቸው ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የአይነት እና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን " ብለዋል።

ከንቲባዋ ፤ " በአካባቢው ያለውን ጥግግትና መጨናነቅ በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የተሽከርካሪ መንገድን በማካተት እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በማያደርጋቸው መልኩ በዘላቂነት በአክሲዮን ተደራጅተው ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል መገንባት እንዲችሉ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ ይደረጋል " ሲሉ ገልጸዋል።

#MayorOfficeofAddisAbaba #Merkato #ShemaTera

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነጋዴዎች #ደረሰኝ #መርካቶ

" ደረሰኝ መቆረጥ አለበት በዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር የለውም " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ በተለይ በግዙፉ የገበያ ማዕከል ' መርካቶ ' በንግድ ስርዓቱ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ነጋዴዎች ሱቅ የመዝጋትና ስራ የማቆም እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ሰሞነኛውን የመርካቶ ገበያ ሁኔታ በተመለከተም ነጋዴዎቹ ከከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተቀምጠው ነበር።

በውይይቱ በነጋዴዎቹ በኩል በርካታ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ተነስተው ነበር። ለተነሱት ጥያቄዎች የመንግሥት አካላት ምላሽ ሰጥተዋል።

ነጋዴዎች ሃሳባቸው ፣ ጥያቄያቸው፣ ቅሬታቸው ምንድነው ?

➡️ ደረሰኝ መቁረጥ ፣ ግብር መክፈል ለሀገር ወሳኝ ፤ ለራስም ይጠቅማል። ግን አከፋፈሉ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።

➡️ እኛ ስንገበያይ ደረሰኝ እናገኛለን ወይ ? አንዳንድ ምርት የሚነሳው ከገበሬ ነው። ከገበሬ ነጋዴ ይሰበስባል ይከፍላል፣ ተረካቢው ይረከባል ይከፍላል፣ ተጭኖ ይመጣል እኛ እንረከባለን ይሄ ሁሉ ይከፍላል ብዙ ነገር ነው ያለው። የቆረጠው ይቆርጥልናል የሌለውን ንግድ ፍቃድ እናያይዛለን። እንዲህ ስንሰራ ነው የቆየነው።

➡️ ሁሉም እየመጣ ባለድርሻ ነኝ ይላል። መርካቶ እንደምንታመስ ያውቃል ሌባው ይገባና " ሄደህ 100 ሺህ ብር ከምትቀጣ ለኔ ይሄን ስጠኝ " ይላል።

➡️ እቃው በደላላ ነው የሚመጣው ፤ ድሮ አስመጪ በእያንዳንዱ ሱቅ ሄዶ እቃ ይበትን ነበር አሁን ግን አስመጪው ለደላላ፣ ለቤተሰብ ፣ ለዘመዱ ፣ ለጎረቤት፣ ለጓደኛ ነው የሚሰጠው። እቃው ይመጣና በተለያየ መጋዘን ይቅመጣል ከዛ በስልክ ነው ልውውጥ የሚደረገው ነጋዴው ደላላውን ' ደረሰኝ ስጠኝ ' ካለው ነገ እቃ አይሰጥም።

➡️ ቁጥጥር እየተባሉ የሚመደቡ ሰዎች ባጅ የላቸው፣ ምናቸውም አይታውቅ፣ ሱቅ የሚገቡት እንደ ሌባ 3 እና 2 እየሆኑ ነው ስለዚህ ህጋዊ ይሁኑ ህገወጥ ምናቸው ይለያል ?

➡️ ባልተማከለ ሲስተም ውስጥ ነው ያለነው። ደረሰኝ አልቆረጣችሁም በሚል መቶ ብር አትርፈን 100 ሺህ ብር ነው የምንጠየቀው።

➡️ እስቲ ኢንዱስትሪውን ተቆጣጠሩ ደረሰኝ ቼክ ይደረግ የሚወጣው አንደርኢንቮይስ ከሆነ በምን አግባብ ነው ነጋዴው የሚጠየቀው ?

➡️ " ደረሰኝ ቁረጡ ደረሰኝ ቁረጡ " ሲባል ሌላ ነገር ነው የሚመስለው ደረሰኝ ይዞት የሚመጣው ገንዘብ ነው። መጀመሪያ የንግድ ስርዓቱ መስተካከል አለበት።

➡️ ለ100 ሺህ ብር ቅጣት በዚህ ፍጥነት ከተሰራ ነጋዴውን ለማገዝ በገንዘብ ሚኒስቴር የሚሰጠቱን ዕድሎች ተፈጻሚ ለማድረግ ለምን አልተቻለም ?

➡️ አሰራሩ እኮ ብዙ ነው። አልታየም። እንደ ከተማ አንድም አስመጪ የለም። አስመጪዎቹ ' መርካቶ መጥተን አንሸጥም ጅግጅጋ መጥታችሁ ግዙ ' ይሉናል። በደረሰኝ ስንት ስቃይ ነው ያለው። እዛ ተኪዶ ነው ሚገዛው ? እሺ እዚህ ስናመጣ ገቢዎች ላይ ብዙ ነገር አለ ፤ ደረሠኝ ይጥላሉ፣ ' አንቀበልም ' ይላሉ የት እንሂድ ?

➡️ አሰራሩ ላይ ትልቅ ችግር አለ።

➡️ አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ አስመጪዎች ደረሰኝ ይሰጣሉ ወይ ? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው።


ለነጋዴዎች ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ምን መለሱ ?

🔴 የገቢዎች የቁጥጥር ሰራተኞችን በተመለከተ መታወቂያ አላቸው፣ 3 እና 4 ሆነው ነው የሚገቡት። መታወቂያ የሌለው ካለ ህገወጥ አጭበርባሪ ነው ተከላከሉት።

🔴 " የገቢዎች ሰራተኛ ነን " ብለው ሲያጭበረብሩ የተያዙ ሰዎች አሉ።

🔴 ለገቢዎች ሰራተኞች መታወቂያ ተሰጥቷል። መታወቂያ ማሳየት አለባቸው። እናተም ጠይቋቸው።

🔴 ደረሰኝ ላለመቁረጥ የሚሰጡትን ምክንያቶች በጋር እየተነጋገርን እንፈታለን እንጂ ደረሰኝ መቁረጥ እንዲቆምላችሁ የምትጠይቁትን ጥያቄ መንግስት መመለስ አይችልም። ይሄን በግልጽ እወቁት።

🔴 በገቢዎች ውስጥ ያሉ ችግሮች ይታወቃሉ መፈታት አለባቸው። ከብልሹ አሰራር፣ ከሌብነት ጋር በተያያዘ የተነሱ ችግሮች ይታረማሉ።

🔴 ቫትን በተመለከተ በአዲሱ አሰራር 7 ሺህ ብር ነው የቀን ግምቱ የተቀመጠው። ቀደም ሲል ቫት የነበረ ወደ ታች ሊወርድ አይችልም። በቀን 7 ሺህ ብር የሚሸጥ ሰው ምን ያክል ነው የሚለውን እናተው ታውቃላችሁ። ቅድሚያ እየተሰጠ ያለው ቫት ውስጥ መግባት እያለበት ቫት ውስጥ ያልገባው ነጋዴ በተለይ መርካቶ እሱ ባለመግባቱ በሚሸጠው እቃ ላይ የዋጋ ልዩነት እየመጣ ስለሆነ ቫት ውስጥ መግባት ያለበትን ቫት ውስጥ እያስገባን ነው።

🔴 ቫት ውስጥ የነበረ ነጋዴ ልወርድ ይገባል ብሎ ተጨባጭ ማስረጃ ካቀረበ ይታያል። አሁን ባለው የዋጋ ንረት እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እንጂ እላይ የነበረው ወደ ታች አይወርድም።

🔴 የቁጥጥር ስርዓቱ እየጠበቀ ነው የሚሄደው።

🔴 እኛ ስለትላንቱ አለነሳንም አሁን ግን መርካቶ የሚደርገው ግብይት በደረሰኝ እና በደረሰኝ ብቻ መሆን አለበት። ይህን የሚያደርገውን ነጋዴ እንደግፋለን።

🔴 ነጋዴው በህጋዊ መንገድ ይጠቀም አልን እንጂ ነጋዴውን የሚያስቀይም ፣ የሚያሳድድ እርምጃ ለመውሰድ የሚፈልግ አካል የለም።

🔴 መርካቶ የሚደረገው እንቅስቃሴ በክልል ጥያቄ ያስነሳል። መረካቶ ደረሰኝ ስለማይቆረጥ የንግዱ ማህበረሰብ ክልል ሄዶ ሲነግድ ደረሰኝ አቅርቡ ሲባል " ያለ ደረሰኝ ነው የገዛነው እዛ ደረሰኝ አልተቆረጠም " የሚሉ አሉ።

🔴 የዚህ አመት እቅዳችን ግዙፍ የሆነ ገቢ ለመሰብሰብ አቅደናል። ይህን የምናደርገው የታክስ ቤዛችንን በማስፋት፣ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ በመቀየር ነው።

🔴 ኢ-መደበኛ እናሳድዳለን አላልንም ግን ወደ መደበኛ ይግባ እያልን ነው።

🔴 ብዙዎቻችሁ (ነጋዴዎች) ያነሳችሁት ጥያቄ ደረሰኝ እንዳይቆረጥ የሚጠይቅ ዝንባሌ አለው። " ደረሰኝ አያስፈልግም " አትሉም ግን ጅምላውን፣ አከፋፋዩን ፣ አምራቹን ቅድሚያ ስጡ ነው የምትሉት። ጅምላውም ላይ፣ አከፋፋዩም ላይ ፣ አምራቹም ላይ እንሰራለን ቸርቻሪም ላይ እንደዛው ይሰራል። ሁሉም ደረሰኝ መቁረጥ አለበት።

🔴 ደረሰኝ ለመቁረጥ የማይስችል ሁኔታ ካለ ማስረዳት ነው እንጂ " ደረሰኝ አንቆርጥ " የሚል እሳቤ ተቀባይነት የለውም።

🔴 በደረሰኝ መቆረጥ አለበት ምንም አይነት ድርድር የለውም በዚህ ጉዳይ። እኛ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ እናስገባለን።

🔴 አቤቱታ ካላችሁ በማንኛውም ጊዜ አቅርቡ። ገቢዎች አካባቢ ያለውን ነገርም እንፈትሻለን።

#AddisAbaba #Merkato

@tikvahethiopia